ኢቃም ከፈርድ (ግዴታ) የጀመአ ሶላት መጀመሪያ ላይ የሚባል መነባነብ ነው። አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረ.ዐ) “የአዛን ቃላት ሁለት ጊዜ እና የኢቃም ቃላትን በተናጠል አንድ ጊዜ ብቻ እንዲል ቢላል ታዟል” ብሏል። (ቡኻሪ)

የፈርድ ሶላት ብቻውን የሚሰግድ ሰው ሶላት ከመጀመሩ በፊት ኢቃም ይላል።
የኢቃም ቃላቶች የሚከተሉት ናቸው።
አሏሁ አክበር (አሏህ ሃያል ነው፤ ሁለት ጊዜ)
አሽሃዱ አላ ኢላሃ ኢለሏህ
(ከአሏህ ውጭ አምልክ አለመኖሩን እመሰክራለሁ፤ አንድ ጊዜ)
አሽሃዱ አነሙሐመደን ረሱሉሏህ
(ሙሐመድ የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ አንድ ጊዜ)
ሃያአለል ሶላ (ወደ ሶላት ኑ)
ሃያ አለል ፈላህ (ወወደ ስኬት ኑ)
ቀድ ቃመቲ ሶላህ (ስግደቱ ሊጀመር ነው፤ ሁለት ጊዜ)
አሏሁ አክበር (አሏህ ሃያል ነው፡ ሁለት ጊዜ)
ላኢላሃ ኢለሏህ (ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም፡ አንድ ጊዜ)
በአዛን እና ኢቃም መካከል የሱና ሶላት መስገድ ይወደዳል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
“በአዛን እና ኢቃም በካከል ሶላት አለ። በአዛን እና በኢቃም መካከል ሶላት አለ። ይህንኑ ለሶስተኛ ጊዜ ካሉ በኋላ ‹መስገድ ለፈለገ ሰው› ሲሉ ጨመሩ።”




Share