ዚክር ማለት አሏህን ማስታወስ ማለት ነው። ዚክር በምላስ ወይም ደግሞ በቀልብ ማድረግ ይቻላል።

ነገርግን በላጩ ዚክር ሁለቱንም አጣምሮ በመጠቀም የሚደረግ ነው። አሏህ ሙእሚኖች ዚክር እንዲያደርጉ አዟቸዋለው።
አል-ቁርአን
(አል-ቁርአን 33፡41-42)
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ማውሳት ብዙ አውሱት። ጧትና ማታም አልቁት።”
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
“አሏህ ብሏል ‹እኔ አገልጋየ እንደሚጠብቀኝ ነኝ፤ እኔን ባነሳ ጊዜ ከእሱ ጋር ነኝ። ለእራሱ (ለብቻው) ካነሳኝ፤ ለእራሴ አነሳዋለሁ። በጀመአ (በስብሰባ) መሃል ካነሳኝ፤ ከእሱ በተሻለ ስብሰባ ማሃል አነሳዋለሁ” ብሏል ብለዋል።

በአንድ ወቅት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶሃባዎቻቸውን እንዲህ ሲሉ ጠየቁ “ከንጉሳችሁ (አሏህ) ዘንድ ንፁህ የሆነ ፣ ደረጃችሁን ከፍ የሚያደርግ ፣ ወርቅና ብር (ሶደቃ) ከምትሰጡት በላይ በላጭ፤ ጠላቶቻችሁ ጋር ተገኛኝታችሁ አንገታቸውን ከምትመቱና አንገታችሁን ከሚመቱ በላይ ከተግባሮቻችሁ ሁሉ በላጩን አላሳውቃችሁምን? ሶሃባዎችም አሳውቁን አሏቸው። እሳቸውም አሏህን ማስታወስ” ነው አሉ።
ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶሃባዎች መካከል አንዱ የሆነው ሙአዝ ኢብን ጀበል (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አለ “አንድን ሰው ከአሏህ ቅጣት የሚያድን ምንም የለም አሏህን ማስታወስ ቢሆን እንጅ። (ትርሚዚ)

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አሏህን ዘወትር ያስታሱ ነበር። ከመተኛታቸው በፊት ፣ ሲራመዱ ፣ ሽንትቤት ሲገቡ ፣ ከእሱ ሲወጡ ፣ ከቤት ሲወጡ ፣ ወደ ገበያ ሲገቡ እና ሌላም ሌላም።
አሏህን የምናስታውስባቸውን የዚክር ስብስቦች የያዙ መጽሐፍት አሉ። እነዚህን ዚክሮች በቀልብ መማር እና የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና መከተል ያስፈልጋል።

አንዳንዶቹ የዚክር አይነቶች ተህሚድ (አልሃምዱ ሊላህ–ምስጋና ለአሏህ) ፣ ተህሊል (ላኢላሃ ኢለሏህ) ፣ ተስቢህ (ሱብሃን አሏህ) እና ተክቢር (አሏሁ አክበር—አሏህ ሃያል ነው) የሚሉትን ይይዛል።
አሏህን ማስታወስ ብዙ ጠቀሜታዎች አሉት። የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪና ሙስሊም)
“ላኢላሃ ኢለሏሁ ወህደሁ ላሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሃምዱ ወሁወ አላ ኩሊ ሸይኢን ቀዲር (ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፤ አንድ ብቸኛ ነው)። ለእሱ ባላንጣ ተጋሪ የለውም። ንግስና ምስጋናም የእሱ ብቻ ነው። እሱ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ ነው።”

ይህን መቶ ጊዜ ያለ ሰው፤ አስር ባሪያዎችን ነፃ የማድረግ ያህል ምንዳ ያገኛል። አንድ መቶ ደግ ስራዎች ይፃፉለታል።
አንድ መቶ ሃጢያቶች ከመዝገቡ ይታበስለታል። ያን ቀን እስከ ምሽት ድረስ ከሸይጧን መከላከያ ጋሻ ይሆንለታል።
በፍርዱ ቀን እሱ ይዞት ከሚመጣው በላይ በላጭ ሆኖ የሚመጣ የለም፤ ከእሱ በላይ አሏህን ያስታወሰ ቢሆን እንጅ። (ቡኻሪና ሙስሊም)
ተስቢህ እና ተክቢር ተመልከቱ



Share