የእስልምና ሃይማኖት በሁለት ምንጮች ላይ የተመሰረተ ነው። እነሱም ቅዱስ ቁርአን እና የነብዩ ሱና ናቸው። በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና እውነት እና በኢስላም ውስጥ ያለውን ቦታ ትማራላችሁ።

የእስልምና ሃይማኖት በሁለት ምንጮች ላይ የተመሰረተ ነው። እነሱም ቅዱስ ቁርአን እና የነብዩ ሱና ናቸው።

በዚህ ፅሁፉ ውስጥ ስለ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና እውነት እና በኢስላም ውስጥ ያለውን ቦታ ትማራላችሁ።

የፅሁፉ አላማ

  1. የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና ጥቅሞች ታውቃላችሁ
  2. ሱና በህግ ድንጋጌዎች ውስጥ ያለውን ጠቀሜታ ታውቃላችሁ
  3. የሱና በህግ ድንጋጌዎች ውስጥ ያለውን ልቅና ትረዳላችሁ

የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና አሏህ ለነብዩ ሙሐመድ ያደረገላቸው ወህይ (ራዕይ) መገለጥ ነው። ከአሏህ መጽሐፍ ጋር የእስልምና ሃይማኖት ምንጭ እና መሰረት ነው።

ሁለቱ የማይነጣጠሉ የእምነት ምስክርነት አካል ናቸውና። በሱና ያላመነ ሰው በቁርአን አያምንም።

የሱና ፍች

የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና የእሳቸውን ንግግሮች ስራዎች ፣ ውሳኔዎች ፣ ግብረገባቸውን እና ስብዕናቸውን ሁሉ የሚያጠቃልል ነው።

ሱና የቃልበቃል ትርጉሙ ‹መንገድ› ወይም ‹ዘዴ› የሚል ነው። ሱና የሚለው የአረብኛ ቃል ፍች በሸሪአ ወይም በእስልምና ህግ ይለያል። ለምሳሌ በእስልምና መሰረታዊ መርሆዎች ዙርያ ኡለማዎች ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተናገሩት ፣ የሰሩት ወይም ያረገገጡት ማንኛውም ነገር ነው።

የሱና ደረጃ

የነብዩ ሱና በእስልምና ውስጥ ትልቅ ቦታ ያለው ሲሆን የሚከተሉት ደረጃውን እና ጠቀሜታዎቹን ያሳያል።

1 ሁለተኛው የህግ ድንጋጌ ምንጭ ነው

ሱና ከቅዱስ ቁርአን ቀጥሎ ሁለተኛው የእስልምና ሃይማኖት ምንጭ ነው። በአል-ሚቅዳድ ኢብን ማዲ ከሪብ አል-ኪንዲ እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ እንዲህ አለ፡

ሱና ከቁርአን ቀጥሎ ሁለተኛው የሸሪአ ህግ ምንጭ ነው። ሁለቱም ምንጮች በጣም አስፈላጊ ሲሆኑ አንድ ሙእሚን ሁለቱንም ሳይዝ እስልምናን ሊተገብር አይችልም። ሱና ቁርአንን ያብራራል፤ ስለእስልምና የአምልኮት ጉዳይ ዝርዝር መረጃ ይሰጣል። ምሳሌ የሶላት ስግደት። አሏህ በቀን አምስት ጊዜ እንድንሰግድ አዞናል። ነገርግን እንዴት መስገድ እንዳለብን አልገለፀልንም። ሱና ይህን ትልቅ የአምልኮት ተግባር እንዴት እንደምንፈፅም ያብራራልናል።

‹‹መጽሐፉ እና ከእሱ ጋር አቻው ተሰጥቶኛል። አንድ ሰው መከዳ (አልጋ መሰል) ጋደም ብሎ እንዲህ ይላል፡ ‹‹ቁርአንን ያዝ። እናም እዚያ የተፈቀደ የምታገኘውን ማንኛውንም ነገር የተፈቀደ አድርገው። እዚያ የተከለከለውን ማንኛውንም ነገር የተከለከለ አድርገው›› ይላል።›› (ሙሰነድ አህመድ 17174)

2 ከሃያሉ አሏህ የሆነ መገለጥ ነው

የነብዩ ሱና ከአሏህ ለመልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ያደረገው የራዕይ መገለጥ ነው። ሃያሉ አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ነጅም 3-4)

