Table of Contents

ነብዩ ኢብራሂም (   ) ከሚስታቸው ሐጀር የወለዱት የበኩር ልጃቸው ነብዩ ኢስማኤል (  )  ነው። አሏህ (  ) ስለ እሱ እንዲህ ይላል፡ በመጽሐፍ ውስጥ እስማኤልን አውሳ፤ በእርግጥ እሱ በቃልኪዳኑ እውነተኛ ነው። መልዕክተኛም ነብይም ነበር። ቤተሰቦቹን በሶላትና በዘካ ያዘ ነበር። ከጌታውም ዘንድ ተወዳጅ ነበር። (አል-ቁርአን 19፡54-55)

ነብዩ ኢብራሂም (  ) ከሐጀር እና ከልጃቸው ኢስማኤል ጋር ምግብ ፣ ፍራፍሬ ፣ ዛፍ እና ውሃ ወደሌለበት ያልታረሰ ጠፍ ወደሆነው ሸለቆ ተሰደዱ። ይህ ቦታ አሁን ላይ መካ ተብሎ ይጠራል።

እዚህ ቦታ ላይ ነብዩ ኢብራሂም ትንሽየ ምግብና ውሃ ሰጥቷቸው ትቷቸው ሄደ። ባሏ ይሄን በፈቃዱ እንዳላደረገ እና ይህን አሏህ እንዲያደርግ አዞት እንደሆነ በመረዳት አሏህ አይተወንም አለች።

አሏህ እሷን እና ልጇን እንደማይተዋቸው እርግጠኛ ነበረች። አሏህም ቅር አላሰኛቸውም። ከመሬት ውሃ እንዲፈልቅላቸው አደረገ። ይህ ውሃ የዘምዘም ውሃ ተብሎ ይጠራል።

ከጅርሁም ጎሳ የሆኑ ሰዎች በእነሱ በኩል እስካለፉበት ጊዜ ድረስ እዚሁ ቦታ ላይ ኖሩ። የውሃ ምንጭ ባገኙ ጊዜ ከእሷና ከልጇ ጋር አብረው መቆየት ይችሉ እንደሁ ጠየቋት። እሷም ተስማማች። ኢስማኤል ( ) አድጎ ለአቅማዳም በደረሰ ጊዜ ከእነሱ መካከል የሆነች ሴት አገባ።

ነብዩ ኢብራሂም (  ) መስዋዕት እንዲያደርግ አሏህ ያዘዘው እስማኤልን ነበር። ነብዩ ኢብራሂም (  ) በህልሙ ኢስማኤልን መስዋዕት ሲያደርገው እንዳየ ለልጁ ሲነግረው ኢስማኤል ( )

አባቴ ሆይ! እንደታዘዝከው አድርግ። አሏህ ከሻ(ከፈቀደ) ከታጋሾች ሆኜ ታገኘኛለህ አለ። (አል-ቁርአን 37፡102 )

ሁለታቸውም ለአሏህ ፈቃድ እራሳቸውን ሰጡ። ነብዩ ኢብራሂም (   ) ልጁን ሊያርድ በግንባሩ ደፍቶ ያዘ። ሞከረ አልቻለም፤ ሞከረ አልቻለም። አሏህ (  ) ራዕዩን እንደ ፈፀመ ነግሮት ትልቅ ወጠጤ በግ በምትኩ ሰጠው። ከእሱ ጊዜ በኋላ ለሚመጡ ትውልዶች ጥሩ ማስታወሻን ጥሎ አለፈ።

በካዕባ ግንባታ አባቱን ነብዩ ኢብራሂም (   ) የረዳው ነብዩ ኢስማኤል (   ) ነው። ይሄን ካደረጉ በኋላ ፀለዩ ጌታችን ሆይ! አገልግሎታችነን ተቀበለን። በእርግጥ ሁሉን ሰሚና ሁሉን አዋቂ አንተ ነህ። (አል-ቁርአን 2፡127)

ኢብራሂም ፣ ዘምዘም ተመልከቱ

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top