
መላኢካ መልአኮች ማለት ሲሆን ነጠላ ቁጥር አመልካቹ ደግሞ መሊክ (መልአክ) የሚለው ቃል ነው። መላኢካዎች አሏህ ከብርሃን የፈጠራቸው መንፈሳዊ ፍጡሮች ናቸው። ከአሏህ የመለኮትነት ድርሻ የላቸውም። ይህ ማለት ፈፅሞ ሊመለኩ አይገባም ማለት ነው።
አይበሉም አይጠጡም ፣ አይራቡም። ዘወትር አሏህን እንደተገዙ እና እሱን እንዳወደሱ የሚኖሩ ሲሆን አሏህ ባዘዛቸው ነገር ፈፅሞ አንታዘዝም አይሉም።
ሁለትም ፣ ሶስትም ፣ አራትም ክንፎች አሏቸው። አንዳንዶቹ እንዲያውም ከዚያ በላይ ክንፎች አላቸው። ተአምራቶችንም መፈፀም ይችላሉ።
መልአኮች የተለያየ ተግባር ወይም ግዴታ አሏቸው። የአሏህን አርሽ (ዙፋን) የሚጠብቁ ፣ የሰውን ልጅ መልካም እና መጥፎ ስራ የሚመዘግቡ የተከበሩ ቁም ፀሐፊዎች አሉ።
ሙታንን መቃብሮቻቸው ውስጥ የሚጠይቁ ሁለት ነኪርና ሙንከር የተባሉ መልአክቶች አሉ። ማሊክ የጀሐነም ፣ ሪድዋን የጀነትን አደራ ሃላፊነት ያለባቸው መልአኮች ናቸው።
ጅብሪል በአሏህ ወህይ (ራዕይ) እና በመልእክተኞች መካከል ያለ መልዕክት አድራሽ ነው። ኢስራፊል በመጨረሻው ቀን ላይ ቀንድ የሚነፋ ሲሆን ሚካኤል ደግሞ የዝናብ እና እዝራኤል የሞት መልአክ ነው። ጥቂቶችን ለመጥቀስ ያህል ብቻ ነው።
መልአኮች የሰው ልጅ ከሚቸገርበት የስጋ ደካማነት የፀዱ ናቸው። ቀንም ሌሊትም የድካም ስሜት ሳይሰማቸው አሏህን በማምለክ ያሞግሳሉ።
ለሙዕሚኖች (ለአማኞች) ምህረትን ይለምናሉ፤ አሏህ በተራገመ ጊዜ ይራገባሉ። አሏህን ይፈራሉ፤ እሱንም በመተናነስ ያመልካሉ። ያዘዛቸውንም ሁሉ ያለማመንታት ይፈፅማሉ።
በመላኢካዎች ማመን ከእምነት ምሰሶዎች ውስጥ አንዱ ነው። መኖራቸውን የካደ ሰው ካፊር ወይም ከሃዲ ነው።