“ከስሜቱ (ከፍላጎቱ) አይናገርም። እሱ (ንግግሩ) የሚወርድ ራዕይ እንጅ ሌላ አይደለም። ሃይለ ብርቱ (መልአክ) አስተማረው።”

3 የቁርአን ማብራሪያ ነው

የነብዩ ሱና የቁርአን ማብራሪያ በውስጡ ይዟል። አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ነህል 44)

“ከግልፅ ማስረጃዎች ጋር በመጽሐፍት ላክናቸው። ወደ አንተም ለሰዎች ወደ እነሱ የተወረደውን (ፍች) ልትገልፅላቸውና ያስተነትኑ ዘንድ ቁርአንን አወረድን።”

የቅዱስ ቁርአን አንቀፆች በብዙ ጉዳዮች ላይ ጠቅለል ያለ ውሳኔ ይዘው የመጡ ሲሆን የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) በንግግራቸው ወይም በቁርአን ውስጥ የተናገሩትን በተግባር ሰርተው አብራርተው አስቀምጠዋል።

ለዚህ ምሳሌ ይህ የአሏህ ንግግር ነው፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኑር 56)

“ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ። ምፅዋትንም ስጡ። መልዕክተኛውንም ታዘዙ። ሊታዘንላችሁ ይከጀላልና።”

ሶላት ስገዱ እና ዘካም (ምፅዋት) ክፈሉ የሚለው ጥቅልል ብሎ የመጣ ሲሆን የዚህ ዝርዝር በሱና ውስጥ ተብራርቷል። በሱና ውስጥ የአምስቱ ሶላቶች (ስግደቶች) ወቅት ፣ የስግደቱ አፈፃፀም ሁኔታ እና ስንቆቻቸው እንደ ፆም ፣ የዘካ ስንቆች በግልፅ ተብራርተዋል።

አሏህ የነብዩ ሱና ጠብቆታል

የነብዩ ሱና አሏህ እንደሚጠብቀው ቃል ከገባው የአደራ ተውስታ ውስጥ አንዱ አካል ነው። አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ሒጅር 9)

“በእርግጥ ዚክሩን (አስታዋሹን) ያወረድነው እኛ ነን። በእርግጥም እኛ እንጠብቀዋለን።”

ዚክር የሚለው ቃል አሏህ ለነብዩ ከቁርአን እና ከሐዲስ የገለጠላቸውን ነገር ሁሉ የሚያጠቃልል ስም ነው።

የዚህ ጥበቃ አንዱ መገለጫ የነብዩ ሱና ሐዲስ ለመሰብሰብ ፣ ለመፃፍ ፣ ዘገባውን ትክክለኛነት የሚቆጣጠሩ ህግጋትን ያስቀመጡ ሊቃውንትን ማዘጋጀቱ ነው።

እነዚህ ሊቃውንት የተጨመሩ ውሸት እና ስህተቶችን የመለየት የመቆጣጠር ስራ ሰርተዋል። የዘጋቢዎችን እና የዐስተላላፊዎችን ታማኝነት አጥንተዋልም። ይህንንም በጥሩ መንገድ ጠብቀው አቆይተዋል።

የነብዩን (ሰ.ዐ.ወ) ሱና ለመጠበቅ በተጠቀመባቸው በእነዚያ ዘጋቢዎች እና ሊቃውንቶች አማካኝነት እንደሚጠበቅ ከአሏህ ዘንድ ዋስትና ተሰጥቶታል።

የሱና ትክክለኛነት

የነብዩ ሱና ከቅዱስ ቁርአን ቀጥሎ ሁለተኛው የህግ ምንጭ ሲሆን የሃያሉ አሏህ ሃይማኖት የተሟላ አይሆንም መጽሐፉን (ቁርአን) እና ሱናን ጎንለጎን አድርጎ በመያዝ ቢሆን እንጅ።

ሱና ህጋዊ ውሳኔዎችን ለማግኘት አስፈላጊ እና ወሳኝ ምንጭ ነው። በእምነት እና በህግ ውሳኔዎች ላይ መተግበር አለበት።

ሱና የቅዱስ ቁርአን ድንጋጌዎችን ሊያብራራ ይችላል። እንዲሁም እራሱን ችሎ ፍርዶቹን ለማፅደቅ ይመጣል። ልክ እንደ ቁርአን የተፈቀደውን የሚፈቅድ ፣ የተከለከለውን የሚከለክል ነው።

