መስጅደል ሐረም መካ ውስጥ የሚገኝ ሐጀረል አስወድን (ጥቁሩ ድንጋይ) እና ካዕባን በውስጡ የያዘ ቅዱስ መስጅድ ነው።
መስጅደል ሐረም
መስጅደል ሐረም

መስጅደል ሐረም መካ ውስጥ የሚገኝ ሐጀረል አስወድን (ጥቁሩ ድንጋይ) እና ካዕባን በውስጡ የያዘ ቅዱስ መስጅድ ነው። መጀመሪያ በጣም ትንሽ የነበረ ሲሆን በግንብ (በግድግዳ) የተከበበ አልነበረም።

መስጅዱን የማተለቅ ስራ መጀመሪያ የተሰራው በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሲሆን ከዛ ደግሞ በኸሊፋው አቡበክር አሲዲቅ ፣ ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ ፣ ኡስማን ኢብኑ አፋን ፣ አብዱሏህ ኢብን አዙበይር ፣ አቡጃዕፈር አልመንሱር እና ሌሎችም ነው።

በቅርቡ ዘምኖ ትልቅ ተጨማሪ ግንባታ የተደረገለት በ1375ዓ.ሂ በንጉስ ፋሐድ ቢን አብዱል አዚዝ ነው።

የመጀመሪያው የአምልኮ ቤት

መስጅደል ሐረም በምድር ላይ የሰው ልጆች ጌታቸውን ያመልኩ ዘንድ የቆመ የመጀመሪያው የአምልኮ ቤት ነው። አሏህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ኢምራን 3፡96)

“በእርግጥ ለሰው ልጆች የተኖረ የመጀመሪያው የአምልኮ ቤት ነው፤ በበካ (በመካ) ውስጥ ነው፤ የተባረከና ለሙዕሚኖች መመሪያ ነው።”

በካ ሌላኛው የመካ ከተማ መጠሪያ ነው። ወደ እሷ የሚገበ ሰው ገዳይ ቢሆን እንኳ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ኢምራን 3፡97)

“ወደ እሷ የገባ ሰው ደህንነቱ (መጠበቅን) አግኝቷል።” (አል-ቁርአን 3፡97)

ይሁን እንጅ በኑህ (ዐ.ሰ) ዘመን ከባድ ጎርፍ ምድርን ባናወጣት ጊዜ ትልቁ ምልክቱ ሙሉ በሙሉ ጠፍቶ ነበር። በኑህ (ዐ.ሰ) ዘመን በጎርፍ የጠፋውን መሰረት ነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) እና ልጃቸው ኢስማኤል (ዐ.ሰ) ከፍ እንዲያደርጉ ካዕባን መልሰው እንዲገነቡ አሏህ አዘዛቸው።

በእርግጥ ወሰረቱ ወደ ጠፋው (ቤት) ቦታ የመራቸው መልአኩ ጅብሪል (ዐ.ሰ) ነው። ገንብተው እንደጨረሱም ሃያሉ አሏህ ስራቸውን እንዲቀበላቸው ፣ እነሱ እና ተወላጆቻቸው ለአሏህ ተገዥ እንዲሆኑ ፣ የሐጅና የኡምራ ስርአት እንዲያሳያቸው ፣ ተውባቸውን እንዲቀበላቸው ፣ ምልክቶቹን የሚያነብላቸው ከራሳቸው መካከል የሆነ መልዕክተኛ እንዲልክላቸው መጽሐፉን እና ጥበቡን የሚያስተምራቸው ከክህደት የሚያጠራቸው መልዕክተኛ እንዲልክላቸው ለመኑ።

አሏህ ፀሎታቸውን ተቀብሎ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ላካቸው። አልቁርአን 2፡127-129

የተቀደሰው መስጅድ ንፁህ እና ከሁሉም የሽርክ አይነቶች የፀዳ ነበር። ነገርግን ጊዜ በገፋ ቁጥር ሰዎች ጣኦቶችን ማምለክ ጀመሩ። ወደ ወደ መካ የጣኦት አምልኮ አመጡ። ሰዎች በካዕባ ውስጥ እና በዙሪያው ጣኦታትን አቆሙ።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መካ በድል እስከተመለሱበት እና እስካስወገዷቸው ጊዜ ድረስ ነበሩ። በእጃቸው በነበረ በትር አውልቀው ጣሏቸው፤ ይህንን አያ(አንቀፅ) አነበቡ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ኢስራዕ 17፡81)

“በል! እውነት መጣ ውሸትም ተወገደ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና።”

