ሲዋክ እና ጥቅሞቹ

Author picture
ኢስላም ንፅህናን የእምነቱ ግማሽ አካል ያደረገ ብቸኛ መለኮታዊ ሃይማኖት ነው። ሲዋክ ማለት ጥርስንና አፍን በእንጨት መፋቂያና መሰል ነገራት ከመጥፎ ጠረንና ቅሪቶች ማጽዳት ማለት ነው፡፡
ሲዋክ እና ጥቅሞቹ

ኢስላም ንፅህናን የእምነቱ ግማሽ አካል ያደረገ ብቸኛ መለኮታዊ ሃይማኖት ነው። ሲዋክ ማለት ጥርስንና አፍን በእንጨት መፋቂያና መሰል ነገራት ከመጥፎ ጠረንና ቅሪቶች ማጽዳት ማለት ነው፡፡

ጥርስንና አፍን በማጽዳት ኒይያ እስከሆነ ድረስ በኮልጌት እና በመሰል ነገራትም መጠቀሙ አጅሩን ያስገኛል፡፡ ቁም-ነገሩ ንጽህናው ላይ እንጂ ማጽጂያው ላይ አይደለምና (አል-ኢስላሙ ሱኣሉን ወጀዋብ ቁ. 219510 )፡፡

3/ ሲዋክን መጠቀም፡- የአፍን ጽዳት ብቻ ሳይሆን የአላህንም ውዴታ ያስገኛል፡፡ የምእመናን እናት ከኾነችው እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንደተነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ አለች፡-

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሱነኑ-ነሳኢይ 5)

‹‹ሲዋክን መጠቀም የአፍን ንጽህና እና የአላህን ውዴታ ያስገኛል››

4/ ሲዋክን በማንኛውም ሰዓት፡ በቀንም ኾነ በለሊት፣ በፆም ወቅትም ኾነ ከፆም ውጭ፣ ከሰአት በፊትም ኾነ በኋላ መገልገል ታላቅ ምንዳ ያለው የጠበቀ ሱንና ተግባር ነው፡፡

አለመጠቀሙ የሚያስጠይቅ የኾነ ዋጂብ አይደለም፡፡ ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪና ሙስሊም)፡

‹‹በኡመቶቼ ላይ ይጠናባቸዋል (አስቸግራቸዋለሁ) ባልል ኖሮ በየሶላቱ መቃረቢያ ሲዋክን እንዲጠቀሙ ባዘዝኋቸው ነበር››

ሲዋክ መጠቀም የሚወደድባቸው ሁኔታዎችና ጊዜያት

ከእንቅልፍ ሲነቁ

ሑዘይፈተ ኢብኑል-የማን (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ አለ፡-

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪና ሙስሊም)

‹‹የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ከእንቅልፋቸው ነቅተው ሲነሱ፡ አፋቸውን በሲዋክ ወደ ጎን ይፈትጉት ነበር››

የአፍ ጠረን ሲቀየር

እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንደተነገረችን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ አለች፡-

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሱነኑ-ነሳኢይ 5)

‹‹ሲዋክ መጠቀም የአፍን ንጽህና እና የአላህን ውዴታ ያስገኛል››

በዉዱእ ወቅት

ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡-

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(አሕመድ የዘገበው)

‹‹በኡመቶቼ ላይ ይጠናባቸዋል (አስቸግራቸዋለሁ) ባልል ኖሮ በየዉዱኡ ሰዓት ሲዋክ እንዲጠቀሙ ባዘዝኋቸው ነበር››

ሶላት ሊጀመር ሲል

ከአቢ ሁረይራህ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንደተነገረን የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- ‹‹በኡመቶቼ ላይ ይጠናባቸዋል (አስቸግራቸዋለሁ) ባልል ኖሮ በየሶላቱ መቃረቢያ ሲዋክን እንዲጠቀሙ ባዘዝኋቸው ነበር›› (ቡኻሪና ሙስሊም)፡፡

