አሏህ ጅን የፈጠረው ጭስ አልባ ከሆነ የእሳት ነበልባል ነው። ጅን ብዙ ቁጥር አመልካች ሲሆን ነጠላ ቁጥር አመልካች የሆነው ቃል ጅኒ የሚለው ነው። አንዳንድ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ እንደሚያምኑት ጅኖች የወደቁ መልአክቶችአይደሉም።

አሏህ ጅኖችን የፈጠራቸው ጭስ አልባ ከሆነ የእሳት ነበልባል ነው። ጅን ብዙ ቁጥር አመልካች ሲሆን ነጠላ ቁጥር አመልካች የሆነው ቃል ጅኒ የሚለው ነው።

አንዳንድ ሰዎች በተሳሳተ መንገድ እንደሚያምኑት ጅኖች የወደቁ መልአክቶች ወይም መላኢካ አይደሉም። አሏህ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ረህማን 55፡15)

ጅኖችን ከጭስ አልባ የእሳት ነበልባል ፈጠራቸው።

አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ:

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ኢማሙ አህመድ)

”መልአክቶች ከብርሃን ተፈጠሩ፤ ጅኖች ከጭስ አልባ የእሳት ነበልባል ተፈጠሩ፤ አደም (በቁርአን እና በሱና) ውስጥ እንደተገለፀላችሁ ተፈጠረ።” 

የመጀመሪያው አልታዘዝም ባይ እምቢተኛ ጅን ኢብሊስ ነው። ጅኖች የእራሳቸው የሆነ ዘር እና ህይወት ያላቸው ፍጡር እንደሆኑ የቁርአን እና የሐዲስ አስተምህሮ ያስረዳል።

ልክ እንደ ሰው ልጆች ሊያምኑ ወይም ሊክዱ ፣ መመሪያውን ሊቀበሉ ወይም ላይቀበሉ ይችላሉ። አሏህ ስለእነሱ ሲናገር

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ጅን 72፡11)

ከእኛም መካከል ደጎች አሉ፤ የዚህ ተፃራሪዎችም አሉ። የተለያየ መንገድን የምንከተል ቡድኖች ነን።

ከጅኖቹ መካከል የሆኑ ቡድኖች ቅዱስ ቁርአን ሲቀሩ በትልቅ አክብሮት እና እምነት ያደምጣሉ።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አህቃፍ 46፡29-32)

አስታውስ ከጅኖች የሆኑ ነፍራን (ቡድኖች) ወደ አንተ በላክን ጊዜ ቁርአንን የሚያደምጡ ሲሆኑ እዚያው በቆሙበት ዝምብላችሁ አድምጡ ተባባሉ። በተጨረሰ ጊዜ ወደ ህዝቦቻቸው አስጠንቃቂ ሆነው ተመለሱ። አሉም፡ ህዝቦቻችን ሆይ! በእርግጥ ከሙሳ በኋላ የወረደውን ፣ ከእሱ በፊት የመጣውን የሚያረጋግጥ ፣ ወደ እውነት እና ወደ ቀጥተኛው መንገድ የሚመራ መጽሐፍ ሰማን። ወገኖቻችን ሆይ! ለአሏህ ተጣሪ ታዘዙ፤ በእሱም እመኑ። (አሏህ) ሃጢያታችሁን ይምርላችኋል፤ ከአሳማሚውም ቅጣት ያድናችኋልና። (ከእሱ) ውጭ ለእሱ አውልያ(ጠባቂ) የለውም። እነዚያ በግልፅ ስህተት (ጥመት) ላይ ናቸው።

ጅኖች የሚበሉ ፣ የሚጠጡ ፣ የሚጋቡ እና የሚራቡ የተገለሉ ፍጡሮች ናቸው። የተለያዩ ነገሮችን የመምሰል ብቃት ያላቸው ሲሆኑ የሰው ልጆች ሊያደርጓቸው ወይም ሊሰሯቸው የማይችሉትን ድንቅ ተግባራትን የመፈፀም ሃይል አላቸው።

ነገርግን የሩቅን ሚስጥር ወይም ያልታየው (ገይብ) ነገር አያውቁም። የራሳቸው የሆነም ምርጫ (ፈቃድ) አላቸው። በመሆኑም በሰሩት ነገር ላይ ይጠየቃሉ።

ኢብሊስ ፣ ሸይጧን እና ነብዩ ሱለይማን ተመልከቱ

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share