ነብዩ ዩኑስ (ዐ.ሰ) ወይም ነብዩ ዩሃንስ ህዝባቸው የጣኦት አምልኮትን እንዲተው ፣ አሏህን ብቻ እንዲያመልኩ እና ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ ጥሪ እንዲያደርጉ አሏህ ለአሲርያዎች የላካቸው ነብይ ናቸው።
ነብዩ ዩኑስ

ነብዩ ዩኑስ (ዐ.ሰ) ወይም ነብዩ ዩሃንስ ህዝባቸው የጣኦት አምልኮትን እንዲተው ፣ አሏህን ብቻ እንዲያመልኩ እና ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ ጥሪ እንዲያደርጉ አሏህ ለአሲርያዎች የላካቸው ነብይ ናቸው።

የመጀመሪያ ማስጠንቀቂያውን ሳይቀበሉ በቀሩ ጊዜ የአሏህ ቁጣ በእነሱ ላይ እንዲሆን ተማፀኑ። ከተማውን ለቀው ወጡ። ነገርግን ሰማዩ ጠቆር ቀለሙን ለወጥ ፣ ጓጓታው በርታ ባለ ጊዜ ይሄማ እንደ ዩኑስ አድ ሰሙድ እና ኑህ ህዝቦች ልንጠፋ ነው ብለው ቶብተው ለጊዜው አሏህ ማራቸው።

ማዕባሉ በተነሳላቸውም ጊዜ ነብዩ ዩኑስ (ዐ.ሰ) እንዲመለስላቸው ፀለዩ።

ዩኑስ (ዐ.ሰ) ቀኑን ሙሉ እየተጓዙ መርከቡ ላይ ተሳፍረዋል። ቀኑ በጨለማ በተተካ ጊዜ በድንገት ማዕበል ነፈሰ። ማዕበሉ መርከቡን የሚሰነጥቀው ይመስል ነበር። ባህሩ ተናወጠ፤ የማዕበሉ ውሽንፍር በጣም ከፍ አለ። ማዕበሉ ቀጠለ።

የመርከቡ አዛዥ የመርከቡን ጭነቶች ባህሩ ላይ እንዲያራግፉ ሰራተኞቹን አዘዛቸው። ጓዝ ሁሉ ተጣለ። ይህ ብቻውን ግን በቂ አልነበረም። ደህንነታቸው አሁንም ክብደት መቀነስ ላይ ነው። እናም ጭነታችነን ለመቀነስ ቢያንስ አንድ ሰው እንኳ እንቀንስ ብለው ወሰኑ።

እጣ ተጥሎ ስሙ የወጣበት ወደ ባህሩ ሊወረወር እጣ እናወጣለን ተባለ። በተጓዞቹ ሁሉ ስም እጣ አወጡ። እጣው ያረፈበት ወደ ባህሩ ይወረወራል አለ አዛዡ። ሰውን ወደ ባህር መወርወር የባህር ላይ ሰዎች እና የሙሽሪኮች ባህል ነው።

ዩኑስ (ዐ.ሰ) ሳይፈልጉት ተሳተፉ። እጣው እሳቸው ላይ አረፈ። ከመካከላቸው የታወቁ የተከበሩ በመሆናቸው ወደ ባህሩ ሊጥሏቸው አልፈለጉም።

ለሁለተኛ እና ለሶስተኛ ጊዜ እጣ ጣሉ፤ ሁለተኛውም ሶስተኛውም እሳቸው ላይ አረፈ። ወደ ባህሩም ተወረወሩ። በአሏህ ትዕዛዝ አሳ ነባሪ ዋጣቸው። አሳ ነባሪው ወደ ታችኛው የባህሩ ክፍል ጠለቀ።

አሳ ነባሪ

ሶስት የጨለማ ሽፋን አንዱ በአንዱ ላይ አካበባቸው። የአሳ ነባሪው ሆድ ጨለማ ፣ የባህሩ የታችኛው ክፍል ጨለማ እና የሌሊቱ ጨለማ ናቸው። ነብዩ ዩኑስ (ዐ.ሰ) በጥልቁ ጨለማ ውስጥ ሆነው አለቀሱ።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አንቢያ 21፡87)

ተቆጥቶ በሄደ ጊዜ (አስታውስ)። በእሱ ላይ ፈፅሞ የማን ፈርድበት መሆናችነን ጠረጠረ። (አሳውም ዋጠው) በጨለማዎች ውስጥ ሆኖ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡። ጥራት ይገባህ። በእርግጥ እኔ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ።

ዩኑስ (ሰ.ዐ.ወ) ደጋግመው ዱአ አደረጉ አሏህን መማፀናቸውን ቀጠሉ። አሏህ ተውባቸውን ተቀበላቸው፤ ማራቸውም። አሳነባሪው በባህሩ ዳርቻ ላይ እንዲተፋቸው ታዘዙ።

መጠለያውን እና ከፍራፍሬ መጠቃቀሚያውን ተሰጡ። በመፀፀቱና እሱን በመማፀኑ ባይሆን ኖሮ የአሳ ነባሪው ሆድ ውስጥ እስከ ፍርዱ ቀን ድረስ ይቆይ እንደነበር አሏህ በቁርአኑ ውስጥ ይናገራል።

መንፈሳቸው ቀለል አካለቸው ጠበቅ ባለጊዜ ተልዕኮውን እንዲፈፅሙ አሏህ አዘዛቸው።

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ሷፋት 37፡147-148)

ወደ መቶ ሽህ እና ከዚያ በላይ ለሆኑ (ደግመን) ላክነው። አመኑ፤ እስከ ጊዜ ድረስ ስንቅን (ምቾትን) ሰጠናቸው።

Related posts

ነብዩ ሱለይማን

ነብዩ ሱለይማን

ነብዩ ሱለይማን (ዐ.ሰ) የነብዩ ዳውድ (ዐ.ሰ) ልጅ ነው። ጠንካራ ንጉስ ሲሆን ከአሏህ ታላላቅ ነብያትም ውስጥ አንዱ ነው። አሏህ ሃይልን ፣ ጥበብ እና እውቀት ሰጥቶታል።

Read More »
ነብዩ ሷሊህ (ዐ.ሰ)

ነብዩ ሷሊህ (ዐ.ሰ)

ነብዩ ሷሊህ (ዐ.ሰ) አሏህ የላካቸው በሰሜን ምዕራብ አረቢያ ፣ በመዲና እና በሶሪያ መካከል ይኖሩ ለነበሩ የሰሙድ ህዝቦች ነው። ይህ ቦታ አለታማ እና ትልቅ ለም ሸለቆ

Read More »
ሑድ (ዐ.ሰ)

ሑድ

የአድ ህዝቦች በደቡባዊ አረብያ ከኦማን የአረቢያ ባህረሰላጤ እስከ የመን ሐድራሙት ደቡባዊ የቀይ ባህር ጫፍ ድረስ ባለው በጣም ሰፊ ሐገር ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ዝቦች ናቸው። ጡንቻቸው

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share