የቅዱስ ቁርአን እና የነብዩ ሐዲሶች ማስረጃ በእስልምና ህግጋት ውስጥ ያለውን ደረጃ እና ቦታ የሚያረጋግጡ ናቸው። ብዙ አያት (አንቀፆች) እና ሐዲሶች ሱናን አጥብቆ መያዝን የሚያዙ እና ሙስጦፋን መታዘዝ ግዴታ መሆኑን የሚያሳዩ ማስረጃዎች አሉ። አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ሐሽር 7)

“መልዕክተኛው የሠጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙ። የከለከላችሁንም ነገር ሁሉ ተከልከሉ።”

አል-ሙቀደም ኢብን መስኡድ የክሪብ አል-ኪንዲ እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ኢብን ማጃ 12)

‹‹አንድ ሰው መከዳ (አልጋ መሰል) ላይ ጋደም ይልና እንዲህ ይላል፡ ‹‹በእኛ እና በእናንተ መካከል ያለው የአሏህ መጽሐፍ ነው። በእሱ ውስጥ ያገኘነው ፈቅደነዋል። በውስጡ ተከልክሎ ያገኘነውን ደግሞ ከልክለናል። ልክ እንደ አሏህ ክልከላ ሁሉ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ክልከላዎችን አድርገዋል።››

0%
2
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ቁርአን እና ሐዲስ

እነዚህን የተዘነጉ የነብዩ ሱናዎች ያውቁ ኖሯል?

ከእነዚህ የተዘነጉ የነብዩ ሙሐመድ ሱናዎች መካከል ጥቂቶቹን ያውቃሉ?
ከዚህ በታች ያሉትን ጥያቄዎች ይመልሱና ምን ያህሉን በትክክል መመለስ እንደሚችሉ እራስወን ይፈትሹ። እየተማሩ እንዲሄዱም ስለእነዚህ የሱና ዒባዳዎች (አምልኮአዊ ድርጊቶች) የሚናገሩ ጥቂት ሐዲሦችን አካትተናል።

1 / 12

Bookmark question icon

1 ነብዩ በፈጅር የሱና ጸሎት ሁለት ረከዓዎች ውስጥ የትኞቹን ሱራዎች መቅራት (ማንበብ) ይመርጡ ነበር?

2 / 12

Bookmark question icon

2 ነብዩ ‘በሕዝቦቼ ላይ መከበድ ባይሆን ኖሮ ባዘዝኳቸው ነበር’ ያሉት የትኛውን የአምልኮ ተግባር ነው?

3 / 12

Bookmark question icon

3 ከሚከተሉት ውስጥ በየቀኑ ከሚሰገዱት 12 በጣም ከጸደቁ ሱናዎች (ሱና ሙአከዳህ) የማይመደበው የትኛው ነው?

4 / 12

Bookmark question icon

4 ነብዩ ከአንድ ሰው ጋር ለመነጋገር በተዘጋጁ ጊዜ:

5 / 12

Bookmark question icon

5 ነብዩ ይተኙ የነበረው:

6 / 12

Bookmark question icon

6 ነብዩ (መጠጥ) በሚጠጡበት ጊዜ ስንት ጊዜ እያቋረጡ (በስንት ትንፋሽ) ነበር የሚጠጡት?

7 / 12

Bookmark question icon

7 ነብዩ የቀረበላቸውን ምግብ ባይወዱት ኖሮ፣ ምላሻቸው ምን ይመስል ነበር?

8 / 12

Bookmark question icon

8 አቡ ሁረይራህ  የነብዩን የአረማመድ ፍጥነት ሲገልጹ፣ እንዲህ ይመስል ነበር ብለዋል:

9 / 12

Bookmark question icon

9. ነብዩ ቤታቸው ውስጥ በሚሆኑበት ጊዜ:

10 / 12

Bookmark question icon

10 ነብዩ ሰውን በጨበጣ እጅ ሰላም በሚሉበት ጊዜ:

11 / 12

Bookmark question icon

11 ነብዩ ማንኛውንም ልብስ በሚለብሱበት ጊዜ:

12 / 12

Bookmark question icon

12 ከሚከተሉት ተግባራት መካከል ነብዩ ያልተሳተፉበትና ተከታዮቻቸውም እንዲያደርጉት ያላበረታቱት የትኛው ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 40%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

ሱና መከተል

አሏህ ባሮቹ መልዕክተኛውን እና ሱናቸውን ፣ ንግግራቸውን ፣ ስራቸውን የህይወት ሁኔታ እንዲከተሉ ደንግጓል።

በብዙ የቁርአን አንቀፆች የነብዩን መንገድ እንድንከተል አሏህ አዞናል። የሚከተለው አንቀፅ ከእነሱ አንዱ ነው።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ሐሽር 59፡7)