ቅዱስ ቁርአን ለመቅራት ስንዘጋጅ

አሊ ኢብን አቢ ጧሊብ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዳስተላልፍው የአላህ መልክተኛ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ አሉ፡- ‹‹የአላህ ባሪያ መፋቂያን ተጠቅሞ ከዚያም ቆሞ መስገድ ሲጀምር፡ መልአኩ ከኋላው በመኾን ወደሱ ጠጋ ብሎ ቂርኣቱን ያዳምጣል›› (ሶሒሑ-ተርጊብ ወት-ተርሂብ 215)፡፡

ወደቤት ሲገቡ

እናታችን ዓኢሻህ (ረዲየላሁ ዐንሃ) እንዲህ ነገረችን፡-

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም የዘገበው)

‹‹የአላህ ነቢይ (ዐለይሂ-ሶላቱ ወስ-ሰላም) ወደቤታቸው ሲገቡ ሲዋክ በመጠቀም ይጀምሩ ነበር››

በየትኛው እጃችን እንጠቀም?

ሲዋክ መጠቀም የሚፈልግ ሙስሊም፡ በተመቸው ኹኔታ በቀኝ እጁም ኾነ በግራው መገልገል ይችላል፡፡ ከፊል የኢስላም ሊቃውንት በግራው ይጠቀም ይላሉ (ይህ የሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ ረሒመሁላህ ምርጫ ነው)፡፡

ሌሎቹ ደግሞ በቀኙ ይገልገል፡፡ ምክንያቱም ሲዋክን መጠቀም ሱንና ተግባር ነው፡፡ መልካም ተግባርን ደግሞ በቀኝ ነው መገልገል ያለብን ይላሉ፡፡

ሸይኽ ሙሐመድ ቢን ሷሊሕ አል-ዑሠይሚን (ረሒመሁላህ) ደግሞ፡- ጉዳዩ በሁሉም ለመገልገል ይመቻል፡፡ ምክንያቱም በየትኛው እጅ መገልገል እንዳለብን የሚጠቁም ግልጽ ሐዲሥ አልመጣምና በፈለግነውና ባመቸን መጠቀም እንችላለን ይላሉ፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡

ሲዋክ ከዚህ ውጭ የኾኑ ሌሎች ከጤና ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጥቅሞች አሉትና ከመጠቀም አንቦዝን፡፡ አላህ ይወፍቀን፡፡

‹‹ንፅህና የኢማን አንድ ክፍል ነው!…›› ረሱል (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ‹ሙስሊም የዘገበው›፡፡

Related posts

ሱጁድ

ሱጁድ

ሱጁድ ማለት በሶላት ውስጥ የመስገጃ ቦታ ላይ ግንባርን የመድፋት ተግባር ነው። ይህ የሚፈፀመው ግንባርን እና አፍንጫን ወለሉ ላይ በማስነካት ፣ መዳፎችን ወለሉ ላይ በማሳረፍ ፣

Read More »
ኢቃም

ኢቃም

ኢቃማ ከፈርድ (ግዴታ) የጀመአ ሶላት መጀመሪያ ላይ የሚባል መነባነብ ነው። አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረ.ዐ) “የአዛን ቃላት ሁለት ጊዜ እና የኢቃም ቃላትን በተናጠል አንድ ጊዜ ብቻ

Read More »
ረከአ

ረከአ

እያንዳንዱ ሶላት የአንድ ወይም የሁለት ፣ የሶስት ወይም የአራት ረከአ ህብር ነው። እያንዳንዱ ረከአ አቋቋሞች ወይም ቅርፆች አሉት፤ መጀመሪያ መቆም ፣ ከዛም መዳፎችን ጉልበት ላይ

Read More »
ሩኩዕ

ሩኩዕ

ሩኩዕ ማለት በሶላት ውስጥ የማጎንበስ ተግባር ነው። ጉልቢን እንደሚይዙ ጣቶችን ዘርዘር አድርጎ መዳፉን ጉልበት ላይ በማስቀመጥ ማጎንበስ ነው። ክርኖች ከፊት እና ከጎን በኩል ራቅ ማለት

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share