አሏህ እንዲህ ይላል፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ኢምራን 3:42)
“መላእክትም ያሉትን (አስታውስ)፡፡ «መርየም ሆይ! አላህ በእርግጥ መረጠሸ፡፡ አነፃሽም፡፡ በዓለማት ሴቶችም ላይ መረጠሽ፡፡»”

አሏህ እንዲህ ይላል፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ኢምራን 3:59)
“አላህ ዘንድ የኢሳ ምሳሌ እንደ አዳም ብጤ ነው፡፡ ከዐፈር ፈጠረው፡፡ ከዚያም ለርሱ (ሰው) «ኹን» አለው፤ ሆነም፡፡”
አሏህ እንዲህ ይላል:
አል-ቁርአን
(ሱረቱ ኒሳዕ 4:171)
“እናንተ የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በሃይማኖታችሁ ወሰን አትለፉ፡፡ በአላህም ላይ እውነትን እንጅ አትናገሩ፡፡ የመርየም ልጅ አልመሲሕ ኢሳ የአላህ መልክተኛ ወደ መርየም የጣላት «የኹን» ቃሉም ከእርሱ የሆነ መንፈስም ብቻ ነው፡፡ በአላህና በመልክተኞቹም እመኑ፡፡ « (አማልክት) ሦስት ናቸው» አትበሉም፡፡ ተከልከሉ፤ ለእናንተ የተሻለ ነውና፡፡ አላህ አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእሱ ልጅ ያለው ከመሆን የጠራ ነው፡፡ በሰማያት እና በምድር ያለ ሁሉ የሱ ነው፡፡ መመኪያም በአላህ በቃ፡፡”

ሙስሊሞች ነብዩ ኢሳ (እየሱስ) እና እናቱ መርየም ይወዳሉን?
ነብዩ ኢሳ (እየሱስን) በቅዱስ ቁርአን ውስጥ በአስራ ስድስት የተለያዩ አጋጣሚዎች በግልጽ ተጠቅሷል።
አላህ እንዲህ ይላል፡-
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ማኢዳ 5፡110)
“አላህ በሚል ጊዜ (አስታውስ)፡- «የመርየም ልጅ ኢሳ ሆይ! በአንተና በእናትህ ላይ (የዋልኩላችሁን) ጸጋዬን አስታውስ፡፡ በሕፃንነትና በከፈኒሳነት (የበሰለ ሰው ሆነህ) ሰዎችን የምትናገር ስትሆን በቅዱስ መንፈስ (በገብሬል) ባበረታሁህ ጊዜ፤ ጽሕፈትንና ጥበብንም ተውራትን እና ኢንጂልንም ባስተማርኩህ ጊዜ ፣ ከጭቃም የወፍ ቅርጽ ብጤ በፈቃዴ በምትሠራ እና በውስጧ በምትነፋ በፈቃዴም ወፍ በምትሆን ጊዜ ፣ እውር ሆኖ የተወለደንና ለምጻምንም በፈቃዴ በምታሽር ጊዜ ፣ ሙታንንም በፈቃዴ (ከመቃብራቸው) በምታወጣ ጊዜ ፣ የእስራኤልንም ልጆች በተአምራት በመጣህባቸውና ከእነሱ እነዚያ የካዱት ይህ ግልጽ ድግምት እንጅ ሌላ አይደለም ባሉ ጊዜ ፣ (ሊገድሉህ ሲያስቡህ) ከአንተ ላይ በከለከልኩልህም ጊዜ (ያደረግሁልህን ውለታ አስታውስ)፡፡”
በሌላ በኩል ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) በቅዱስ ቁርአን ውስጥ አራት ጊዜ ብቻ በግልጽ ተጠቅሰዋል፡፡
የእየሱስ እናት የሆነችው ድንግል ማርያም ግን ስምንት ጊዜ የተጠቀሰች ሲሆን በእሷ ስም የተሰየመ ሙሉ ሱራ (ምዕራፍ) አለ።
ሁሉን ቻይ የሆነው አላህ እንዲህ ብሏል፡-
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ኢምራን 3፡45)
“መላእክት ያሉትን (አስታውስ)፡- «መርየም ሆይ! አላህ ከእሱ በሆነው ቃል ስሙ አልመሲህ ዒሳ የመርየም ልጅ በዚህ ዓለም እና በመጨረሻውም ዓለም የተከበረ ከባለሟሎችም በሆነ (ልጅ) ያበስርሻል፡፡»”
ቤተሰባቸው በተከበረው ቁርአን ውስጥ ሦስት ጊዜ ተጠቅሷል።
እንዲሁም በእነሱ ስም የተሰየመ ሙሉ ሱራ (ምዕራፍ) (አሊ-ዒምራን) በመኖሩ ተከብረዋል።
ይህ ምዕራፍም በምእመናን ልብና አእምሮ ውስጥ ለዘላለም ተቀርጿል።




Share