መልዕክተኛው የሰጣችሁን ያዙ፤ የከለከላችሁን ተው። አሏህን ፍሩ በእርግጥ አሏህ ቅጣቱ ብርቱ ነው።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለሶሃባዎቻቸው ሱናቸውን ያስተምሩ ነበር። እንዲከተሉትም ይገፋፏቸው ነበር። ረዘም ባለው ሐዲሳቸው በአንድ ወቅት እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪና ሙስሊም)

“ሱናየን እና በትክክል የተመሩትን ኸሊፋዎች ሱና አጥብቃችሁ ያዙ።” (ትርሚዚ) የሱና ተቃራኒ ቢድአ(በአምልኮት ላይ መፈላፈስ፣ ፈጠራ) ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አሉ፡ “በእዚህ በእኛ ጉዳይ የሆነን ነገር የፈጠረ ከእኛ አይደለም እሱ ተመላሽ ነው።” ብለዋል።

አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ኢምራን 31)

“አሏህ የምትወዱ እንደሆናችሁ ተከተሉኝ በላቸው። አሏህም ይወዳችኋል። ወንጀላችሁን ይምርላችኋል። በእርግጥ አሏህ አዛኝ መሃሪ ነው።”

አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አዕራፍ 158)

“ትመሩ ዘንድ ቅንን መንገድ ተከተሉ።”

ኢርባድ ቢን ሰሪያህ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(አቡዳውድ 4607)

‹‹ሱናየን እና በትክክል የተመሩትን ኸሊፋዎችን ተከተሉ። ይህንንም በመንጋጋ ጥርሳችሁ ነክሳችሁ (አጥብቃችሁ) ያዙት። ቢድአ (ፈጠራን በኢስላም) ተጠንቀቁ፤ ሁሉም ፈጠራ ቢድአ ነው፤ ሁሉም ቢድአ ደግሞ ጥመት ነው።››

መከተል ማለት የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) የተናገሩትን ፣ የሰሩትን እና የኖሩበትን መንገድ መከተል ነው። ትዕዛዛቸውን መታዘዝ ፣ የከለከሉትን መከልከል ፣ የአምልኮ ተግባራትን በእሳቸው መንገድ መስራት እና መረተግበር ነው።

መከተል (መታዘዝ) ከግዴታዎች ውስጥ አንዱ ግዴታ እና ከሚወደዱት ውስጥም አንዱ የሚወደድ ተግባር ነው።

ሱና የመከተል ትሩፋት

ሱናን መከተል ብዙ ጥቅሞች እና ፍሬዎች አሉት። እነሱም

አብዱሏህ ቢን አምር እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ትርሚዚ 2641)

‹‹የእስራኢል ልጆች የደረሰባቸው ነገር በእኔ ኡመት ላይ ይደርስባቸዋል። ኮቴ በኮቴ (እግር በእግር) ይከታተላሉ። አንድ ሰው በግልፅ ከእናቱ ጋር ቢገናኝ ከእኔ ኡመት (ህዝቦች) ያን የሚያደርግ ይኖራል። በእርግጥ የእስራኢል ልጆች በ72 ቡድን ተከፋፈሉ። የእኔ ኡመት በ73 ቡድን ተቧድነው ይከፋፈላሉ። ሁሉም የእሳት ናቸው አንዷ ቡድን ስትቀር አሉ። ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! የትኛዋ ናት? አሉ (ሶሃቦች)። እሳቸውም፡ ‹‹እኔ እና ሶሃቦቼ ያለንባት ናት አሉ።››

ሱናን አጥብቆ መያዝ መመራትን የሚያስገኝ እና ከጥመት የሚታደግ ነው። አሏህ አንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አዕራፍ 158)

ትመሩ ዘንድ ተከተሉት።

አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(የአል-ሐኪም ሙስተድረክ 319)

‹‹ሁለት ነገሮችን ትቼላችኋለሁ፤ እነሱን ከያዛችሁ አትጠሙም። እነሱም የአሏህ መጽሐፍ እና የእኔ ሱና ናቸው።››

የአንድ ስራ ተቀባይነት የሚወሰነው ከሱና ጋር የሚስማማ ከሆነ ነው። አንድ የአሏህ ባሪያ የሚሰራው ስራ በነብዩ ሱና መሰረት መሆን አለበት። አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም 1718)

