አረፋ አረፋት ተብሎ ይጠራል። አረፋ ከመካ በስተ ሰሜን በኩል የሚገኝ በጣም ሰፊ አውላላ ሜዳ ነው። በሐጅ ወቅት በዙልሂጃ ወር በአስረኛው ቀን ፀሐይ ከወጣች በኋላ እስክትጠልቅ ድረስ ሁጃጆች በዚህ ለጥ ያለ ሜዳ ለአንድ ቀን ይሰባሰባሉ።
አረፋ ተራራ

አረፋ አረፋት ተብሎ ይጠራል። አረፋ ከመካ በስተ ሰሜን በኩል የሚገኝ በጣም ሰፊ አውላላ ሜዳ ነው። በሐጅ ወቅት በዙልሂጃ ወር በአስረኛው ቀን ፀሐይ ከወጣች በኋላ እስክትጠልቅ ድረስ ሁጃጆች በዚህ ለጥ ያለ ሜዳ ለአንድ ቀን ይሰባሰባሉ።

አረፋ ውስጥ መቆየት የሐጅ ዋነኛ የላቀ ተግባር ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ሐጅ አረፋ ነው” እስኪሉ ድረስ። (ትርሚዚ)

ሐጅ ማድረግ አስቦ ነገርግን የአረፋ ሜዳ ላይ የመገኘት እድሉ ያመለጠው ሰው ሐጁ ወደ ኡምራ ዞሯል። እናም ለሐጁ ላመለጠው ማካካሻ እንዲሁም ከብት መስዋዕት ማድረግ አለበት።

በዚህ ታላቅ ቀን አሏህ ልቅናውን በሚያረጋግጥ መልኩ ወደ ታችኛው ሰማይ ይወርዳል። አሏህ እዚያ ቦታ ላይ ያሉ ሰዎችን ያመሰግናል። ለመልአክቶችም “ባሮቼን ተመልከቷቸው ወደ እኔ ተመሰቃቅለው ፣ አቧራ ለብሰው መተዋል ፣ በእያንዳንዱ ጥልቅ ሸለቆ ውስጥ ሆነው የሚያለቅሱ ባሮቼን ተመልከቱ። ምህረት ያደረኩላቸው መሆኑን ምስክር ሁኑ” ይላል።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም)

“አሏህ ብዙ ሰዎችን ከጀሐነም እሳት የሚያድንበት በአረፋ ቀን ከሚያደርገው የበለጠ ሌላ ቀን የለም። በዚህ ቀን አሏህ ለሰዎቹ ቅርብ ይሆናል። በባሮቹ በመኩራት መልአክቶቹን “ምን እንደሚፈልጉ አያችሁ?” ሲል ይጠይቃቸዋል”

አረፋ

ሁጃጆቹ የዝሁር እና የአሱር ሶላቶችን ያሳጥራሉ ይቀጥላሉም። ይህ ማለት ለእያንዳንዱ ሶላት ከአራት ረከአ ይልቅ ሁለት ረከአ ይሰግዳሉ ማለት ነው። ሁለቱ ሶላቶች የሚሰገዱት አንዱ ከሌላኛው ቡኋላ ነው። በአንድ አዛን ሁለት የተለያየ ኢቃማ የሚደረግ ሲሆን አንዱ ለዙሁር ሌላኛው ለአሱር ነው።

ሁጃጆች አረፋ ላይ እንዳሉ አሏህን በማስታወስ ፣ በመለመን ፣ በማሞገስ ፣ በማመስገን እና ምህረቱን በመለመን ፀሐይ እስክትጠልቅ ድረስ ቀኑን ያሳልፋሉ።

አረፋ

ሐጅ ፣ ሚና ፣ ሙዝደሊፋ ፣ ሰኢ ፣ አዛን እና ኢቃም ተመልከቱ

Related posts

ኡምራ አደራረግ

የኡምራ አፈፃፀም

ኡምራ ኢቲማር ከሚለው የአረብኛ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ጉብኝት ማለት ነው። ኡምራ በኢህራም ላይ መሆን ፣ በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ማድረግ ፣ በሶፋ እና መርዋ መካከል

Read More »
ኢህራም

ኢህራም

ኢህራም ሐጅ ወይም ኡምራ ለማድረግ ወይም ደግሞ ሁለቱንም ለማድረግ መነየት ነው። ምክኒያቱም ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ “የስራዎች ሁሉ ምንዳ መሰረቱ ኒያ ነው” ብለዋልና።

Read More »
ሚና

ሚና

ሚና ከመካ በምስራቅ በኩል 4.8ኪ.ሜ ራቅ ብሎ የሚገኝ በረሃማ ቦታ ሲሆን በርካታ የሐጅ ተግባራቶች የሚፈፀሙት በዚሁ ቦታ ነው።

Read More »
ሐጅ

ሐጅ

ሐጅ አምስተኛው የእስልምና ምሰሶ ሲሆን በገንዘቡ እና በአካሉ የአሏህን ቤት መጎብኘት የሚችል ሰው በህይወት ዘመኑ አንድ ጊዜ ይህን የማድረግ ግዴታ አለበት።

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share