መዲና የስሪብ ተብላ ትጠራ የነበረ ሲሆን ሁለቱ ታዋቂ የአውስ እና የሐዝረጅ ጎሳዎች ይኖሩባት ነበር።
እንዲሁም ከኢስላም በፊት አንዳንድ የአረብ እና የይሁዳ ጎሳዎች ይኖሩባት ነበር። ብዙ ሰሞችም አሏት።
ለምሳሌ ጦባ (መልካሟ) ፣ ሐረም (መጠለያ/ቅድሷ) ፣ ጦይባ (ንፁሃ) እና አል-ሃቢባ (ተወዳጇ) ናቸው። ነገርግን ይበልጥ የምትታወቀው መዲና በሚለው ነው።
መዲና የሚለው ስም መዲነቱ ነብይ (የነብዩ ከተማ) የሚል ቃል ሲያጥር ሲሆን ስሙ የተሰጣት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከመካ መሰደዳቸውን ከትሎ ለእሳቸው መጠለያ በመስጠቷ ዝነኛ ከሆነች በኋላ ነው።


ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በአይር እና በሰውር ተራራ መካከል ያለውን ቅዱስ መጠለያ አድርገውታል። ዛፎቹ እንዳይቆረጡ ፣ የሰሚ ስሚ አሉቧልታ እንዳይፈጠርባት አደርገዋል።
ሙስሊሞች መካን እንደሚወዱት ወይም ከዚያ በላይ እንዲወዷት እና አሏህ እንዲባርካት ለምነዋል።
በአንድ ወቅት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሲገልፃት “ልክ እንደ ምድጃ ናት። ኸቢስ (ቆሻሻዎችን ፣ መጥፎ ሰዎችን) ታስወጣለች፤ ጥሩዎችንም ታነፃለች” ብለው ነበር። (ሙስሊም)

መዲና በውስጧ መስጅደ ነበውይ ወይም የነብዩ መስጅድ ይዛለች። ይህ መስጅድ መካ ውስጥ ከሚገኘው ቅዱሱ መስጅድ ቀጥሎ በቅድስናው እና በታላቅነቱ ሁለተኛው መስጅድ ነው።
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የተሰደዱትም ወደ መዲና ነው። ነዋሪዎቿም መጠለያ እና ሙሉ ድጋፍ ሰጥተዋቸዋል። በመጨረሻም የእስልምና ዋና ከተማ ሆነች።
ነብዩ የሞቱትም የተቀበሩትም መዲና ውስጥ ነው። አሁንም ቢሆን ቀብራቸው ያለው እዚችው ከተማ ውስጥ ነው።