‹‹ከእኛ ትዕዛዝ ውጭ የሆነን ስራ የሰራ ሰው እሱ (ስራው) ተመላሽ ነው (ተቀባይነት የለውም)።››

ሱናን መከተል ማለት ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መጠጋት ነው። ከሱና የሸሸ ሰው፤ ከነብዩ ሸሽቷል። አነስ ቢን ማሊክ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ሶስት ወንዶች ስለ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የአምልኮ ሁኔታ ሊጠይቁ ወደ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶች ቤት መጡ። ስለዛ በተነገራቸው ጊዜ የእራሳቸው አምልኮ አንሶ ታያቸው።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያለፈው እና መጭው ወንጀላቸው ሁሉ ተምሮላቸው ሳለ (ይህን ካደረጉ) ታዲያ እኛ ከነብዩ አንፃር የትነው ያለነው? አሉ። ከእነሱም አንደኛው ‹‹የሌሊት ሶላት ዘላለም እሰግዳለሁ›› አለ። ሌላኛው ደግሞ ‹‹አመቱን ሙሉ እፆማለሁ፤ ፆሜንም አልፈታም›› አለ።

ሶስተኛው ደግሞ ‹‹ከሴቶች እርቃለሁ ለዘላለምም አላገባም›› አለ። የአሏህ መልዕክተኛ ወደ እነሱ መጡና ‹‹እንትን እንትን ያሉት ሰዎች እናንተው እራሳችሁ ናችሁን? አሉ። በአሏህ ይሁንብኝ! ከእናንተ በላይ አሏህን እፈራለሁ ነገርግን እፆማለሁ፤ ፆምን እፈታለሁ ፣ እሰግዳለሁ፤ እተኛለሁ ፣ ሴቶችንም አገባለሁ አሉ። ከሱናየ የራቀ ሰው ከእኔ አይደለም አሉ።›› (ቡኻሪ 5063)

ሱናን መከተል ከፈተና እና ከሳማሚ ቅጣት ያድናል። አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኑር 63)

እነዚያ ትዕዛዙን የሚጥሱ መከራ አይደርስባቸውም፤ አሳማሚ ቅጣት እንዳያገኛቸው ይጠንቀቁ።

ሱናን መከተል እና መፈፀም በሁሉም ዳር (ቤት-ሐገር) ስኬት እና ደስታን ያስገኛል። አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኑር 52)

“አሏህ እና መልዕክተኛውን የሚታዘዝ ሰው ፣ አሏህንም የሚፈራ እና የሚጠነቀቅ ሰው፤ እነዚያ ፍላጎታቸውን የሚያገኙ ናቸው።”

0%
2
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ቁርአን እና ሐዲስ

ጥያቄና መልስ፡ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና

የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና ትምህርት ፈተና 7 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 6 ጥያቄዎችን በትክክለ መመለስ አለባችሁ።

1 / 7

Bookmark question icon

1 ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተገለጠላቸው ራዕይ ምን እና ምን ያጠቃልላል?

2 / 7

Bookmark question icon

2 ሱና በህግ ድንጋጌዎች ውስጥ ያለ ሃሳብ ነው። ሆኖም ልክ እንደ ቁርአን ሁሉ በእሱ መሰረት መስራት ግዴታ ነው።

3 / 7

Bookmark question icon

3 አሏህ የሐዲሶችን ጥናት በሚከታተሉ ሊቃውንት አማካኝነት ሱና ተጠብቆ እንዲቆይ አድርጓል።

4 / 7

Bookmark question icon

4 ሱና _____ ነው

5 / 7

Bookmark question icon

5 ሱናን የመከተል ጥቅሞች እና ፍሬዎች የሆኑት የትኞቹ ናቸው?

6 / 7

Bookmark question icon

6 አንድ ሙስሊም ሰው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) መከተል አይገደድም።

7 / 7

Bookmark question icon

7 ሁለተኛው የእስልምና ህግ ምንጭ ምንድን ነው?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 43%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

ቢድአ ፈጠራ በእስልምና ተመልከቱ

Related posts

ሐዲሰል ቁድሲ

ሐዲሰል ቁድሲ

ሐዲሰል ቁድሲ (ቅዱስ ወይም መለኮታዊ ንግግር) ማለት ትርጉሙ ከአሏህ የሆነ፤ የቃላት አቀማመጡ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሆነ ንግግር ነው። የሚከተለው ሐዲስ የሐዲሰል ቁድስ አንድ ማሳያ ምሳሌ ነው።

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share