ነብዩ ሱለይማን (ዐ.ሰ) የነብዩ ዳውድ (ዐ.ሰ) ልጅ ነው። ጠንካራ ንጉስ ሲሆን ከአሏህ ታላላቅ ነብያትም ውስጥ አንዱ ነው። አሏህ ሃይልን ፣ ጥበብ እና እውቀት ሰጥቶታል።
ነብዩ ሱለይማን

ሱለይማ (ዐ.ሰ) የነብዩ ዳውድ (ዐ.ሰ) ልጅ ነው። ጠንካራ ንጉስ ሲሆን ከአሏህ ታላላቅ ነብያትም ውስጥ አንዱ ነው። አሏህ ሃይልን ፣ ጥበብ እና እውቀት ሰጥቶታል።

የአዕዋፍትን እና የእንሰሳትን ቋንቋ እንዲረዱ አሏህ አስተምሯቸዋል። ቅዱስ ቁርአን እንዲህ ይነግረናል።

በአንድ ወቅት ጉንዳኖች ይኖሩበት በነበረ ሸለቆ ነብዩ ሱለይማን እና ወታደሮቹ ሲያልፉ አንድ ጉንዳን ወገኖቹን “ሱለይማን እና ወታደሮቹ ሳይጨፈልቋችሁ ወደ ቤታችሁ ሽሹ” እያለ ሲያስጠነቅቅ ሰማው።

በአንድ ወቅት ጉንዳኖች ይኖሩበት በነበረ ሸለቆ ሱለይማን እና ወታደሮቹ

ይህን እንደሰማም ነብዩ ሱለይማን (ዐ.ሰ) ፈገግ ብለው “ሃይልና ችሎታን ሰጠኸኝ፤ በእኔና በወላጆቼ ላይ የለገስከንን ፀጋሀን እንዳመሰግን የምትወደውንም በጎ ስራ እንድሰራ ምራኝ። ከመልካም ባሮችህም አድርገኝ” ሲሉ ዱአ አደረጉ። (አል-ቁርአን 27፡19) ላይ ተመልከቱ።

ንፋስ ነብዩ ሱለይማን እንዲያገለግለው አሏህ አድርጓል። በትዕዛዙ ይነፍሳል። የፈለገበት ቦታ ያደርሰዋል።

በእሱ ትዕዛዝ ጅኖች እንዲሰሩ አድርጓቸዋል። የፈለገውንም ያደርጋሉ። አንዳንዶቹ ወደ ባህር በመግባት ድንቅ ሃብቶቿን ያመጣሉ።

ንፋስ ሱለይማን እንዲያገለግለው አሏህ አድርጓል።

አንዳንዶቹ የሰው ልጆች ሊሰሩ የማይችሉትን እጅግ በጣም ከባድ ስራዎች ይሰራሉ። ወታደሮቹ እንኳ ከሰው ፣ ከጅን እና ከአዕዋፍት የሆኑ ናቸው። አሏህ የቀለጠ ነሐስ እንዲፈስለት አድርጓል።

እነዚህ እና ለሌሎች አለማዊ ስጦታዎች ነብዩ ሱለይማን (ዐ.ሰ) ሁሌም አሏህን ያመሰግናሉ እንዲሁም ሰዎች አሏህን ብቻ እንዲያመልኩ እና አሏህ በእነሱ ላይ ያደረገውን ጸጋ አስበው እንዲያመሰግኑ ያስተምሩ ነበር።

አንድ ቀን ነብዩ ሱለይማን (ዐ.ሰ) አዕዋፍቱን እየፈተሸ ባለበት ሁፖ የምትባለው ወፍ ከመካከላቸው አለመኖሯን ልብ አሉ። ላለመኖሩ ጥሩ ምክኒያት ካልኖረው በቀር……..። ወዲያውኑም ወፉ ጠቃሚ ዜና እየበረረ ይዞ መጣ።

ሁፖ የምትባለው ወፍ

ሼባ ተብሎ ከሚየታ ራቅ ካለ ከተማ እንደመጣ እና ይህን ሐገር የምትገዛ… ቢልቂስ የምትባል ንግስት በጣም እፁብ ድንቅ የሆነ ዙፋን ጨምሮ በጣም ብዙ ነገር አላት።

ይህ ሁሉ ሃብት ቢኖራቸውም ሸይጧን እሷን እና ህዝቦቿን በሃያሉ አሏህ ፈንታ ፀሐይን እንዲያመልኩ አታሏቸዋል አለ።

የወፉን መረጃ ለማረጋገጥ ነብዩ ሱለይማን (ዐ.ሰ) ወፉን አስይዞ ልግስቷ ደብዳቤ ላከ። ደብዳቤው እሷን እና ህዝቦቿን አሏህን ብቻ እንዲያመልኩ የሚጣራ ነበር።

አማካሪዎቿን አማከረች። እነሱም በሱለይማን ላይ ጦር ለመምዘዝ ከበቂ በላይ ሃይለኖችነ እና ጠንካሮች ነን አሉ።

ሁፖ

ቢልቂስ ሃሳቡን አልወደደችውም፤ ይልቁንም እጅግ ውድ የሆኑ ስጦታዎችን ለሱለይማን ልትልክ ወሰነች።

ይህ ለመልዕክተኞቿ ስለ ሱለይማን (ዐ.ሰ) እና ስለወታደሮቹ ጥንካሬ ለማወቅ የሚችሉበት ጥሩ አጋጣሚ እንደሆነ አሰበች።

ድንቅ ስጦታዎቿን ከሱለይማን ፊት በቀረቡ ጊዜ ሱለይማን (ዐ.ሰ) “እናንተ ከያዛችሁት በላይ አሏህ ለእኔ የሰጠን እጅግ በጣም በላጭ ነው። ከእናንተ የምፈልገው ሙስሊም እንድትሆኑ ነው” አላቸው።

