ሚና ከመካ በምስራቅ በኩል 4.8ኪ.ሜ ራቅ ብሎ የሚገኝ በረሃማ ቦታ ሲሆን በርካታ የሐጅ ተግባራቶች የሚፈፀሙት በዚሁ ቦታ ነው።

ሁጃጆች በተርዊያ ቀን ፀሐይ ከመግባቷ በፊት ወይም ከገባች በኋላ ወደ ሚና ያቀናሉ። በዙል ሂጃ በዘጠንኛው ቀን ፀሐይዋ ከወጣች በኋላ ወደ አረፋ ይሄዳሉ።
በአረፋ ሜዳ ላይ ከቆዩ በኋላ እና ሙዝደሊፋ ውስጥ ሌሊቱን ካሳለፉ በኋላ በአስረኛው ዙልሂጃ በእርዱ ቀን ፀሐይዋ ከወጣች በኋለ ወደ ሚና ይመለሳሉ።
ሁጃጆቹ ወደ ሚና ተመልሰው አራት ረከአ ሶላቶችን ወደ ሁለት ረከአ አሳጥረው ይሰግዳሉ፤ ሳይቀላቀል ማለት ነው።
በአስራ አንደኛው እና በአስራ ሁለተኛው ሁልሂጃ ሌሊቱን ሚና ውስጥ ማሳለፉ ግዴታ ነው።

ሚና ውስጥ ሶስት ጀምራት (የድንጋይ ምሰሶዎች) አሉ። ነጠላ ቁጥር አመልካቹ ጀምራ ሲሆን ትርጉሙም የድንጋይ ምሰሶ ማለት ነው።
እነሱም ጀምረቱል አቀባ (የአቀባ የድንጋይ ምሰሶ) ፣ ጀምረቱል ውስጧ (መካከለኛው ምሰሶ) ፣ ጀምረቱል ሱግራ (ትንሹ ምሰሶ) ናቸው።
የሐጅ ተግባራት ውስጥ አንዱ በእርዱ ቀን በጀምረቱል አቀባ ላይ ጠጠሮችን መወርወወር ሲሆን እንዲሁም በዙልሂጃ 11ኛው ፣ 12ኛው እና 13ኛው ቀን በሶስቱም ምሰሶዎች ላይ ጠጠሮችን መወርወርን ይይዛል።
ሁጃጆች ትንሹን ምሰሶ በጠጠር ይመታሉ፤ በመቀጠል መካከለኛውን ጀምራ እና በመጨረሻም የአቀባን ምሰሶ በዚሁ ቅደም ተከተል በሶስቱ ቀናቶች ከቀትር በኋላ በጠጠር ይመታሉ። እያንዳንዱን ምሰሶ በሰባት ጠጠሮች አሏሁ አክበር እያሉ ይመታሉ።
በ13ኛው ዙልሂጃ ጠጠር መወርወር ምርጫ እንጅ ግዴታ አይደለም። ሁጃጆች በ12ኛው ዙልሂጃ ጠጠሮችን ከወረወሩ በኋላ ወደ መካ ከተማ በመመለስ ጠዋፍ አል-ወዷ (የስንብት ጠዋፍ) ያደርጋሉ። ነገርግን ፀሐይዋ ከመጥለቋ በፊት ወጥተው መሄድ አለባቸው።

ጠዋፍ ፣ ሐጅ ፣ አረፋ እና ሙዝደሊፋ ተመልከቱ




Share