የእስልምና ሊቃውንት የነብዩ ሱና መዝግቦ እና ጠብቆ በማቆየት ፣ ትክክለኛው ከደካማው በመለየት ፣ የዠጋቢዎችን ታማኝነት በማጥናት እድሚያቸውን ለዚሁ አላማ ሰጥተው ኖረዋል።
በዚህ ትምህርት ውስጥ ሱናን በፅሁፋ ላይ ማስፈር ምን እንደሆነ ፣ ደረጃዎቹን እና በጣም ወሳኝ የሚባሉ የሱና መጽሐፍት ትማራላችሁ።
የጽሁፉ አላማ
- የነብዩ ሱና የመፃፍ ደረጃዎችን ታውቃላችሁ
- የታወቁ ወሳኝ የሐዲስ መጽሐፍት ታውቃላችሁ
- የአንድን ሐዲስ ትክክለኛነት እና ደካማነት እንዴት ማወቅ እንደምትችሉ ትረዳላችሁ
የእስልምና ሊቃውንቶች ሱናን በመፃፍ እና ጠብቆ በማቆየት ፣ ትክክለኛውን ከደካማው በመለየት ፣ የዘጋቢዎችን ታማኝነት በማጥናት እድሜያቸውን ለዚሁ አላመ ሰጥተው ኖረዋል።
የነብዩን ሱና በፅሁፍ የማስፈር ትርጉም
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በንግግር ፣ በስራ እና በዘገባ ያስተላለፉትን ነገር ሁሉ መፃፍ ፣ መመዝገብ እና በመጽሐፍ መልክ ማሰባሰብ ነው።
የነብዩ ሱና እና ሐዲሶች በመጽሁፍ የማስፈር ሂደት የተለያዩ ደረጃዎችን ያልፋል። እነሱም፡-
- የመጀመሪያው ደረጃ፡ በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና በሶሃቦች ጊዜ መፃፉ
- ሁለተኛው ደረጃ፡ የሐዲስ በፅሁፍ የማስፈር ሂደት በታቢኦች ዘመን ፣ መጨረሻ ላይ
- ሶስተኛው ደረጃ፡ ሱናን በመጽሐፍ መልክ የማሰባሰብ ሂደት
- አራተኛው ደረጃ፡ ከሌሎች ንግግሮች ጋር ሳይቀላቀል የነብዩን ሐዲሶች ብቻ ነጥሎ የመሰብሰብ እና የማደራጀት ሂደት
የመጀመሪያው ደረጃ
በነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እና በሶሃቦች ዘመን ሐዲስን በጽሁፍ የመሰነድ ስራ የጀመረው በመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ዓ.ሂ ነው።
ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሳቸው ከቁርአን ጋር እንዳይቀላቀል በመፍራት እንዳይፃፍ ከልክለው ነበር።
አቡ ሰኢድ አልሁድሪ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ሙስሊም 3004)
‹‹ከእኔ ምንም ነገር አትፃፍ። ከቁርአን በቀር ከእኔ ማንኛውንም ነገር የፃፈ ሰው፤ ያጥፋው። በቃሉም ይተርክ። በእሱ ላይ ጥፋት የለበትምና። ውሸትን ወደ እኔ ያስጠጋ ሰው (ሆንብሎም ብለዋል) በእርግጥ መኖሪያውን የጀሐነም እሳት ውስጥ ይፈልግ ብለዋል።››
ሆኖም የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶች ተጠብቀው የቆዩት እና የተላለፉት በቃል ትረካ ነው። ከዚያም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የተወሰኑ ሶሃቦች እንዲፅፉ ፈቀዱላቸው።
