የገላ ትጥበት በአረብኛ ጉሱል ተብሎ ይጥራል። ጉሱል ሙሉ አካልን መታጠብ ነው። ከሶላት በፊት ንፁህ ለመሆን ሙስሊሞች ከፊል ትጥበት ወይም ውዱእ ያደርጋሉ። ነገርግን በአንዳንድ ጉዳዮች የገላ ትጥበት የግድ መደረግ አለበት።

ሙሉ ትጥበት የሚያስገድዱ ጉዳዮች የሚከተሉት ናቸው።
- ግብረ ስጋ ግኑኝነት ካደረጉ በኋላ ወይም የዘር ፈሳሽ ነቅተው ወይም በህልማቸው ተኝተው ሲፈስ
- ሴት ልጅ የወር አበባ ወይም የወሊድ ደም ስትጨርስ
- አዲስ ሙስሊም ለመጀመሪያ ጊዜ ሸሃዳ (የእምነት ምስክርነት ቃል) ከተቀበላ በኋላ
- አንድ ሙስሊም ከሞተ በኋላ ለቀብር ሲያዘጋጁት
የገላ ትጥበት የሚወደድባችው ሁኔታዎች ደግሞ የሚከተሉተ ናቸው።

የገላ ትጥበት እንደሚከተለው ነው።

- የገላ ትጥበት በማድረግ ትልቁን ቆሻሻ ለማስወገድ በመነየት (በማሰብ) ቢስሚላህ (በአሏህ ስም) ማለት
- ሁለቱንም እጆች እስከ እጅ አንጓ ድረስ ሶስት ጊዜ ማጠብ
- ሃፍረተ ገላን እና ዙሪያውን ማጠብ
- ውዱእ ማድረግ፤ እዚህ ላይ እግሮችን ውዱእ ሲያደርጉ ማጠብ ወይም ጉሱል አድርገው ሲጨርሱ ማጠብ ይቻላል።
- እርጥበት ባላቸው ጣጦች ፀጉርን ማሸት

- እራስ ላይ ሶስት ጊዜ ውሃ ማፍሰስ እና ጆሮን ጨምሮ ማጠብ። ሴቶች ሽሩባቸውን ወይም ስሬታቸውን እንዲፈቱ አይታዘዙም (ግዴታ ይደለም)። ሶስት ጊዜ እራሳቸው ላይ ውሃ ማፍሰስ እና ሳይፈቱ ማሸት በቂ ነው።

- በቀኝ ጎን ውሃ ማፍሰስ፤ ከዛም ከላይኛው የአካል ክፍል በመጀመር እስከታችኛው የአካል ክፍል ማድረስ። ከዛም በግራ ጎን እንዲሁ ተመሳሳይ ማድረግ። ውሃው በሁሉም የአካል ክፍል መዳረሱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ለምሳሌ ድብቅ በሆኑ ቦታዎች በብብት ፣ በእንብርት እና የጆሮ የውስጠኛው ክፍል ወ.ዘ.ተ ናቸው።
ጦሐራ ፣ ውዱእ ፣ ተየሙም ፣ ኢህራም ፣ አረፋ እና ሸሃዳ ተመልከቱ




Share