አዛን ፈርድ (የግዴታ) ሶላቶች መጥሪያ ነው። በመጀመሪያ ሙስሊሞች ያለ አዛን መስጊድ ውስጥ ይገኙ ነበር። አብዱሏህ ኢብኑ ዘይድ በህልሙ የአዛን አደራረግ እንደተማረ ሊነግራቸው መጣ።
አዛን

አዛን ፈርድ (የግዴታ) ሶላቶች መጥሪያ ነው። በመጀመሪያ ሙስሊሞች ያለ አዛን መስጊድ ውስጥ ይገኙ ነበር።

እናም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶሃቦቻቸውን አማከሩ፤ አንዳንዶቹ የይሁዳዎች ጡሩንባ ለመጠቀም ሃሳብ አቀረቡ፤ ሌሎቹ ደግሞ የክርስቲያኖች ቃጭል /ደወል/ ላይ ሃሳብ አቀረቡ።

ነገርግን አንዱም ለእሱ የሚያስደስት አልነበረም። ጉዳዩ እየተወያዩበት እያለ አብዱሏህ ኢብኑ ዘይድ በህልሙ የአዛን አደራረግ እንደተማረ ሊነግራቸው መጣ። ለቢላል እንዲያስተምረው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)  ጠየቁት።

አዛን አድራጊ

ቢላል ቢን ረባህ በኢስላም የመጀመሪያው ሙአዚን (አዛን አድራጊ) ነው። ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ ለሶላት ጥሪ ሲያደርግ በሰሙት ጊዜ ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሄደና አብዱሏህ ኢብኑ ዘይድ እንዳየው ያለ ህልም እሱም ተመሳሳይ ህልም እንዳየ ነገራቸው።

የአዛን ቃላቶች

አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር

አዛን አደራረግ

አሏህ ሃያል ነው! አሏህ ሃያል ነው! (አራት ጊዜ)

አሽሃዱ አላኢላሃ ኢለሏህ

ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ አለመኖሩን እመሰክራለሁ! (ሁለት ጊዜ)

አሽሃዱ አነሙሐመደን ረሱሊሏህ

ሙሐመድ የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን እመሰክራለሁ (ሁለት ጊዜ)

ሀያአለ ሶላ

ወደ ሶላት ኑ (ሁለት ጊዜ)

ሃያ አለፈላህ

ወደ ስኬት ኑ (ሁለት ጊዜ)

አሏሁ አክበር አሏሁ አክበር (ሁለት ጊዜ)

አሏህ ሃያል ነው! አሏህ ሃያል ነው!

ላኢላሃ ኢለሏህ (1ጊዜ)

ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ አለመኖሩን እመሰክራለሁ!

ለንጋት (ለፈጅር) ሶላት ጥሪ ሲደረግ “አሶላቱ ኸይሩን ሚነነውም (ሶላት ከእንቅልፍ ይበልጣል) የሚለው አባባል ሁለት ጊዜ ሃያ አለል ፈላህ ከሚለው አረፍተነገር ቡኋላ  ይባላል።

አዛን በታወጀ ጊዜ ሸይጧን ላለመስማት ይሸሻል። ሙስሊሞች አዛን ሲሰሙ ለእያንዳንዱ ጥሪ መመለስ እና ከሙአዚኑ በኋላ እሱን ተከትለው ደግመው ማለት ይገባቸዋል።

ሙአዚኑ ሃያ አለሶላ (ወደ ሶላት ኑ) እና ሃያ አለል ፈላህ (ወደ ስኬት ኑ) ሌሎች ሰዎች ላሃውለውላ ቅወተ ኢላ ቢላህ (ሃይልም ብልሃትም የለም ከአሏህ ቢሆን እንጅ) ይላሉ።

አዛኑን የሰማ ማንኛውም ሰው ወይም ጅን በፍርዱ ቀን ለሙአዚኑ ይመሰክሩለታል።

የአዛን ጥሪ የሚያደርግ ሰው ሙአዚን ተብሎ ይጠራል። ከአዛን ቡኋላ የሚከተለውን በሉ

አሏሁመ ረበ ሃዚሂ ዳዕወቲ ታማ ወሶላቲል ቃኢማ አቲ ሙሐመደን አልወሲላ ወል  ፈዲላ ወበአስሁ መቃመን ማህሙደኒለዚ ወአደተሁ ኢነከ ላቱህሊፉል ሚአድ።

ትርጉም፡ አሏህ ሆይ! የዚች ምሉዕ ጥሪና የዚች ለመስገድ የቀረበች ሶላት አምላክ ነህ። ለሙሐመድ ወሲላ እና ፈዲላ የተባሉ ገነቶችን ለግሳቸው። ቃል የገባህላቸውን የተመሰገነ ደረጃም አጎናፅፈህ ከሞት ቀስቅሳቸው። አንተ ቃልህን የምታጥፍ አይደለህምና። (ቡኻሪ)

ለበለጠ መረጃ ኢቃም እና ሸይጧን የሚሉ አርዕስቶችን ተመልከት

0%
18
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ሶላት

ጥያቄና መልስ: አዛን

‹‹አዛን››የሚለው ትምህርት ፈተና 6 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 5 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 4

Bookmark question icon

1 ከአዛን (ከሶላት ጥሪ) ጀርባ ያለው ጥበብ ምንድን ነው?

2 / 4

Bookmark question icon

2 የአዛን ጥሪ የሚያደርገው ተጣሪ (ሙአዚን) የፈጅር ሶላት ላይ የሚጨምረው የትኛውን ነው?

3 / 4

Bookmark question icon

3 የጀመአ ሶላት አዛን እና ኢቃምን ሆን ብሎ (አውቆ) መተው ሁክሙ ምንድን ነው?

4 / 4

Bookmark question icon

4 የሶላት ተጣሪው (ሙአዚኑ) በሚጣራ ጊዜ እሱ የሚለውን ደግሞ ማለት ሁክሙ ምንድን ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 51%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

ሲዋክ እና ጥቅሞቹ

ሲዋክ እና ጥቅሞቹ

ኢስላም ንፅህናን የእምነቱ ግማሽ አካል ያደረገ ብቸኛ መለኮታዊ ሃይማኖት ነው። ሲዋክ ማለት ጥርስንና አፍን በእንጨት መፋቂያና መሰል ነገራት ከመጥፎ ጠረንና ቅሪቶች ማጽዳት ማለት ነው፡፡

Read More »
ሱጁድ

ሱጁድ

ሱጁድ ማለት በሶላት ውስጥ የመስገጃ ቦታ ላይ ግንባርን የመድፋት ተግባር ነው። ይህ የሚፈፀመው ግንባርን እና አፍንጫን ወለሉ ላይ በማስነካት ፣ መዳፎችን ወለሉ ላይ በማሳረፍ ፣

Read More »
ኢቃም

ኢቃም

ኢቃማ ከፈርድ (ግዴታ) የጀመአ ሶላት መጀመሪያ ላይ የሚባል መነባነብ ነው። አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረ.ዐ) “የአዛን ቃላት ሁለት ጊዜ እና የኢቃም ቃላትን በተናጠል አንድ ጊዜ ብቻ

Read More »
ረከአ

ረከአ

እያንዳንዱ ሶላት የአንድ ወይም የሁለት ፣ የሶስት ወይም የአራት ረከአ ህብር ነው። እያንዳንዱ ረከአ አቋቋሞች ወይም ቅርፆች አሉት፤ መጀመሪያ መቆም ፣ ከዛም መዳፎችን ጉልበት ላይ

Read More »

Share