አብዱሏህ ቢን አምር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሰማሁትን ሁሉንም እፅፍ ነበር፤ ከእሱ ለመሸምደድ አስቤ። ቁረይሾች ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ አንዳንዴ በቁጣ አንዳንዴ በደስታ የሚናገር የሰው ልጅ ሆኖ ሳለ ከእሱ የሰማሃውን ሁሉ ትፅፋለህን? ሲሉ ከለከሉኝ። ከዚያም መፃፌን አቆምኩና ለአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ስለ ነገሩ ገለፅኩላቸው። እሳቸውም በጣታቸው ወደ አፋቸው እየጠቆሙ ‹‹ነፍሴ በእጁ በሆነችው ይሁንብኝ! ከእሱ የሚወጣው እውነት ብቻ ነው›› አሉ።›› (አቡዳውድ 3646)
በአል-ወሊድ ቢን ሙስሊም ሐዲስ ውስጥ አል-አውዘይ እንዳስተላለፈው አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዲህ አለ፡ አሏህን ካላቁ በኋላ ‹‹አሏህ መካ ውስጥ መፋለምን ከልክሏል። ለመልዕክተኛው እና ለምዕመናን በእሷ ላይ ስልጣንን ሰጥቷል።
ከእኔ በፊት ለማንኛውም ሰው መፋለም አልተፈቀደም፤ ከቀኑ በተወሰነው ክፍል ብቻ ለእኔ ተፈቀደልኝ። ከእኔም በኋላ ለማንም አይፈቀድም። ያደን እንስሳት ሊሳደዱ አይገባም። እሾሃማ ቁጥቋጦዎቿ መነቀል የለባቸውም።
በውስጧ ወደቀን ነገር ማንሳት አይፈቀድም፤ ለእሱ (ለሚያነሳው ነገር) ለሰዎች ያሳወቀ ቢሆን እንጅ። ዘመዶቹ የተገደሉበት ሰው ካሳን የመቀበል ወይም አፀፋውን የመመለስ (የመበቀል) ምርጫ አለው። አል-አባስ አለ ‹‹አል-ኢዝሂር በቀር፤ ምክኒያቱም ይህን የምንጠቀመው በመቃብሮቻችን እና በቤቶቻችን ውስጥ ነውና›› አለ።
የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ‹‹አቡሻህ ፃፈው›› አሉ። (ንዑስ ተራኪው አል-አውዘኢን ጠየቀው) የአሏህ መልዕክተኛ ፃፈው? ያሉት ያሉት ምን ለማለት ነው አለ። እሱም ሲመልስ ‹‹ከአሏህ መልዕክተኛ የሰማውን ንግግር ነው›› አለ። (ቡኻሪ 2434 ፣ ሙስሊም 1355)
ሁለተኛው ደረጃ
ሐዲስን በፅሁፍ ላይ የማስፈር (የመሰነድ) ስራ የተከናወነው በሁለተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አመተ ሂጅራ በታቢኦች ዘመን ማብቂያ ነው። ይህ ጽህፈት የሚታወቀው የነብዩ ሱና ጥቅል ጽህፈት በመሆኑ ነው።
ነገርግን የተለየ አቀማመጥ አልነበረውም። ያ ያሳሰበው የመጀመሪያው ሰው የሙዕሚኖች (የአማኞች) መሪ (አሚር) የሆነው ኡመር አብዱል አዚዝ (ረሂመሁሏህ) ነው።
ሆኖም ሁለቱን ኢማሞች ሺሃብ አዙሁሪ እና አቡበክር ቢን ሃዝም ሱናውን እንዲሰበስቡ አዘዛቸው።
ከዚያም የሚከተለውን ለተለያዩ ሐገራት ፃፈ፡ ‹‹የሐዲስ እውቀት እንዳይተፋ በመፍራት እና የሌሊቱን መሞት አሳስቦኝ የአሏህ መልዕክተኛን ሐዲስ አሰባስቤ መዝግቤዋለሁ።››
ስለዚህ ሐዲሱን በትዕዛዙ መሰረት የፃፈው የመጀመሪያው ኢማሙ አዝሁሪ (ረሂመሁሏህ) ነው። ይህ ደግሞ የሱና እና የሐዲሶች አጠቃላይ መጽሐፍ ጅምር ነው።
ሶስተኛው ደረጃ፡ የሱና ጥንቅር በኢማን ፣ እውቀት ፣ ንፅህና ፣ ሶላት ወዘተ በሚሉ ርዕሶች ተከፋፍሎ እና በደንብ ተደራጅቶ በመጽሐፍ መልክ የተሰነደበት ነው።
