መስጅድ (ብቁ. መሳጅድ) ማለት የእስልምና የአምልኮ ቦታ ሲሆን የሙስሊሙ ማህበረሰብ ሙሉ ህይወት የሚያጠነጥነው በዚሁ ዙሪያ ነው።
መስጅድ ካለው ጥቅም አኳያ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ወደ መዲና ከተማ መሰደዳቸውን ተከትሎ ከሰሯቸው ተግባራት የመጀመሪያው መስጊድ መገንባት ነበር።


በመጀመሪያ ደረጃ መስጅዶች
አል-ቁርአን
(ሱረቱ ኑር 24፡36)
አሏህ እንድትቆም እና (እንድትከበር) ስሙ በውስጧ እንዲወሳ ባዘዘው ቤቶች ውስጥ አወድሱት።
በእርግጥ መስጅድ ከአሏህ ዘንድ ተወዳጅ ቦታ ነው። ምክኒያቱም በእስልምና ልዩ ቦታና ደረጃ አለውና።
ለአሏህ ሲሉ እነሱን ለሚገነቡ አሏህ ድንቅ ሽልማትን ይሸልማቸዋል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
”የአሏህን ውዴታ ለማግኘት ሲል ብቻ መስጊድ የገነባ ሰው፤ አሏህጀነት ውስጥ ቤት ይገነባለታል።”
መስጊድ ሁልጊዜም ንፁህ እና ፅዱ መሆን አለበት። ሙስሊሞች መስጅዳቸውን ማክበር ፣ መጠበቅም እና መንከባከብም አለባቸው።
ደስ የማይል ሽታዎችን እና ቅድስናውን የሚጥሱ ወይም ኢባዳ ላይ ያሉትን የሚረብሹ ልጆችን ይዘው መምጣ አይገባም።
በእነሱ ውስጥ ድምፅን ከፍ አድርጎ መጮህ ፣ በአለማዊ ጉዳይ መወያት ወይም ግብይት መፈፀም አይፈቀድም። አምስቱን ሶላቶች መስጅድ ውስጥ መስገድ ትልቅ ምንዳ ያስገኛል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
”መስጅዱን ጧትም ማታም አዘውትረው ለሚጎበኙ ሰዎች አሏህ እንግዳ ተቀባይዮችን አዘጋጅቷል።
እንዲህም ብለዋል፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
”ልቡ ከመስጅድ ጋር የተንጠለጠለች ሰው ከመለኮታዊ ዙፋን (ከአርሽ) ጥላ ስር ቦታ ይኖረዋል።
መስጅዶች በሙዕሚኖች ላይ ያላቸው ሐቅ (መብት)
መስጅድ የአሏህ (ሱ.ወ.ተ) ቤት ሲሆን ልክ እንደማንኛውም ነገር የራሱ መብት አለው። ከነዚህ መብቶች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፦
➊ኛ መስጅድ በገባን ጊዜ ከመቀመጣችን በፊት ሁለት ረከአ ልንሰግድበት
ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በሐዲሳቸው እንዲህ ብለዋል፦ አንዳችሁ መስጅድ በገባ ጊዜ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከአ ይስገድ ብለዋል።
➋ኛ ቁጭብለን ቁርአን ልንቀራበት
በሙስሊም እንደተዘገበው የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ); ከአሏህ ቤት የአሏህን መፅሐፍ ለመቅራት እና በአንድ ላይ ሊያጠኑት የሚሰባሰቡ ሰዎች የሉም የምንፈስ እርጋታና ምህረት አካቧቸው ፣ መላኢካዎች ከበዋቸው እና አሏህ ከነሱ ጋር ሆኖ ቢሆን እንጅ ብለዋል።
➌ኛ ምንም አይነት ንግድ ወይም ግብይት ላናካሂድበት
የአሏህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ); መስጅድ ውስጥ የሸጠ ሰው አሏህ በሽያጫችሁ(በንግዳችሁ) ስኬትን አይስጣችሁ በሏቸው ብለዋል።
➍ኛ የመስጅዱን ፅዳት መጠበቅ እና ጥሩ መአዛ እንዲኖረው ማድረግ
➎ኛ በውስጡ ቁጭ ብለን በዲናችን ዙርያ ለሙስሊም እህት ወንድሞቻችን ምክር መስጠት ወይም እርስበርስ መመካከር
➏ኛ መስጅድ በምንቆይባቸው ጊዜያቶች ውስጥ አሏህን ብዙ ልናወሳበት(ልናስታውስበት)
ሶላት እና መዲና ተመልከቱ





Share