ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያኔ ያስሪብ ተብላ ወደምትጠራው የአሁኗ መዲና ከተማ በተሰደዱ ጊዜ ጋልበዋት በነበረችው ግመል ዙሪያ ተከታዮቻቸው እና የከተማዋ ሹማምንት ምርጥ ልብሶቻቸውን እና አንፀባራቂ የብረት መከላከያ ልብሶችን እንደለበሱ ተቀበሏቸው።
ጋልበዋት በነበረችው ግመል ዙሪያም ተሰባሰሰቡ። ሁሉንም በትሁት አንደበታቸው መለሱላቸው። “ይች ግመል በአሏህ የታዘዘች ናት። ያረፈችበት ማንኛውም ቦታ የእኔ ቤት የሚሆነው።” ግመሏም ልጓሟን እየጎተተች ሄደች። ትንቢታዊው የመስጅድ ቦታ ላይ እንደደረሰች በርከክ ብላ አረፈች። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ይህ ነው ቤቱ” አሉ።

መስጅድ የገነቡበትም እዚያው ቦታ ነው። እናም መሬቱ ተገዛ ወለሉ በዘንባባ ዛፍ ቀንዘል ተፀዳ ፣ በእሱ ላይ የነበረው የሙሽሪኮች መቃብር ተቆፍሮ እንዲወጣ ተደረገ፤ ተደለደለ።
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መስጅዱን በጡብ እና በድንጋይ በመገንባት እሳቸውም ተሳትፈዋል። ጣራው በዘንበባባ ቀንዘል እንዲሸፈን እና በቆሙ የዘንባባ ዛፎች ግንድ እንዲደገፉ ተደርጓል።
ከመስጅዱ ጀርባ ሌሊቱን እዚያው ለሚያሳልፉ እና ለደካማ ሶሃባዎች ማረፊያ አሱፍህ የተባለ የተከለለ ቦታ ገበንብተዋል። መስጅዱ መጀመሪያ የሰፋው በእራሳቸው በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሲሆን በኸሊፋዎች በአቡበክር አሲዲቅ ፣ በኡመር ኢብን አል-ኸጧብ ፣ በኡስማን ኢብን አፋን እና በወሊድ ኢብን አብዱል መሊክ እና በንጉስ ፋሓድ ኢብን አብዱል አዚዝ የንገትስና ዘመን ነው።


መስጅደ ነበውይ ከመስጅደል ሐረም ቀጥሎ በእስልምና በጣም የሚወደደውና የሚከበረው ሁለተኛው መስጅድ ነው። ብዙ ትሩፋቶችም አሉት። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ እና ሙስሊም)
“ማንኛውንም ቦታ (ለአምልኮ) ጉብኝት ልዩ ቦታ መጀመር የለባችሁም ሶስት መስጅዶች ሲቀሩ፤ የመካ ቅዱስ መስጅድ ፣ ይህ የእኔ መስጅድ እና መስጅደል አቅሷ ናቸው።”
እንዲህም ብለዋል፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(አህመድ)
“በዚህ በእኔ መስጅድ ውስጥ የተሰገደች አንድ ሶላት ሌላ ቦታ ከተሰገደ ሽህ ሶላቶች በላይ በላጭ ናት። የቅዱሱ (መካ) መስጅድ ሲቀር። በቅዱሱ መስጅድ የተሰገደች አንዲት ሶላት ሌላ መስጅድ ውስጥ ከተሰገደ ሽህ ሶላቶች በላይ በላጭ ናት።”
የነብዩ መስጅድ ረውዷ (የአትክልት ስፍራ) ተብሎ የሚጠራ ትልቅ ቦታ አለው። ስለ እሱ በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪና ሙስሊም)
“በቤቴና በሚንበሬ መካከል ከጀነት የአትክልት ቦታዎች የሆነ የአትክልት ቦታ አለ።”

መስጅድ ፣ በይቱል መቅዲስ እና መዲና ከተማ ተመልከቱ




Share