በዚህ ደረጃ፡ ኢማሙ ማሊክ ቢን አነስ (ረሂመሁሏህ) ሙወጧዕን ያዘጋጁበት ነው። ይህ ደረጃ የሚታወቀው የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ንግግሮች ከሰሃቦች እና ከታቢኦች ንግግር እና ፈትዋ ጋር የተደባቁበት በመሆኑ ነው።
አራተኛው ደረጃ
ይህ ደረጃ የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶች በመከፋፈል ፣ በመሰብሰብ እና ከሶሃቦች እና ከታቢኦች ንግግር ጋር ሳይቀላቀል (ከሚያስፈልገው ከተወሰነው በቀር) የተደራጀበት እና የተሰነደበት ጊዜ ነው።
ሐዲሱን በፅሁፍ ላይ የማስፈር ስራ ግቡን የመታው በሶስተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ነው።
ኢማሙ አል-ቡኻሪ ሰሂህ ቡኻሪን ፣ ኢማሙ ሙስሊም ሰሂህ ሙስሊም እና ከሱነን መጽሐፍት ደግሞ ሱነን አቡዳውድ ፣ ትርሚዚ ፣ ነሳኢ ፣ ኢብን ማጃ ፣ ሱነን ዳርሚ እና ሌሎች ታዋቂ የሐዲስ መጽሐፍት የተዘጋጁበት ወቅት ነው።
አስፈላጊ እና ወሳኝ የሱና መጽሐፍት (ኪታብ)
ከብዙ የነብዩ ሱና ኪታቦች መካከል ስድስቱ ታዋቂዎች ናቸው። እነሱም ሰሂህ ቡኻሪ ፣ ሰሂህ ሙስሊም ፣ ሱነን አቡዳውድ ፣ ኢብን ማጃ ፣ ነሳኢ እና ትርሚዚ ናቸው።
ከሱነን የሱና መጽሐፍት ታዋቂ የሆኑት ደግሞ አል-ዳሪሚ ፣ ሙሰነድ ኢማሙ አህመድ እና ሙወጧ ኢማሙ ማሊክ ናቸው።
የስድስቱ መጽሐፍት መግቢያ
ህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያገኙት የሡና ኪታቦች መካከል ስድስቱ መጽሐፍት ይጠቀሳሉ። እነሱም፡-
- ሰሂህ አል-ቡኻሪ (የሞተው 256ዓ.ሂ)
ፀሐፊው ከአሏህ መልዕክተኛ የደረሰውን ኢማን ፣ የአምልኮ ተግባራት ፣ ግብይት ፣ ጦርነት ፣ ትርጉም እና ትሩፋቶች ወ.ዘ.ተ በሚሉ ይዘቶች መልክ የተደራጀ ሰፊ እና ሁሉን አቀፍ ከሆኑ የሐዲስ መጽሐፍት ውስጥ አንዱ ነው።
- ሰሂህ ሙስሊም (የሞተው 261ዓ.ሂ)
በይዘታቸው ሰፊ እና ሁሉን አቀፍ ከሆኑ የሐዲስ መጽሐፍት ውስጥ አንዱ ሲሆን ፀሐፊው የሐዲሶችን ትክክለኛነት ላይ ትኩረት አድርጎ ሰርቷል።
ነገርግን እሱን ለማስተካከል ከተጠቀመጡ ቅድመ ሁኔታዎች አንፃር ሲታይ ከቡኻሪ ቀለል ይላል። በዚህም ምክኒያት ከቡኻሪ ቀጥሎ ሁለተኛው መጽሐፍ ነው።
- ሱነን አቡዳውድ (የሞተው 275ዓ.ሂ)
‹‹ሱነን›› ተብለው ከሚጠሩ መጽሐፍት ውስጥ አንዱ ነው። ምክኒያቱም ጽሐፊዎቻቸው ያዘጋጇቸው ከፊቅህ ጋር በተያያዘ ነውና። ፀሃፊው በመጽሐፍ ውስጥ ሰሂህ እና ሐሰን እና ጥቂት ደካማ ሐዲሶች አካቷል።
- ሱነን ትርሚዚ (የሞተው 279ዓ.ሂ)
ሰፊ የሐዲስ ስብስብ ከያዙ መጽሐፍት ውስጥ አንዱ ነው። በዚህ መጽሐፍ ጸሐፊው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሐዲሶችን እምነት ፣ የአምልኮ ተግባራት ፣ ግብይቶች ፣ ጦርነቶች ፣ የትርጉም ማብራሪያ ፣ ትሩፋቶች በሚሉ ርዕሶች አደራጅቶ ሰንዷል።
ነገርግን ሰሂህ (ትክክለኛ) ሐሰን (ጥሩ) ዶኢፍ (ደካማ) ሐዲሶች ቢኖሩም ፀሐፊው ሰሂህ ሐዲሶች ላይ ትኩረት አላደረገም።
- ሱነን ነሳኢ (የሞተው 303ዓ.ሂ)
