ኢማን ወይም እምነት

Author picture
ኢማን ስለ እስልምና እውነተኛነት በምላስ መመስከርን ፣ በልብ ማመን እና በተግባር መፈፀም ይይዛል። ስድስቱ የኢማን ምሰሶዎች በአሏህ ፣ በመልአክቶች ፣ በመጽሐፍት ፣ በመልዕክተኞች ፣ በመጨረሻው ቀን ፣ በመለኮታዊ ድንጋጌ ማመን ናቸው።
ኢማን

ኢማን ወይም እምነት ስለ እስልምና እውነተኛነት በምላስ መመስከርን ፣ በልብ ማመን እና መልካም ተግባርትን በመፈፀም ማሳየትን አቅፎ ይይዛል።

ስድስቱ የኢማን ምሰሶዎች በሚከተሉት ማመን በአሏህ ፣ በመልአክቶች ፣ በመጽሐፍት ፣ በመልዕክተኞች ፣ በመጨረሻው ቀን ፣ ጥሩም ይሁን መጥፎ በመለኮታዊ ድንጋጌ ማመን ናቸው።

አሏህ

ኢማን የሚከተሉትን ይይዛል፡-

  1. አሏህ ስለመኖሩ ፣ የፍጥረተ አለሙ እና በውስጡ ያሉ ነገሮች ሁሉ ጌታ ስለመሆኑ አጥብቆ ማመን
  2. አሏህ ከፍጡራኑ ጋር የማይመሳሰሉ ውብና ፈፅሞ እንከን የሌለባቸው ስምና ባህርያቶች ያሉት መሆኑን ማመን
  3. አምልኮ የሚገባው አሏህ ብቻ መሆኑን ማመን
የኢማን ሚዛን

እንዲሁም ኢማን በአሏህ እና በመልእክተኛው የተጠቀሱ ነገሮችን ለምሳሌ ጀሐነም ፣ ጀነት ፣ ሲራጥ ፣ አል-ከውሰር ፣ በፍርዱ ቀን የሰው ልጅ ስራ የሚመዘንበት ሚዛን ስለመኖሩ ማመን አብሮ ይይዛል።

መስጅድ

ኢማን ምልክቶች አሉት። አንዳንዶቹ በተከታዩ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ንግግር ተጠቅሰዋል።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ)

“አንዳችሁም አላመናችሁም ለእራሱ የወደደውን ነገር ለመንድሙ እስካልወደደ ድረስ።”

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አሉ፡ “የሚከተሉት ሶስት ባህርያቶች ያሉት ሰው የኢማን ጥፍጥና(ቃና) ይኖረዋል።

  1. ለእሱ ከምንም ነገር በላይ አሏህ እና መልዕክተኛው ውድ የሆኑለት
  2. ሰውን የሚወድ እና ውዴታውም ለአሏህ ብቻ ብሎ የሆነ
  3. ወደ ጀሐነም እሳት መወርወርን እንደሚጠላ ሁሉ መክፈርን መጥመምን የሚጠላ የሆነ።” (ቡኻሪ)

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም)

“በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ ሰው መልካም ነገር ይናገር ወይም ዝም ይበል። በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ ለጎረቤቱ ደግ ይሁን። በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ ለእንግዳው ደግ ይሁን።”

መልካም ስራዎችን መስራት ኢማን ይጨምራል። መጥፎ ስራዎችን መስራት ደግሞ ኢማን ይቀንሳል። ጀነት ውስጥ የሚገቡት ሙዕሚኖች (አማኞች) ብቻ ናቸው።

ትንሽየ የብናኝ ክብደት ያህል ኢማን ያለችው ሰው እንኳ ቢሆን ጀሃነም ውስጥ ለዘላለሙ አይኖርም።

አሏህ ፣ መላኢካ ፣ የውመል ቂያማ ፣ ረሱል ፣ ቀደር ፣ ጀነት ፣ ጀሐነም እና ሲራጥ ተመልከቱ

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share