መካ በምዕራባዊ ሳውዲ አረቢያ፤ በቀይ ባህር ጠረፍ አቅራቢያ የምትገኝ ከተማ ናት። በካ ፣ ኡመል ቁራ (የከተሞች እናት) እና በለደል አሚን (ደህንነቷ የተጠበቀ ከተማ) ተብላም ትጠራለች።
መካ

መካ በምዕራባዊ ሳውዲ አረቢያ፤ በቀይ ባህር ጠረፍ አቅራቢያ የምትገኝ ከተማ ናት። ሌሎች መጠሪያ ስሞች አሏት። እነሱም በካ ፣ ኡመል ቁራ (የከተሞች እናት) እና በለደል አሚን (ደህንነቷ የተጠበቀ ከተማ) የሚሉት ናቸው።

መካ የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የትውልድ ቦታ ስትሆን በመካከሏ ካዕባን አቅፎ የያዘው መስጅደል ሐረም ይገኛል። በመላው አለም ላይ የሚገኙ ሙስሊሞች በቀን አምስት ጊዜ ወደ ካአባ አቅጣጫ ዞረው ይሰግዳሉ።

ጥንታዊ መካ

መካ ውስጥ የሚገኘው መስጅደል ሐረም ምድር ላይ በጣም ቅዱሱ መስጅድ ነው። በውስጡ የተሰገደች አንድ ሶላት ሌላ ቦታ ከተሰገደ አንድ መቶ ሽህ ሶላት በላይ በላጭ የሆነችበት ነው።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(አህመድ)

“(መዲና ውስጥ) በዚህ በእኔ መስጅድ ውስጥ የተሰገደች አንድ ሶላት (መካ ውስጥ) ከቅዱሱ መስጅድ ውጭ ሌላ ቦታ ከተሰገደ አንድ ሽህ ሶላት በላይ በላጭ ናት። በቅዱሱ መስጅድ ውስጥ የተሰገደች አንድ ሶላት ሌላ መስጅድ ውስጥ ከተሰገደ አንድ መቶ ሽህ ሶላቶች በላይ በላጭ ናት።”

የመካ ከተማ

የመካ ከተማ መጀመሪያ የተቆረቆረው ከሚስቱ ሐጀር እና ከልጁ እስማኤል ጋር በተሰደደው በነብዩ ኢብራሂም (ሰ.ዐ.ወ) እና በቤተሰቦቹ ነው። ይህ የተሰደዱበት ቦታ በአሁኑ አጠራር መካ ከተማ ተብሎ ይጠራል።

መካ በዚያን ጊዜ ባዶ ጠፍ በረሃ ነበረች። ህይወት ያለው ነገር እንኳ የሚኖርባት አትመስልም ነበር።

ከካዕባ ቀጥሎ የተባረከው ቅዱሱ የዘምዘም ምንጭ ውሃ ይገኛል። ይህ የምንጭ ውሃ ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) በዛ በረሃ ሐጀርን እና ልጇን ብቻቸውን ትቷቸው በሄደ ጊዜ አሏህ የሰጣቸው ምንጭ ነው።

የዘምዘም ውሃ በማያረጥር እና በማያሻማ ሁኔታ በምድራችን ብቸኛው ቅዱስ እና የተባረከ ውሃ ነው።

መካን አሏህ የተቀደሰ ቦታ አድርጎታል። ሆኖም አሾሆቿን ቢሆን እንኳ መንቀል ፣ ዛፎቿን መቁረጥ ፣ እንስሳዎቿን ማደን እና ማባረር ፣ ደም ማፍሰስ ፣ የወደቀን ነገር ማንሳት አይፈቀድም።

አሏህ ከሁሉም የሽርክ አይነቶች ጠብቋታል። ሙስሊም ያልሆኑ ሰዎችም ወደ እሷ እንዳይገቡ በጥብቅ ከልክሏል።

0%
7
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

የእስልምና ምሰሶች

ጥያቄና መልስ፡ የነብዩን ከተማ መጎብኘት

‹‹የነብዩን ከተማ መጎብኘት›› የሚለው ትምህርት ፈተና 6 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 5 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 6

Bookmark question icon

1 የነብዩ መስጅድ ውስጥ መስገድ ሽልማቱ_____ ነው፡፡

2 / 6

Bookmark question icon

2 ከእስልምና አንፃር ምድር ላይ ካሉ ቦታዎች ሁሉ በላጭ የሆኑትን በደረጃ አስቀምጡ፡፡

3 / 6

Bookmark question icon

3 መዲና ውስጥ በሚሆኑ ጊዜ መጎብኘት እና በውስጣቸው መስገድ የተወደደ የሆኑ መስጅዶች የትኞቹ ናቸው፡፡

4 / 6

Bookmark question icon

4 ከሚከተሉት መስጅዶች ውስጥ በአንዱ መስገድ ኡምራ ከማድረግ ጋር እኩል ሽልማት አለው፡፡ የትኛው መስጅድ ነው?

5 / 6

Bookmark question icon

5 መዲና ውስጥ የሚኖር አንድ ሙስሊም ሰው አሏህ ያዘዘው ነገር በተመለከተ ተጨማሪ ጥንቃቄ ማድረግ እና አሏህ እና መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) መታዘዝ አለበት፡፡

6 / 6

Bookmark question icon

6 በመዲና ውስጥ ዛፍ መቁረጥ እና እንስሳ ማደን ሁክሙ ምንድን ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 39%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

መስጅደል ሐረም ፣ ዘምዘም ፣ ኢብራሂም እና ኢስማኤል ተመልከቱ

Related posts

የዘምዘም ውሃ

የዘምዘም ውሃ

የዘምዘም የውሃ ጉድጓድ የሚገኘው ከካዕባ ቀጥሎ ነው። ውሃው ምድር ላይ ካለ ውሃ ሁሉ ቅዱስ እና ድንቅ ውሃ ነው። በምድር ላይ በላጩ ውሃ የዘምዘም ውሃ ነው።

Read More »
እስልምና በኢትዮጵያ፡

እስልምና በኢትዮጵያ፡ ከጥንታዊ ሥረ-መሠረቱ እስከ ዘመናዊ ስርጭቱ

ኢትዮጵያ ከዓለም ጥንታዊ ሥልጣኔዎች አንዷ ስትሆን በርካታ እምነቶች ያስተናገደች ምድርም ነች። ከእነዚህም መካከል እስልምና እና ክርስትና ይገኙበታል። እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ የራሱን ጉልህ አሻራ ያሳረፈ ሃይማኖት

Read More »
የቀናት አቆጣጠር

የእስልምና የቀናት አቆጣጠር

ከእስልምና በፊት አረቦች የራሳቸው የሆነ የቀናት አቆጣጠር አልነበራቸውም። ምንም እንኳ አስራ ሁለቱን የጨረቃ ወራቶች ቢያውቁም ጊዜን የሚያሰሉት አንድ ልዩ ክስተት ከፊቱ ወይም ከኋላው የተከሰተበትን ጊዜ

Read More »
መስጅደ ነበውይ

መስጅደ ነበውይ የነብዩ መስጅድ

ነብዩ ያኔ ያስሪብ ተብላ ወደምትጠራው የአሁኗ መዲና በተሰደዱ ጊዜ ጋልበዋት በነበረችው ግመል ዙሪያ ተከታዮቻቸው እና የከተማዋ ሹማምንት ምርጥ ልብሶቻቸውን እና የብረት መከላከያ ልብሶችን እንደለበሱ ተቀበሏቸው።

Read More »

Share