ኢድ በአል ምንድን ነው ሙሰሊሞችስ ለምን ያከብሩታል?

Author picture
ኢድ የአረብኛ ቃል ሲሆን በአል የሚል ትርጉም አለው። በእስልምና ሃይማኖት ያሉት ሁለት ኢዶች ወይም በአላት ብቻ ናቸው። ኢደል አድሃ (የእርድ በአል) እና ኢደል ፊጥር (የፆም መፍቻ) በአል ናቸው።
ኢድ

ኢድ የአረብኛ ቃል ሲሆን በአል የሚል ትርጉም አለው። በእስልምና ሃይማኖት ያሉት ሁለት ኢዶች ወይም በአላት ብቻ ናቸው።

ኢደል አድሃ (የእርድ በአል) እና ኢደል ፊጥር (የፆም መፍቻ) በአል ናቸው። ኢዱል ፊጥር የሚከበረው በሸዋል ወር የመጀመሪያ ቀን ላይ ነው።

አሏህ ታማኝ ባሪያቹን ለረመዷን ወር ፆም ስላደረሳቸው እና ፆሙን እንዲፆሙ ስላስቻለቸው ለአሏህ ምስጋና የሚያደርሱበት የደስታ እና የምስጋና መግለጫ ነው።

ኢዱል አዱሃ ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ልጃቸው ነብዩ ኢስማኤል ለአሏህ ሲሉ መስዋዕት ለማድረግ የነበራቸውን ፍቃደኝነት እና ዝግጁነት ለማስታወስ ሲባል በዙል ሂጃ አስረኛ ቀን ላይ የሚከበር በአል ነው። በእነዚህ ሁለት በአል መፆም በጥብቅ የተከለከለ ነው።

እነዚህን ሁለት በአል ለሙስሊሞች የመረጠው አሏህ (ሱ.ወ.ተ) እራሱ ነው። “የአሏህ መልዕክተኛ ወደ መዲና በተሰደዱ ጊዜ እዚያ ያሉ ሰዎች በአመቱ ውስጥ ሁለት ቀናቶችን ለሳቅ ለጨዋታ ብለው ለይተው አገኟቸው።

እነዚህ ሁለት ቀናቶች ምንድን ናቸው ሲሉ ጠየቋቸው። “በጃሂልያው ዘመን (በድንቁርናው ዘመን) በእነዚህ ቀናቶች እንስቅ እንጫወት ነበር” ሲሉ መለሱላቸው።

እናም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ‹አሏህ ሁለት በላጭ ቀናቶችን የኢዱል አዱሃ እና የኢዱል ፊጥር ሰጣችሁ” አሉ። (አቡዳውድ እና ነሳኢ)

0%
0
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ፆም

ጥያቄና መልስ፡ ኢደል ፊጥር እና ኢደል አዱሃ

ኢደል ፊጥር እና ኢደል አዱሃ የሚለው ትምህርት ፈተና 8 ጥያቄዎችን ይዟል፡፡ ፈተናውን ለማለፍ 6 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ፡፡

1 / 8

Bookmark question icon

1 መሱአት ወይም ካረደው ነገር (በግ ፣ ፍየል ወ.ዘ.ተ) ከፊሉን መሸጥ ሸሪአዊ ብያኔው ምንድን ነው?

2 / 8

Bookmark question icon

2 አንድ ሙስሊም ሰው መስዋዕት ካረደው (በግ ፣ ፍየል) ከፊሉን አንስቶ ላራጁ ወይም ቆዳውን ለገፈፈው ሰው ስላረደለት ቢሰጠው ለእሱ የተፈቀደ ነው፡፡

3 / 8

Bookmark question icon

3 በላጭ ከሆኑ የአመቱ ቀናት መካከል

4 / 8

Bookmark question icon

4 የመስዋዕት ወይም የእርድ ጊዜ

5 / 8

Bookmark question icon

5 በእናቱ ማህፀን ውስጥ ላለ ፅንስ በእሱ ስም ዘካቱል ፊጥር መክፈል_______

6 / 8

Bookmark question icon

6 አንድ በግ _______ በቂ ነው፡፡

7 / 8

Bookmark question icon

7 በኢዱል ፊጥር ከተፈቀዱ ነገሮች ውስጥ

8 / 8

Bookmark question icon

8 በኢድ ቀን የመፆም ሸሪአዊ ብያኔ ምንድን ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 0%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

በእነዚህ ሁለት በአል ገላን መታጠብ ፣ ጥሩ ልብስ መልበስ ፣ ሽቶ መነስነስ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶሃባዎች ተግባር ነበር።

