ረመዷን በእስልምና የቀናት አቆጣጠር መሰረት ዘጠንኛው ወር ነው። በዚህ ወር ከንጋት ጀምሮ ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ በጥብቅ ይፆማል። ይህን ወር መፆም ከአምስቱ የእስልምና ምሰሶዎች ውስጥ አንዱ ነው።

ረመዷን በእስልምና የቀናት አቆጣጠር መሰረት ዘጠንኛው ወር ነው። በዚህ ወር ከንጋት ጀምሮ ፀሐይ እስከምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ በጥብቅ ይፆማል።

ይህን ወር መፆም ከአምስቱ የእስልምና ምሰሶዎች ውስጥ አንዱ ነው። በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና እንደተገለፀው የረመዷንን ወር መፆም ብዙ ጥቅሞች አሉት። የሚከተሉት የተወሰኑት ናቸው።

ረመዷን በእስልምና የቀናት አቆጣጠር መሰረት ዘጠንኛው ወር ነው።
  • የፆመኛ ሰው አፍ ሽታ ከሚስክ ሽታ በላይ ተወዳጅ ነው። (ቡኻሪ)
  • ፆመኛ ሰው ሁለት የደስታ ጊዜያቶች አሉት፤ አንዱ ፆሙን ሲፈታ እና ሌላኛው ደግሞ ጌታውን ሲያገኝ በመፆሙ የሚደሰተው ነው። (ቡኻሪና ሙስሊም)
  • ጀነት ውስጥ ፆመኞች ብቻ የሚገቡበት ረያን ተብሎ የሚጠራ በር አለ። በእሱ የሚገባ የለም እነሱ (ፆመኞች) ቢሆኑ እንጅ። (ቡኻሪ)
  • በዚህ ወር የጀነት በሮች ይከፈታሉ ፣ የጀሐነም በሮች ይዘጋሉ ፣ አጋንቶችም ተጠፍረው ይታሰራሉ። (ቡኻሪ)
  • አሏህ ፆምን ለእራሱ መረጠ፤ እናም የሚመነዳው እሱ ነው። ምንዳውን የሚያባዛው ያለልኬታ (ያለሂሳብ) ነው  ሐዲሰል ቁድሲ ውስጥ እንዳለው “..ፆም ሲቀር እሱ ብቻ ለእኔ ነው። ለእሱም እኔ እመነዳዋለሁ።” (ቡኻሪ)
  • በእያንዳንዱ የረመዷን ምሽት አሏህ ሰዎችን ከጀሐነም እሳት ያድናል። (ትርሚዚ ተዘግቦታል፤ አል-ሃኪም ሶሂህ ብለውታል)
  • ለይለቱል ቀድር (የድንጋጌይቱ ሌሊት) ከሽህ ወራቶች በላይ በላጭ ነው። የሚገኘውም በዚሁ ወር ውስጥ ነው። በዚህ ሌሊት ምንዳውን እንደሚያገኝ አምኖ እና ተስፋ አድርጎ ሶላቶችን የሰገደ ያለፉ ወንጀሎቹ ሁሉ ይማሩለታል። (ቡኻሪ እና ሙስሊም)
ለይለቱል ቀድር

በእርግጥ የረመዷን ወር ልክ እንደ ትምህርት ተቋም ነው። ደግነት እና ሃይማኖተኛነትን ያስተምራል።

ሙስሊሞች ይህን ወር ሲፆሙ ከምግብ ፣ ከመጠጥ እና ከግብረስጋግኑኝነት ብቻ አይደለም የሚታቀቡት ይልቁንም በሚችሉት አቅም ሁሉንም የሃጢያት ተግባራቶች ለማስወገድ ይታገላሉ።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) አሉ፡ “አንዳችሁ በፆማችሁ ጊዜ መጥፎ ቃልን አይጠቀም ወይም የብልግናን ተግባር አይፈፅም። የሆነ ሰው ከተፋለመው ወይም ከሰደበው “እኔ ፆመኛ ነኝ! እኔ ፆመኛ ነኝ!” ይበለው ብለዋል። (ቡኻሪና ሙስሊም)

እንዲህም ብለዋል፡ “(ፆመኛ ሆኖ) መጥፎ ንግግርን እና ተግባርን ያልተወ ሰው ምግብ እና መጠጥ መተውን አሏህ አይፈልግም።” (ቡኻሪ)

ሃያሉ ፣ ጥበበኛው የአለማት ጌታ፤ የሰው ልጆችን ሁሉ የፈጠረ ጌታ ለፉጡራኖቹ የተሻለውን ነገር እሱ ያውቃል። በሚያዛቸው ነገሮች ሁሉ በጎ አለ። ይህን በጎ ነገር በእኛ ውስን እውቀት ላንረዳው እንችል የሆናል እንጅ ሁሉም ነገር ለበጎ ነው።

