ሱጁድ ማለት በሶላት ውስጥ የመስገጃ ቦታ ላይ ግንባርን የመድፋት ተግባር ነው። ይህ የሚፈፀመው ግንባርን እና አፍንጫን ወለሉ ላይ በማስነካት ፣ መዳፎችን ወለሉ ላይ በማሳረፍ ፣ ጣቶችን ከትከሻ ጋር ትይዩ አድርጎ ወደ ቂብላ በመቀሰር ነው።
ክንዶች ከወለሉ ከፍ ፣ ከጎን ራቅ ማለት አለባቸው። የእግር ጣቶችን ወለሉ ላይ በመትከል ወደ ቂብላ አቅጣጫ ማዞር ነው። በሱጁድ ወቅት ክርንን ወለሉ ላይ ፣ ደረትን ወይም ሆድን ታፋ ላይ ማድረግ አያስፈልግም።
ሱጁድ ላይ ቅዱስ ቁርአን መቅራት አይፈቀድም። ይልቁንም ለዚህ አለም እና ለመጭው አለም ብዙ ዱአ ማድረግ ይገባል። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ)
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ሙስሊም)
“ባሪያው ለጌታው በጣም ቅርብ የሚሆነው ሲጁድ ላይ በሆነ ጊዜ ነው። እናም በእሷ ብዙ ዱአን ማድረግን አብዙ” ብለዋል።
ሱጁድ ላይ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያነቡት የነበረው ዱአ ‹ሱብሃነ ረቢየል አዕላ (ልኡል ሃያል የሆነው ጌታየ ከጉድለት ሁሉ የጠራ ነው)› የሚለው ነው። ይህንን ሶስት ጊዜ ይደግሙት ነበር።





Share