ስጦታውን መልሰው ይዘውላት እንዲሄዱ እና ይህን አይነት አምልኮቷን የማታቆም ከሆነ ግዛቷን እነደሚያወድመውና ህዝቦቹን እንደሚያሰደታቸው እንዲነግሯት አዘዘ።

መልዕክተኞቹ መልዕክቱን ባደረሱ ጊዜ ሱለይማንን ለመጎብኘት ወሰነች። ጉብኝቷን እንዲያሳውቁላት መልዕክተኛ ላከች።

እሷ ከመድረሷ በፊት ከጅኖች መካከል ዙፋኗን እንዲያመጡለት ሱለይማን (ዐ.ሰ) ጠየቃቸው። ከሰዎች መካከል የሆነ እውተኛ አማኝ፤ የሱለይማን ግዛት ፈለስጢን እና የቢልቂስ ደግሞ የመን ውስጥ ቢሆንም አንኳ የአሏህን ታላቅ ስም የሚያውቅ ሰው በአይን እርግብግቢት ፍጥነት ይዞለት መጣ።

ቢልቂስ የነብዩ ሱለይማን ቤተ መንግስት በደረሰች ጊዜ ድንቅ በሆነ ዝግጅት ደስ የሚል አቀባበል ተደረገላት። በትንሹ ቅርፁን ወደ ተቀየረው ዙፋኗ እየጠቆመ ዙፋንሽ ይሄን ይመስላል እንዴ ብሎ ጠየቃት።

በጥንቃቄ ካየችና ከፈተሸች ቡኋላ የሚያመሳስለውን ነገር ልብ ስላለች “ልክ የኔኑ ነው የሚመስለው” ስትል መለሰችለት። በዚህ መልሷ በጣም ብለህ እንደሆነች ተረዳ።

ቢልቂስ የሱለይማን ቤተ መንግስት በደረሰች ጊዜ

ወደ ትልቁ አዳራሽም ጠራት። ወለሉ ምስልን የሚያሳይ ፣ ከስር ውሃ ይመስላል። ውሃ እንደሆነ ስላሰበች ወለሉን ስትረግጥ የታችኛውን ልብሷን በትንሹ ከፍ አድርጋ ነበር። ከለስላሳ ጠርሙስ እንደተሰራም ነብዩ ሱለይማን (ዐ.ሰ) ነገሯት።

ቢልቂስ እጅግ በጣም ጠንካራ ከሆነ ንጉስ እና ከአሏህ መልዕክተኛ ጋር እንደሆነች ስለተረዳች የፀሐይ አምልኮቷን ትታ ነብዩ ሱለይማን (ዐ.ሰ) ወደ ጠሯት እውነተኛ እምነት መጣች፤ ህዝቦችቿም እንዲያምኑ ጠየቀች።

ጅኖች የማዕድን ስራቸው ላይ

በአንድ ወቅት ጅኖች የማዕድን ስራቸው ላይ መሆናቸውን እየተቆጣጠሩ ባለበት በድንገት ሞቱ። ቀጥ ብለው በተቀመጡበት አኳኋን ለረዥም ጊዜ ቆይተዋል። አንዳቸውምመሞታቸውን አላወቁም።

ጅኖቹ ሱለይማን (ዐ.ሰ) አሻግሮ እያየን ነው ብለው በማሰብ ስራቸውን ቀጠሉ። ጋደም ባሉበት በኩል ትል ትል እየቆነጠረ ሲበላቸው ቆየ።

ከብዙ ቀናት በኋላ ጉንዳኖቹ የሱለይማን ምርኩዝ ይበሉ ጀመር። የምርኩዛቸውን የታችኛውን ክፍል መብላት ቀጠሉ። ምርኩዛቸው ከእጃቸው ወደቀ። አካላቸው መሬት ላይ ረገፈ።

ሰዎችም ተሯሩጠው ወደ እሳቸው ሄዱ። ሞተዋል። ጅኖች የሩቅ ሚስጥርን አያውቁም፤ ቢያውቁ ኖሮ ነብዩ ሱለይማን (ዐ.ሰ) በህይወት አሉ እያሉ ስራቸውን ባልቀጠሉ ነበር።

ጉንዳኖቹ የሱለይማን ምርኩዝ ይበላ ጀመር

Related posts

ነብዩ ዩኑስ

ነብዩ ዩኑስ

ነብዩ ዩኑስ (ዐ.ሰ) ወይም ነብዩ ዩሃንስ ህዝባቸው የጣኦት አምልኮትን እንዲተው ፣ አሏህን ብቻ እንዲያመልኩ እና ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ ጥሪ እንዲያደርጉ አሏህ ለአሲርያዎች የላካቸው ነብይ ናቸው።

Read More »
ነብዩ ሷሊህ (ዐ.ሰ)

ነብዩ ሷሊህ (ዐ.ሰ)

ነብዩ ሷሊህ (ዐ.ሰ) አሏህ የላካቸው በሰሜን ምዕራብ አረቢያ ፣ በመዲና እና በሶሪያ መካከል ይኖሩ ለነበሩ የሰሙድ ህዝቦች ነው። ይህ ቦታ አለታማ እና ትልቅ ለም ሸለቆ

Read More »
ሑድ (ዐ.ሰ)

ሑድ

የአድ ህዝቦች በደቡባዊ አረብያ ከኦማን የአረቢያ ባህረሰላጤ እስከ የመን ሐድራሙት ደቡባዊ የቀይ ባህር ጫፍ ድረስ ባለው በጣም ሰፊ ሐገር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ዝቦች ናቸው። ጡንቻቸው

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share