ትዕዛዛቱን መታዘዝ እና የከለከላቸውን ነገሮች መራቅ አለብን። እንዲሁም አለማዊና ቁሳዊ ነገሮችን አለመፈለግ ይኖርብናል። አሏህ እንደሚለው

“ብታውቁ መፆማችሁ ለእናንተ በላጭ ነው።”
(አል-ቁርአን 2፡184)
0%
1
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ፆም

ጥያቄና መልስ፡ የረመዷን ፆም

የረመዷን ፆም ፈተና 4 ጥያቄዎችን ይዟል፡፡ ፈተናውን ለማለፍ 3 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ፡፡

1 / 4

Bookmark question icon

1 የፆም ወቅት የሚጀምረው _______ ነው፡፡

2 / 4

Bookmark question icon

2 ጀነት ውስጥ _______ ተብሎ የሚጠራ በር አለ፡፡ በእሱም በኩል የሚገቡት ፆመኞች ብቻ ናቸው፡፡

3 / 4

Bookmark question icon

3 ከረመዷን ወር ትሩፋቶች (ጥቅሞች) ውስጥ የሆነው የትኛው ነው?

4 / 4

Bookmark question icon

4 አሏህ ፆምን የደነገገው ለየትኞቹ ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 0%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

ፆም ፣ ለይለቱል ቀድር ፣ ሐዲሰል ቁድሲ እና ኢእቲካፍ ተመልከቱ

0%
0
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

የእስልምና ምሰሶች

ስለ ረመዳን ያላቸሁን እውቀት ፈትሹ (ለጀማሪዎች)

1 / 9

Bookmark question icon

1 ረመዳን በኢስላማዊ የቀን አቆጣጠር ስንተኛው ወር ላይ ይገኛል?

2 / 9

Bookmark question icon

2 ረመዳን ከሚከተሉት የቁርአን ሱራዎች (ምዕራፎች) ውስጥ በየትኛው ውስጥ ተጠቅሷል?

3 / 9

Bookmark question icon

3 የረመዳንን ወር መጾም ከእስልምና አምስቱ ምሰሶዎች ስንተኛው ነው?

4 / 9

Bookmark question icon

4 ዒድ አል-ፊጥር (ከረመዳን ጾም በኋላ የሚከበረው በዓል) በየትኛው ቀን ላይ ይውላል?

5 / 9

Bookmark question icon

5 በረመዳን ወር የተካሄደው ዝነኛ ውጊያ (ዘመቻ) የትኛው ነው?

6 / 9

Bookmark question icon

6 እውነት ወይስ ሐሰት፡ ቁርአን በረመዳን ወር በአላህ (ሱ.ወ) የተወረደ ብቸኛው ቅዱስ መጽሐፍ ነው?

7 / 9

Bookmark question icon

7 ለይለቱል-ቀድር ከምን የምትበልጥ ሌሊት ናት?

8 / 9

Bookmark question icon

8 በፍርዱ ቀን (በቂያማ) ረመዳንን የጾሙ ሰዎች በየትኛው የጀነት በር እንዲገቡ ይነገራቸዋል?

9 / 9

Bookmark question icon

9 እውነት ወይስ ሐሰት፡ በመርሳት መብላት ወይም መጠጣት ጾምን ያፈርሳል (ያበላሻል)?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 0%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

ኢእቲካፍ

ኢእቲካፍ

ኢእቲካፍ ማለት ወደ አሏህ የበለጠ ለመቅረብ በማሰብ የረመዷን የመጨረሻ አስር ቀናትን መስጅድ ውስጥ ተቀምጦ ማሳለፍ ነው። ለይለቱል ቀድር (የድንጋጌው/የውሳኔው ሌሊት) በዚህ ጊዜ ውስጥ ይገኛል። ቅዱስ

Read More »
ለይለቱል ቀድር

ለይለቱል ቀድር

ለይለቱል ቀድር (የውሳኔው ምሽት) በመጨረሻው የረመዷን አስር ሌሊቶች ውስጥ በአንዱ ሌሊት ውስጥ የሚገኝ ነው። ይህ ምሽት አሏህ ቁርአን ያወረደበት እና በጎ ስራዎችን ከሽህ ወራቶች ስራ

Read More »
የፍላጎት ፆም

የፍላጎት ፆም

የፍላጎት ፆም በተወሰኑ ወቅቶችና አጋጣሚዎች መፆም የተወደደ ነው። ከነዚህም መካከል፦ የአረፋ ቀን መፆም፡ በ9ኛው ዙልሂጃ የሚውል ሲሆን ሀጅ ላይ ያልሆኑ ሰዎች ቢፆሙት ይወደዳል።

Read More »
ፆም

ፆም

ሲያም (ፆም) ማለት የአሏህን ውዴታ በመሻት ፀሐይ ከወጣችበት ጊዜ አንስቶ እስከ ምትጠልቅበት ጊዜ ድረስ ከምግብ ፣ ከመጠጥ እና ግብረ ስጋ ግኑኝነት ከመፈፀም መታቀብ ነው።

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share