ኢእቲካፍ ማለት ወደ አሏህ የበለጠ ለመቅረብ በማሰብ የረመዷን የመጨረሻ አስር ቀናትን መስጅድ ውስጥ ተቀምጦ ማሳለፍ ነው። ለይለቱል ቀድር (የድንጋጌው/የውሳኔው ሌሊት) በዚህ ጊዜ ውስጥ ይገኛል።

ቅዱስ ቁርአን ይህን ሲገልፅ ከሽህ ወራቶች በላይ በላጭ ነው ይላል። በዚህ ወቅት ኢእቲካፍ ላይ ያለ ሰው ለአጭር ጊዜ እና በጣም አስፈላጊ ለሆነ ነገር ብቻ ካልሆነ በቀር መስጅዱን ለቆ መውጣት አይፈቀድም።
ለምሳሌ ለተፈጥሮ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ወይም ምግብ ሊያመጣለት የሚችል ሰው ከሌለ ምግቡን ለማምጣት ወ.ዘ.ተ። ኢእቲካፍ ላይ የሆነ ሰው የተለያዩ የአምልኮ ተግባራት በመፈፀም ጊዜውን ማሳለፍ ይኖርበታል።
ለምሳሌ ቁርአን መቅራት ፣ አሏህን ማስታወስ (በዚክር) ፣ አሏህን ማመስገን እና ማላቅ ፣ ዱአ ማድረግ ፣ የእስልምና እውቀቱን ማዳበር ፣ ትምህርት መስጠት ወ.ዘ.ተ

ይህ የኢእቲካፍ ተግባር የነብዩ ሱና ነው፤ ግዴታ ግን አይደለም። ነገርግን ኢእቲካፍ ላይ ለመሆን ቃል የገባ ሰው ቃልኪዳኑን መሙላት አለበት።
ረመዷን ፣ ለይለቱል ቀድር ተመልከቱ



Share