ሩኩዕ ማለት በሶላት ውስጥ የማጎንበስ ተግባር ነው። ጉልቢን እንደሚይዙ ጣቶችን ዘርዘር አድርጎ መዳፉን ጉልበት ላይ በማስቀመጥ ማጎንበስ ነው። ክርኖች ከፊት እና ከጎን በኩል ራቅ ማለት አለባቸው።
ሩኩዕ

ሩኩዕ ማለት በሶላት ውስጥ የማጎንበስ ተግባር ነው። ጉልቢን እንደሚይዙ ጣቶችን ዘርዘር አድርጎ መዳፉን ጉልበት ላይ በማስቀመጥ ማጎንበስ ነው። ክርኖች ከፊት እና ከጎን በኩል ራቅ ማለት አለባቸው።

ጀርባ ቀጥ ብሎ ከወለሉ ጋር ትይዩ መሆን አለበት። እራስ ወደ ላይም ወደታችም መታጠፍ የለበትም። በቃ መካከለኛ።

ሩኩዕ ላይ ቅዱስ ቁርአን መቅራት አይፈቀድም። ይልቁንም አሏህን ማላቅ ይኖርብናል። ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሩኩዕ ላይ ያነቡት የነበረው ዚክር ሱነብሃነ ረቢየል አዚም (ታላቅ የሆነው ጌታ ከጉድለቶች ሁሉ የጠራ ነው) የሚለው ነው። እኛም ማድረግ ያለብን ይህንኑ ነው።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እነዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም)

“(ሶላት ውስጥ ሱጁድ ወይም ሩኩዕ ባደረኩ ጊዜ ቁርአን መቅራትን ተከለከልኩ። በሩኩዕ ላይ ጌታችሁን አልቁ፤ ስጁድ ላይ ብዙ ዱአ አድርጉ፤ ዱአችሁ ምላሽ ለማግኘት የቀረበ ነውና።”

ሩኩዕ ማጎንበስ

ሶላት እና ሱጁድ ተመልከቱ

Related posts

ሲዋክ እና ጥቅሞቹ

ሲዋክ እና ጥቅሞቹ

ኢስላም ንፅህናን የእምነቱ ግማሽ አካል ያደረገ ብቸኛ መለኮታዊ ሃይማኖት ነው። ሲዋክ ማለት ጥርስንና አፍን በእንጨት መፋቂያና መሰል ነገራት ከመጥፎ ጠረንና ቅሪቶች ማጽዳት ማለት ነው፡፡

Read More »
ሱጁድ

ሱጁድ

ሱጁድ ማለት በሶላት ውስጥ የመስገጃ ቦታ ላይ ግንባርን የመድፋት ተግባር ነው። ይህ የሚፈፀመው ግንባርን እና አፍንጫን ወለሉ ላይ በማስነካት ፣ መዳፎችን ወለሉ ላይ በማሳረፍ ፣

Read More »
ኢቃም

ኢቃም

ኢቃማ ከፈርድ (ግዴታ) የጀመአ ሶላት መጀመሪያ ላይ የሚባል መነባነብ ነው። አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረ.ዐ) “የአዛን ቃላት ሁለት ጊዜ እና የኢቃም ቃላትን በተናጠል አንድ ጊዜ ብቻ

Read More »
ረከአ

ረከአ

እያንዳንዱ ሶላት የአንድ ወይም የሁለት ፣ የሶስት ወይም የአራት ረከአ ህብር ነው። እያንዳንዱ ረከአ አቋቋሞች ወይም ቅርፆች አሉት፤ መጀመሪያ መቆም ፣ ከዛም መዳፎችን ጉልበት ላይ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share