ይህ የሐዲስ ስብስብ መጽሐፍ ከፊቅህ ጋር በተያያዘ በምዕራፎች ተከፋፍሎ እና ተደራጅቶ የጠዘጋጀ ነው። በውስጡም ሰሂህ (ትክክለኛ) ፣ ሐሰን (ጥሩ) እና ዶኢፍ (ደካማ) ሐዲሶችን ይዟል።
- ሱነን ኢብን ማጃ (የሞተው 273ዓ.ሂ)
ይህ የሐዲስ ስብስብ መጽሐፍ ከፊቅህ ጋር በተያያዘ በምዕራፎች ተከፋፍሎ እና ተደራጅቶ የተዘጋጀ ነው።
መጽሐፌ ሰሂህ ፣ ሐሰን እና ዶኢፍ ሐዲሶችን አካቶ ይዟል። ነገርግን ዶኢፍ (ደካማ) ሐዲሶቹ ይበዛሉ።
ኢማሙ ሐፊዝ አቡ አል-ሐጃጅ አል-ማዚ (የሞተው 742ዓ.ሂ) እንዲህ ብሏል፡-
ሱናን በተመለከተ አሏህ አዋቂ ሸምዳጆችን (ሃፊዞችን) ፣ እውቅ ሊቃውንትን ፣ በገንዘባቸው የሚለውጡ የሆኑን ሰጥቶታል።
በዚህም በአክራሪዎች እንዳይበረዙ ፣ እንዳይቀየር ፣ ካላዋቂዎች ትርጉም እና ስህተት እንዲፀዳ በማድረግ አሏህ ጠብቆ አቆይቶታል።
እንዳይጠፋ እና ጠብቆ ለማቆየት በማሰብ በብዙ መንገዶች ከፋፍለው እና አደራጅተው በፅሁፍ መልክ ሰንደው አስቀምጠዋል።
በአከፋፈሉነ እፁብ ድንቅ ፣ በአዘገጃጀቱ ረቂቅ ፣ በጣም ትክክል ፣ በጣም ጠቀሚ እና በበረካው ከሁሉም በላይ የላቀ በግኝቱ በጣም ቀላል ፣ የተስማሙበትም ሆኑ ያልተስማሙበት ሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለው እና በሁሉም ሁኔታዎች ውስጥ የላቀ ደረጃ ያለው ነው።
እነዚህ ትክክለኛ የሰነድ ስብስቦች አብዱሏህ ኢብን ኢስማኢል አል-ቡኻሪ ፣ የዐቡ አል-ሁሴን ሙስሊም ኢብን አል-ሃጃጅ አል-ኒሰፑሪ ትክክለኛ ስብስቦች እና ከዚያም ‹‹የአል-ሱነን›› መጽሐፍት በአቡዳውድ ሱለይማን ኢብን አል-ሻአስ አል-ሰጂስታኒ እና ከዚያም ደግሞ ‹‹የአል-ጃሚዕ›› መጽሐፍ በአቡ አብዱረህማን አህመድ ኢብን ሹአይብ አል-ነሳኢ እና ኢብን ማጃ ተብሎ የሚታወቀው አቡ አብዱሏህ ሙሐመድ ኢብን የዚድ መጽሐፍ ‹‹አልሱነን›› ስራዎች ተጠቃሽ ናቸው። ምንም እንኳ ኢብን ማጃ ከሌሎቹ አንፃር ደከም ያለ ቢሆንም ማለት ነው።
እያንዳንዳቸው እነዚህ ስድስት መጽሐፎች በዚህ ጉዳይ ላይ ግንዛቤው ያላቸው ሰዎች ዘንድ በጣም የጣወቁ ሲሆን በእስልም ሐገሮች ተሰራጭተዋል ትልቅ ጥቅም ሰጥዋል።›› (ተህዚቡ አልከማል ጥራዝ 1 ገፅ 147)
ትክክለኛ እና ደካማ ሐዲስን መለየት
አንድ ሙስሊም ሰው የሐዲስን ደረጃ ትክክለኛ ተቀባይነት ያለው ወይም ደካማ ወይም ደግሞ ተቀባይነት የሌለው ነው የሚለው በሐዲስ ጥናት ላይ የተሰማሩ ሊቃውንት ስራ በመመልከት ማወቅ ይቻላል።
በእርግጥ እነዚህ ሊቃውንት ሐዲስን ከአነጋገር ፣ ከዘገባው ሰንሰለት ፣ ተቀባይነት ያለው እና ተቀባይነት የሌለው ስለመሆኑ ያጠኑታል።
በዚህ መንገድ የተፃፉ እና የተደራጁ ብዙ መጽሐፍት አሉ። እንዲሁም ደካማ ሐዲሶችን ከትክክለኛው ለማወቅ እና ለመረዳት የሚያስችሉ ብዙ አስተማማኝ አፕልኬሽኖች እና የመማሪያ መድረኮች አሉ።
የሐዲሶችን ደረጃ ለማወቅ ከሚረዱ አፕልኬሽኖች እና የመማማሪያ መድረኮች መካከል
በመቶ ሽህ የሚቆጠሩ ሐዲሶችን ያካተተው የሐዲስ አውደ-ጥበብ ዱራር አለ-ሱኒ ድህረገፅ ላይ ይገኛል። ከዚህ ሊንክ ማግኘት ይቻላል፡ https://dorar.net/hadith

Share