ነብዩ ኢስማኤል

Author picture
ነብዩ ኢብራሂም ከሐጀር እና ከልጃቸው ኢስማኤል ጋር ምግብ ፣ ፍራፍሬ ፣ ዛፍ እና ውሃ ወደሌለበት ያልታረሰ ጠፍ ወደሆነው ሸለቆ ተሰደዱ። ይህ ቦታ አሁን ላይ መካ ተብሎ ይጠራል።
ኢስማኤል

ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ከሚስታቸው ሐጀር የወለዱት የበኩር ልጃቸው ነብዩ ኢስማኤል (ዐ.ሰ)  ነው። አሏህ (ዐ.ሰ) ስለ እሱ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ መርየም 19፡54-55)

“በመጽሐፍ ውስጥ እስማኤልን አውሳ፤ በእርግጥ እሱ በቃልኪዳኑ እውነተኛ ነው። መልዕክተኛም ነብይም ነበር። ቤተሰቦቹን በሶላትና በዘካ ያዘ ነበር። ከጌታውም ዘንድ ተወዳጅ ነበር።

ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ከሐጀር እና ከልጃቸው ኢስማኤል ጋር ምግብ ፣ ፍራፍሬ ፣ ዛፍ እና ውሃ ወደሌለበት ያልታረሰ ጠፍ ወደሆነው ሸለቆ ተሰደዱ። ይህ ቦታ አሁን ላይ መካ ከተማ ተብሎ ይጠራል።

እዚህ ቦታ ላይ ነብዩ ኢብራሂም ትንሽየ ምግብና ውሃ ሰጥቷቸው ትቷቸው ሄደ። ባሏ ይሄን በፈቃዱ እንዳላደረገ እና ይህን አሏህ እንዲያደርግ አዞት እንደሆነ በመረዳት አሏህ አይተወንም አለች።

አሏህ እሷን እና ልጇን እንደማይተዋቸው እርግጠኛ ነበረች። አሏህም ቅር አላሰኛቸውም። ከመሬት ውሃ እንዲፈልቅላቸው አደረገ። ይህ ውሃ የዘምዘም ውሃ ተብሎ ይጠራል።

ከጅርሁም ጎሳ የሆኑ ሰዎች በእነሱ በኩል እስካለፉበት ጊዜ ድረስ እዚሁ ቦታ ላይ ኖሩ። የውሃ ምንጭ ባገኙ ጊዜ ከእሷና ከልጇ ጋር አብረው መቆየት ይችሉ እንደሁ ጠየቋት። እሷም ተስማማች። ኢስማኤል (ዐ.ሰ) አድጎ ለአቅማዳም በደረሰ ጊዜ ከእነሱ መካከል የሆነች ሴት አገባ።

ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) መስዋዕት እንዲያደርግ አሏህ ያዘዘው እስማኤልን ነበር። ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) በህልሙ ኢስማኤልን መስዋዕት ሲያደርገው እንዳየ ለልጁ ሲነግረው ኢስማኤል (ዐ.ሰ)

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ሷፋት 37፡102 )

“አባቴ ሆይ! እንደታዘዝከው አድርግ። አሏህ ከሻ(ከፈቀደ) ከታጋሾች ሆኜ ታገኘኛለህ አለ።”

ሁለታቸውም ለአሏህ ፈቃድ እራሳቸውን ሰጡ። ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ልጁን ሊያርድ በግንባሩ ደፍቶ ያዘ። ሞከረ አልቻለም፤ ሞከረ አልቻለም። አሏህ ራዕዩን እንደ ፈፀመ ነግሮት ትልቅ ወጠጤ በግ በምትኩ ሰጠው። ከእሱ ጊዜ በኋላ ለሚመጡ ትውልዶች ጥሩ ማስታወሻን ጥሎ አለፈ።

በካዕባ ግንባታ አባቱን ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) የረዳው ነብዩ ኢስማኤል (ዐ.ሰ) ነው። ይሄን ካደረጉ በኋላ ፀለዩ

አል-ቁርአን

(ሱረቱል በቀራ 2፡127)

“ጌታችን ሆይ! አገልግሎታችነን ተቀበለን። በእርግጥ ሁሉን ሰሚና ሁሉን አዋቂ አንተ ነህ።”

ኢብራሂም ፣ ዘምዘም ተመልከቱ

Related posts

ነብዩ ዩኑስ

ነብዩ ዩኑስ

ነብዩ ዩኑስ (ዐ.ሰ) ወይም ነብዩ ዩሃንስ ህዝባቸው የጣኦት አምልኮትን እንዲተው ፣ አሏህን ብቻ እንዲያመልኩ እና ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ ጥሪ እንዲያደርጉ አሏህ ለአሲርያዎች የላካቸው ነብይ ናቸው።

Read More »
ነብዩ ሱለይማን

ነብዩ ሱለይማን

ነብዩ ሱለይማን (ዐ.ሰ) የነብዩ ዳውድ (ዐ.ሰ) ልጅ ነው። ጠንካራ ንጉስ ሲሆን ከአሏህ ታላላቅ ነብያትም ውስጥ አንዱ ነው። አሏህ ሃይልን ፣ ጥበብ እና እውቀት ሰጥቶታል።

Read More »
ነብዩ ሷሊህ (ዐ.ሰ)

ነብዩ ሷሊህ (ዐ.ሰ)

ነብዩ ሷሊህ (ዐ.ሰ) አሏህ የላካቸው በሰሜን ምዕራብ አረቢያ ፣ በመዲና እና በሶሪያ መካከል ይኖሩ ለነበሩ የሰሙድ ህዝቦች ነው። ይህ ቦታ አለታማ እና ትልቅ ለም ሸለቆ

Read More »

Share