የኢድ ሶላት

ተክቢራ ጮህ ብለው ያደርጋሉ። ሰላምታን ይለዋወጣሉ፤ በተፈገቀዱ ነገሮች ይስቁ ይጫወታሉ።

እውነተኛ የአሏህ ወዳጆች በኢደል አድሃ ያረዱትን ስጋ ብቻቸውን አይበሉም።

ይልቁንም የተወሰነውን ለጎረቤቶቻቸው ፣ የተወሰነውን ለዘመዶቻቸው ፣ የተወሰነውን ለጓደኞቻቸው እና ለድሆች ያከፋፍላሉ።

የኢድ ሶላት ሁለት ረከአዎችን የያዘ ሲሆን ስግደቱ የሚፈፀመው ያለ አዛን እና ያለ ኢቃም ነው።

በማስከተልም ኹጥባ (ትምህርት) ይሰጣል። ኹጥባውም ሁለት ክፍሎች አሉት፤ በመካከላቸው ከተወሰነ ማረፍ ጋር።

የእርድ ከብቶች

ሁለቱ የኢድ ሶላቶች ተረጋገጡ እና መደበኛ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ተግባር ሲሆኑ ሁሌም ታድመውባቸዋል። እንዲሁም ወንዶችን ብቻ ሳይሆን ሴቶች እና ህፃናትም እንዲታደሙባቸው ያበረታቱ ነበር። የነዚህ ሶላቶች ወቅት የሚጀምረው ፀሐይዋ የጦር ከፍታ ያህል በአድማሱ ላይ ከፍ ብላ ከወጣች በኋላ ነው።

ነገርግን የኢደል አዱሃ ሶላት ሰዎች እርዳቸውን እንዲፈፅሙ ቀደም ብሎ በሰአቱ መስገድ በላጭ ነው።

የኢደል ፊጥር ሶላት ሰዎች ዘካቱል ፊጥር እንዲከፍሉ ለማስቻል ሰአቱን ገፋ አድርጎ መስገድ በላጭ ነው።

የኢድ ሶላት ሁለት ረከአዎችን የያዘ ሲሆን ስግደቱ የሚፈፀመው ያለ አዛን እና ያለ ኢቃማ ነው።

ስግደቱ የሚፈፀመው ሁለቱ የጁምአ ሶላት ረከዎች በሚፈፀሙበት መንገድ ሲሆን ብቸኛው ልዩነት የኢድ ሶላቶች የሚፈፀሙት በመጀመሪያው ረከአ ኢማሙ (አሰጋጁ) ሰባት ጊዜ ተክቢር (አሏሁ አክበር) ይላል፤ የሶላት መግቢያ ተክቢራን ጨምሮ  ማለት ነው።

ከእሱ ጀርባ ያሉ ተከታዮች ደግሞ በእያንዳንዱ ተክቢር እጆቻቸውን እስከ ታችኛው የጆሮ ጫፍ ወይም እስከ ትከሻቸው ድረስ ከፍ በማድረግ ተክቢር (አሏሁ አክበር) ይላሉ።

በመቀጠል ኢማሙ ሱረቱል ፋቲሃ እና ሱረቱል አዕላ… (ምዕራፍ 87) ያነባል።

በሁለተኛው ረከአ ከመጀመሪያው ረከአ ሲነሳ የሚለው ተክቢራ ጨምሮ ስድስት ጊዜ ተክቢር ይላል። ከዛም ሱረቱል ፋቲሃን እና ሱረቱል አል-ጋሽያ (ምዕራፍ 88) ያነባል።

ከእሱ ጀርባ ያሉ ተከታዮችም በእያንዳንዱ ተክቢራ እጆቻቸውን እስከ ታችኛው የጆሯቸው ጫፍ ወይም እስከ ትከሻቸው ከፍ በማድረግ ተክቢር ይላሉ።

ስግደቱ እንደተጠናቀቀም ኢማሙ የኢድ ትምህርት ወይም ኹጥባ ይሰጣሉ። በሁለቱ ክፍሎች መካከል በጣም ለአጭር ሰአት ያህል ይቀመጣሉ።

ትምህርቱ እንዳለቀም ሁሉም ወደየመጣበት ይመለሳል። የኢድ ሶላት ያለፈው ወይም ያመለጠው ሰው አራት ረከአ መስገድ ይጠበቅበታል።

0%
1
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ፆም

ጥያቄና መልስ፡ ኢድ

ኢድ የሚለው ትምህርት ፈተና 5 ጥያቄዎችን ይዟል፡፡ ፈተናውን ለማለፍ 4 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ፡፡

1 / 5

Bookmark question icon

1 ወደ ኢድ ቦታ እንዲሄዱ እስልምና ያዘዛቸው የትኞቹን ነው?

2 / 5

Bookmark question icon

2 የሙስሊሞች ያልሆኑ በአላትን ማክበር _______

3 / 5

Bookmark question icon

3 ከኢደል-ፊጥር እና ከኢደል አዱሃ ጋር ሌላን ቀን ኢድ አድርጎ መያዝ

4 / 5

Bookmark question icon

4 የዒድ ሶላት (ስግደት) ወቅቱ ወይም ጊዜው የትኛው ነው?

5 / 5

Bookmark question icon

5 በኢድ ሶላት ተክቢራ ማብዛት ተደንግጓል፡፡ ከማንበቡ በፊት ከእያንዳንዱ ረከአ መጀመሪያ የመግቢያ ተክቢራ ሳይጨምር ስንት ጊዜ ተክቢር (አሏሁ አክበር) ይላል

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 36%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

ኢድ

ተክቢር ፣ አዛን ፣ ኢቃም ፣ የገላ ትጥበት ፣ ነብዩ ኢብራሂም እና መዲና ከተማ

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share