ኡምራ የሚለው ቃል ኢቲማር ከሚለው የአረብኛ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙ ጉብኝት ማለት ነው። ኡምራ በኢህራም ላይ መሆንን ፣ በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ማድረግ ፣ በሶፋ እና መርዋ መካከል መጓዝ ፣ ራስን መላጨት ወይም ፀጉርን ማሳጠር አጠቃሎ የያዘ ነው።

ኡምራ ቅዱስ ተግባር ነው። ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ “ከአንድ ኡምራ እስከ ቀጣዩ ኡምራ ባለው መካከል ለተፈፀመ ማኝናውም ወንጀል ስርየት (ምህረት) ነው። ቅቡልነትን ያገኘ ሐጅ ምንዳው (ሽልማቱ) ምንም ሳይሆን ጀነት ነው።”
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሶሃቦቻቸው ኡምራ እንዲያደርጉ እንዲሁም በቤተሰባቸው ስም ቢሆን እንኳ ይህንኑ እንዲፈፅሙ ያበረታቷቸው ነበር። ለቂት ኢብን አሚር እንዳስተላለፈው
“ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መጣሁና አባቴ በጣም አርጅቷል ሐጅ ወይም ዑምራ ለማድረግ ፣ ጉዞ ለመጓዝ አቅም የለውም አልኳቸው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በአባትህ ስም ሃጅ እና ዑምራ አድርግ አሉኝ።” (ትርሚዚ እና አቡዳውድ)
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(አህመድ እና ኢብኑ ማጃ)
“በረመዷን ወር ኡምራ ማድረግ ሐጅ ከማድረግ ጋር (ምንዳው) እኩል ነው።”

ነገርግን ይህ ገንዘብም አቅምም ያለው ሰው ግዴታ የሆነውን ሐጅ ከመፈፀም ነፃ አያደርግም። በሌላ ወቅት ደግሞ እንዲህ አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ነሳኢ ፣ ኢብ ማጃ እና ኢብኑ ሂባን)
“ሁጃጆች እና እነዚያ ዑምራ የሚያደርጉ የአሏህ እንግዶች ናቸው። ፀሎታቸው ይመለሳል፤ የለመኑት ምህረት ይሰጣቸዋል።”
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አንዲህ አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ነሳኢ)
“የአሏህ እንግዶች ሶስት ናቸው። እነሱም በአሏህ መንገድ ጅሃድ የሚያደርጉ ፣ ሀጅ የሚያደርጉ እና ዑምራ የሚያደርጉ ናቸው።”
ኡምራ ለማድረግ የምንከተላቸው
- ሐጅ ወይም ኡምራ ማድረግ ያሰበ ሰው በኢህራም ሁኔታ ላይ መግባት አለበት ብለው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በወሰኑት መሰረት ሚቃት ተብሎ የሚታወቀው ቦታ ላይ በኢህራም በመግባት ያስፈልጋል
- መካ ከተማ ውስጥ ከሚገኘው ቅዱሱ መስጅድ እስኪደርሱ ድረስ ተልቢያ ማለት
- በካዕባ ዙሪያ ከቀኝ ወደ ግራ በመዞር ሰባት ጊዜ ጠዋፍ ማድረግ
- ከተቻለ ጠዋፍ ካደረጉ ቡኋላ ከመቃመ ኢብራሂም ቡኋላ ሁኖ ሁለት ረከአ መስገድ። ካልሆነ በቅዱስ መስጅድ ውስጥ ማኝኛውም ቦታ በላይ መስገድ ይቻላል።
- በሶፋና መርዋ ኮረብታዎች መካከል ሰባት ጊዜ ሰኢ ማድረግ። ሰኢውን ሶፋ ላይ ጀምሮ መርዋ ላይ መጨረስ።
- ራስን መላጨት ወይም ፀጉርን ማሳጠር። ለሴቶች የጣታቸውን ጫፍ ታክል ፀጉራቸውን መቁረጥ

ረመዷን ፣ ኢህራም ፣ ጠዋፍ ፣ ሰኢ እና ሐጅ ተመልከቱ




Share