ከመስጅደል ሐረም ጋር የተያያዘው አንደኛው ክስተት የየመን ገዥ አብርሃ የየመን ዋና ከተማ ሰንአ ውስጥ ቤተመቅደስ ገንብቶ አረቦች ከመካ ይልቅ እሱ ወደ ገነባው ቤተመቅደስ ሐጅ እንዲያደርጉ ለማድረግ የሞከተረበት አመል ፊል (የዝሆኑ አመት) ክስተት ነው። አሏህም እሱን እና ወታደሮቹን ሙሉ በሙሉ አጠፋቸው።

መስጅደል ሐረም በምድር ላይ እጅግ ቅዱሱ መስጅድ ነው። ብዙ ትሩፋቶችም አሉት። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(አህመድ)

“በእኔ በዚህ መስጅድ የተሰገደ አንድ ሶላት ሌላ ቦታ ከተሰገደ ከሽህ ሶላቶች በላይ በላጭ ነው። ቅዱሱ መስጅድ (መካ) ውስጥ ካልሆነ በቀር። ቅዱሱ መስጅድ ውስጥ የተሰገደ አንድ ሶላት ሌላ መስጅድ ውስጥ ከሚሰገድ አንድ መቶ ሸህ ሶላቶች በላይ በላጭ ነው።”

መስጅድ
0%
6
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ሐጅ

ጥያቄና መልስ፡ የመካ አል-ሙከረማ እና የመስጅደል ሀረም ትሩፋቶች

‹‹የመካ አል-ሙከረማ እና የመስጅደል ሀረም ትሩፋቶች››የሚለው ትምህርት ፈተና 5 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 4 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 5

Bookmark question icon

1 አሏህ ዘንድ እና መልዕክተኛው ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ዘንድ ተወዳጅ የሆነው ሐገር የትኛው ነው?

2 / 5

Bookmark question icon

2 ካዕባን መጀመሪያ የገነባው ማነው?

3 / 5

Bookmark question icon

3 መካ የሚገኘው የት ውስጥ ነው?

4 / 5

Bookmark question icon

4 መስጅደል ሐረም እና በመስጅደል አቅሷ ግንባታ መካከል ያለው ወቅት

5 / 5

Bookmark question icon

5 ምድር ላይ አሏህን ለማምለክ የተሰራ የመጀመሪያው መስጅድ የትኛው ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 40%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

መስጅድ ፣ አመል ፊል የዝሆኑ አመት ፣ መስጅደ ነበውይ ፣ በይተል መቅዲስ እና መካ ተመልከቱ

Related posts

የዘምዘም ውሃ

የዘምዘም ውሃ

የዘምዘም የውሃ ጉድጓድ የሚገኘው ከካዕባ ቀጥሎ ነው። ውሃው ምድር ላይ ካለ ውሃ ሁሉ ቅዱስ እና ድንቅ ውሃ ነው። በምድር ላይ በላጩ ውሃ የዘምዘም ውሃ ነው።

Read More »
እስልምና በኢትዮጵያ፡

እስልምና በኢትዮጵያ፡ ከጥንታዊ ሥረ-መሠረቱ እስከ ዘመናዊ ስርጭቱ

ኢትዮጵያ ከዓለም ጥንታዊ ሥልጣኔዎች አንዷ ስትሆን በርካታ እምነቶች ያስተናገደች ምድርም ነች። ከእነዚህም መካከል እስልምና እና ክርስትና ይገኙበታል። እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ የራሱን ጉልህ አሻራ ያሳረፈ ሃይማኖት

Read More »
የቀናት አቆጣጠር

የእስልምና የቀናት አቆጣጠር

ከእስልምና በፊት አረቦች የራሳቸው የሆነ የቀናት አቆጣጠር አልነበራቸውም። ምንም እንኳ አስራ ሁለቱን የጨረቃ ወራቶች ቢያውቁም ጊዜን የሚያሰሉት አንድ ልዩ ክስተት ከፊቱ ወይም ከኋላው የተከሰተበትን ጊዜ

Read More »
መስጅደ ነበውይ

መስጅደ ነበውይ የነብዩ መስጅድ

ነብዩ ያኔ ያስሪብ ተብላ ወደምትጠራው የአሁኗ መዲና በተሰደዱ ጊዜ ጋልበዋት በነበረችው ግመል ዙሪያ ተከታዮቻቸው እና የከተማዋ ሹማምንት ምርጥ ልብሶቻቸውን እና የብረት መከላከያ ልብሶችን እንደለበሱ ተቀበሏቸው።

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share