አደም (ዐ.ሰ)

Author picture

Table of Contents

አደም( ﷺ ) አሏህ የፈጠረው የመጀመሪያው ሰው ብቻ አይደለም የመጀመሪያው ነብይም ነው። አሏህ አደምን ከጭቃ እና ሁን ብሎ እንደፈጠረው ቁርአን ያስረዳል። አደምን እንደሚፈጥር አሏህ ለመልአክቶች በነገራቸው ጊዜ መጥፎ ነገር የሚሰራ ፍጡር ለምን እንደሚፈጥር ጠየቁ። ነገርግን አደምን የነገራቶችን ስም አስተማረው ከእነሱ በላይም እንደማያውቁ ተመለከቱ።

አሏህ መልአክቶችን ለአደም እንዲሰግዱ ባዘዛቸው ጊዜ፤ ሁሉም ሰገዱ ኢብሊስ ሲቀር። እሱም ከጅኖች መካከል ነበር። በእብሪተኝነት እኔ ከእሱ የተሻልኩ ነኝ። እኔን ከእሳት ፈጠርከኝ፤ እሱን ደግሞ ከጭቃ ፈጠርከው አለ። (አል-ቁርአን 38፡76)

አሏህ ለእሱ ሚስት ፈጠረለት። ልክ እንደ አደም የሐዋ መፈጠር በቁርአን ውስጥ አልተገለፀም። ቢሆንም ከአደም ጋር ተመሳሳይ ተፈጥሮ እና ነፍስ ጋር አጋር እንደፈጠረለት ተገልፃል። ቁርአን እንዲህ ይላል፡ እሱ ያ ከአንዲት ነፍስ የፈጠራችሁ፤ ከእርሷም መቀናጆዋን ወደ እርሷ ይረካ ዘንድ ያደረገ ነው። ከእሱ ሚስቱን ፈጠረለት፤ እሷ ጋር መኖር ይደሰት ዘንድ። (አል-ቁርአን 7፡189)

አደም እና ሐዋ ጀነት ውስጥ ደስ እንዳላቸው እንዲኖሩ ተፈቅዶላቸው ነበር። ነገርግን ከአንዲት ዛፍ እንዳይበሉ ፈሬዋን እንዳያጣጥሙ ተከልክልው ነበር። በመጨረሻም ሁለቱም በሰይጣን ፈተና ወደቁ። እሱም እንዲህ አላቸው። ጌታችሁ መልአኮች እንዳትሆኑ ወይም ለዘላለሙ እንዳትኖሩ ካልሆነ በቀር ጌታችሁ ከዚች ዛፍ አልከለከላችሁም አላቸው። (አል-ቁርአን 7፡20)

በብልጠት እንዲሳሳቱ አደረጋቸው። ከዛፉ ፍሬ በቀመሱ ጊዜ እርቃናቸውን መሆናቸውን ተመለከቱ። ከጀነት በሆኑ ቅጠሎች እራሳቸውን መሸፈን ጀመሩ። አሏህም ከዛፏ እንዳይበሉና ከሸይጧን ፈተናዎች ያስጠነቀቃቸውን አስታወሳቸው።

ከመጽሐፍ ቅዱስ አስተምህሮቶች በተቃራኒ ቁርአን ለስህተታቸው ግሳፄውን (ሃላፊነቱን) አደምና ሐዋ ላይ ነው ያደረገው። ምንም እንኳ ከእሱ በፊት ብትበላም ከዛፍ እንዲበላ ሐዋ አደምን ፈተነችው አይልም። ሐዋ በቁርአን ውስጥ አታላይ አይደለችም። ሃጢያት የፈፀሙት ሁለቱም ናቸው። አሏህን ምህረት ለመኑ፤ አሏህ ሁሉንም ማራቸው።

ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችነን በደልን (አሳሳትን)፤ ባትምረን እና ባታዝንልን በእርግጥ ከከሳሪዎች አንሆናለን አሉ።

(አል-ቁርአን 7፡23)

ስለዚህ የሃጢያት የዘር ውርርስ የሚባል ጥያቄ በኢስላም የለም። ሰዎች ምርጫ ወይም ፈቃድ አላቸው። ስለዚህ በፍቃዳቸው በምርጫቸው ለሰሩት ስራና ለሚያስከትለው ውጤት ከአሏህ ፊት ተጠያቂዎች ናቸው።

(ለተጨማሪ መረጃ ኢብሊስና ሸይጧን የሚለውን ርዕስ ተመልከቱ)

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top