ዱአ (ፀሎት) ከልብ አሏህን መለመን ነው። ለአለማዊ ጥቅም ለምሳሌ ሃብት ፣ ስኬት ፣ ጤና ወይም ደግሞ ለሃይማኖታዊ ጥቅም ለምሳሌ ምህረት ለማግኘት ፣ ጀነት ለመግባት ሊደረግ ይችላል። ዱአ የሙእሚኖች መሳሪያ ነው፡፡

አሏህ (ሱ.ወ.ተ) አማኞች እሱን እንዲለምኑ ሲያዝ እንዲህ አለ፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ጋፊር 40፡60)
“ጌታችሁም አለ ለምኙኝ እቀበላችኋለሁና።”
ዱአ ምላሽ የሚያገኝባቸው ጊዚያት
አንድ ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዳሉት ለዱአ አሏህ ምላሽ የሚሰጥበት የተወሰኑ ጊዜያት አሉ።
ከእነዚህ ጊዜያቶች መካከል የመጨረሻው የሌሊቱ አንድ ሶስተኛ ፣ በአዛን እና በኢቃም መካከል ያለችው ጊዜ ፣ በጁምአ ቀን ሰአቷ ያልተወሰነች ጊዜ ፣ በአረፋ ቀን ፣ ከፈርድ ሶላት መጨረሻ ፣ ሌሊት ሲነቁ ፣ በለይለቱል ቀድር ምሽት እና ዝናብ ሲጥል ናቸው።

እንዲሁም አሏህ በፍትህ እጦት የሚሰቃዩ ፣ የመንገደኞች ዱአ ፣ ወላጆች ለልጆቻቸው የሚያደርጉት ዱአ ፣ የፆመኛ ሰው ዱአ ይቀበላል።
ዱአን አሏህን በማመስገን እና በማላቅ ፣ የአሏህን ሰላምና በረካን በመልዕክተኛው ላይ እንዲሆን በመለመን መጀመር ያስፈልጋል።
ሃጢያትን በማመን እና ተውባ በማድረግ ፣ ቁጥር ስፍር የለሌለው ችሮታውን ማመስገን ፣ እሱን በቅንነት መገዛት ፣ የነብዩ ዱአዎችን መጠቀም ያስፈልጋል።
እንዲሁም የአሏህን ሰላም እና በረከት በነብዩ ሙሐመድ ላይ እንዲያደርግ በመለመን ዱአውን መጨረስ።
ዱአ አደራረግ
ዱአ ሊደረግ የሚገባው ሙሉበሙሉ እራስን ዝቅ አድርጎ በመተናነስ ነው። ዱአን ማድረግ የሚገባውም ለአሏህ ብቻና ብቻ ነው።
ፀሎት ስታደርጉ በንፅህና ላይ ሆናችሁ ወደ ቂብላ በመዞር እጃችሁን ከፍ አድርጋችሁ የሰራችኋቸውን መልካም ስራዎች በመጥቀስ በስሞችና በባህሪያቶቹ ለምኑት።
ዱአ በሚያደርጉ ጊዜ እብሪተኛ መሆን አያስፈልግም። ለምሳሌ ለዘላለሙ አኑረኝ ማለት ፣ ስንት አመት ለመንኩት ምላሽ የለም ማለት ፣ ነብይ አድርገኝ ማለት ወ.ዘ.ተ መታገስ ያስፈልጋል።
እንዲሁም አሏህ ለዱአችን ምላሽ የሚሰጠን ቢሆንም ወዲያውኑ ምላሽ መጠበቅ አይኖርብነም።
ነገርግን አሏህ ለሚያውቀው ምክኒያት ምላሽ ካላገኘን ታግሰን ውጤት እስክናይ ድረስ ፀሎት ማድረግ አለብን።
አቡ-ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪና ሙስሊም)
“የባሪያው ፀሎት በአሏህ ምላሽ ያገኛል ትዕግስት አጥቶ “አሏህን ለመንኩት ነገርግን ዱአየ ምላሽ አላገኘም” ካላለ በቀር።”
ለፀሎት ምላሽ የሚሰጠው አሏህ ብቻ መሆኑን መረዳት እና ለባሪያው መልካም ነገር የሚሰጠው እሱ ብቻ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል።
ገቢው ሃላል (የተፈቀደ) መሆኑን ማረጋገጥም ያስፈልጋል። ዱአ አድረገን ከጨረስን በኋላ ኢንሻ አሏህ (አሏህ ከፈቀደ) ማለት የለብንም።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አንድ ወቅት ሲናገሩ የሆነ ሰው አሏህን በለመነ ጊዜ ከሚከተሉት መካከል አንዱ ይሆናል
- አሏህ ለዱአው ምላሽ ይሰጣል፤ የጠየቀውንም ነገር ይሰጠዋል
- ዱአ አድራጊውን ከጉዳት ይጠብቀዋል
- ለፍርዱ ቀን የሚቀመጥለት መልካም ምንዳ ይመነዳዋል ሲሉ ጠቅሰዋል።
አረፋ ፣ አዛን ፣ ኢቃማ ፣ እና ለይለቱል ቀድር ተመልከቱ



Share