ተክቢር አሏህ አክበር ማለት ነው። ብዙ ትሩፋቶች ያሉት የዚክር አይነት ነው። ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ሙስሊም)
“(እነዚህን ቃላት ያለ) ሱብሃን አሏህ (አሏህ ከድለት የፀዳ ነው) ፣ ወልሐምዱ ሊላህ (ምስጋና ለአሏህ) ፣ ወላኢላሃ ኢለሏህ (ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም) ፣ ወሏሁ አክበር(አሏህ ሃያል ነው) ማለት ፀሐይ ከወጣችበት ነገር ሁሉ በላይ ለእኔ የተወደደ ነው።”

አሏህ አክበር የሚለው ቃል ትልቅ ከመሆኑ የተነሳ በአዛን መጀመሪያ እና መጨረሻ ላይ ፣ ከሶላት መጀመሪያ ላይ ፣ ሩኩዕ ሲያደርግ ፣ ሱጁድ ሲያደርጉ ፣ ከሲጁድ በኋላ ሲቀመጡና ሲነሱ የመሚባል ነው። በብዙ አጋጣሚዎችና ጊዜያትም ይባላል።
ለምሳሌ አዲስ ጨረቃ ስትታይ ፣ በኢዱል ፊጥር እና በኢዱል አዱሃ ወቅት ነው። ተክቢር በዙልሂጃ በዘጥኝኛው ቀን ጧት ፈጅር ላይ ይጀምርና በአስራ ሶስተኛው ቀን ከአስር ቡኋላ ያበቃል።
ኢደል ፊጥር በተመለከተ ተክቢራው የሚጀምረው ወደ ኢድ ሶላት መሄድ በተጀመረበት ጊዜ ሲሆን የሚያበቃው ደግሞ ኢማሙ ሶላቱን ለማሰገድ ብቅ እስካለበት ጊዜ ድረስ ነው።
በእነዚህ ሁለት ወቅቶች የሚባለው እንደሚከተለው ነው። ‹አሏህ አክበር ፣ አሏህ አክበር ፣ ላ ኢላሃ ኢለሏህ ፣ አሏህ አክበር ፣ አሏህ አክበር ወሊላሂል ሐምድ (አሏህ ታላቅ ነው ፣ አሏህ ታላቅ ነው ፣ ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም ፣ አሏህ ታላቅ ነው ፣ አሏህ ታላቅ ነው፣ ምስጋና ይገባው።”
አሏህ አክበር ማለት አሏህ የሁሉ የበላይ ነው ማለት ነው። እሱ ጠንካራው ፣ ሃያሉ ፣ የሻውን ሰሪ ነው። እሱ የያዘውን የሚሰጥ ፣ የሰጠውን የሚይዝ አንድም የለም። ከአሏህ በቀር ህይወት የሚሰጥ እና ሞትን የሚያስከትል አንድም የለም።
ዚክር ፣ ተስቢህ ፣ ኢደል ፊጥር እና ኢዱል አዱሃ ተመልከቱ



Share