የዝሆኑ አመት ወይም አመል ፊል ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተወለዱበት አመት ነው።
ከእስልምና በፊት አረቦች የራሳቸው የሆነ የቀን አቆጣጠር አልነበራቸውም። በመሆኑም ለአመት ስም የሚሰጡት በጊዜው የተፈፀመን ክስተት በመንተራስ ነው።
ሆኖም ነብዩ ሙሐመድ የተወለዱበት አመት የዝሆን አመት ተብሎ ይጠራል። የዝሆኑ አመት (ህዳር 30 571 ዓ.ሂ) አብርሃ ከሰንአ ወደ ሙጋማስ ያደረገው ዘመቻ
ምክኒያቱም አብርሃ አል-አሽረም የተባለ የአቢሲንያ ግዛት የየመን ክርስቲያን አስተዳዳሪ ከአባን ለማጥፋትና በእሱ ፈንታ የመን ውስጥ የሰራውን ቤተ መቅደስ እንዲሳለሙ ለማድረግ አስቦ ትልልቅ ዝሆኖችን እና ወታደሮችን ይዞ ወደ መካ ጉዞ ያደረገበት አመት ነው።
የአብርሃም ወታደር በጣም ጠንካራ ስለነበር የካዕባ ጠባቂዎች ለመከላከል አልቻሉም፤ አልሞከሩም።
ይሁእንጅ የአብርሐምን መጥፎ እቅድ በከንቱ እንዲያበቃ በማድረግ አሏህ የተቀደሰ ቤቱን ጠበቀው። አሏህም በአፋቸው እና በጥፍራቸው ድንጋይ የያዙ ወታደር ወፎችን ላከበት።
ሆኖም ሁሉም እስኪጠፉ ድረስ ወረወሩባቸው። ቁርአን ስለ ዝሆኑ ታሪክ በሱረቱ አልፊል ውስጥ ይናገራል።
አል-ቁርአን
አል-ቁርአን 105:1-5
“በዝሆኑ ባለቤቶች ጌታህ ምን እንደሰራ አላየህምን በእሱም ላይ መንጎች የሆኑ ወፎች ላከ። ከተጠበሰ ጭቃ በሆነ ድንጋይ የምትወረውርባቸው የሆነችን አዕዋፍ ቅጠሉ እንደ ተበላ አዝመራ አደረጋችሁ።”
የአብርሐም ወታደሮች በድንገት በወፎች መንጋ ተቀደሙ። ከምስር ፍሬ ከፍ ባሉ ትንሽየ ድንጋዮች ተመቱ። እነዚህ ድንጋዮች በወታደሮቹ ላይ በወደቀ ጊዜ ስጋቸው ይፈራርስ ነበር።
ሁሉም የሞቱት በዚህ መልኩ ነው። አብርሃ የሸሸው ስጋው እየተቆራረጠ እያለ ነው። ነገርግን የሞተው ወደ የመን እየተመለሰ በላበት ጊዜ ነው።



