የቅዱስ ቁርአን ሽልማት

Author picture
የቅዱስ ቁርአን ታላቅነት እና ክብሩን የሚገልፁ ብዙ ትሩፋት አሉት። በዚህ ትምህርት ውስጥ የተወሰኑትን ትማራላችሁ።

የቅዱስ ቁርአን ታላቅነት እና ክብሩን የሚገልፁ ብዙ ትሩፋት አሉት። በዚህ ትምህርት ውስጥ የተወሰኑትን ትማራላችሁ።

የቅዱስ ቁርአን ትሩፋት (ምንዳ)

ቅዱስ ቁርአን የሚከተሉትን ጨምሮ ብዙ ትሩፋቶች አሉት።

1 ቁርአንን ተምሮ የማስተማር ችሮታ

ኡስማን ኢብን አፋን (ሰ.ዐ.ወ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹ከእናንተ መካከል በላጩ ቁርአንን ተምሮ ያስተማረ ነው።›› (ቡኻሪ 5027)

2 የቁርአን ሰዎች የተመረጡ የአሏህ ሰዎች ናቸው። አነስ ቢን ማሊክ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

‹‹በእርግጥ አሏህ ከሰዎች ቤተሰብ አለው። እነሱም (ሶሃቦቹ)፡ ‹‹የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! እነሱ እነማን ናቸው?›› አሏቸው። እሳቸውም አሉ፡ ‹‹እነሱ የቁርአን ሰዎች፤ የአሏህ ቤተሰቦች የእሱ ምርጦች ናቸው።›› (ኢብን ማጃ 215)

3 አንድን የቁርአን ፊደል ማንበብ ብዙ እጥፍ ሽልማት ይዟል። አብዱሏህ ኢብን መስኡድ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

‹‹ከአሏህ ኪታብ አንዲትን ፊደል ያነበበ ሰው መልካም ስራ አለው። መልካም ስራውም በአስር እጥፍ ይባዛል። አሊፍ ላም ሚም አንድ ፊደል ነው አልልም። አሊፍ አንድ ፊደል ፣ ላም አንድ ፊደል ሚም አንድ ፊደል ቢሆን እንጅ።›› (ትርሚዚ 2910)

4 ቁርአን ለማንበብ እና ለማጥናት በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ የመላኢኮች በዙሪያቸው መሆን ፣ ሰላም እና እዝነት በእነሱ ላይ መሆኑ

አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

‹‹በአሏህ ቤት ውስጥ (መስገድ) የአሏህን መጽሐፍ ለማንበብ እና ለማጥናት የሚሰባሰቡ ሰዎች የሉም፤ ሰላም ፣ መረጋጋት እና እዝነት በእነሱ ላይ የሆነ ፣ መላኢካዎች በዙሪያቸው ያካበቧቸው ፣ አሏህ እሱ ዘንድ ባለው ስብስብ መሃል ያወሳቸው ቢሆን እንጅ።›› (ሙስሊም 2699)

5 ቁርአን ለወዳጁ አማላጅ መሆኑ

አቡ ኡማማ አል-ባሂሊ እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ አለ፡ ‹‹ቁርአንን አንብቡ በትንሳኤው ቀን ለወዳጆቹ አማላጅ ሆኖ ይመጣልና።›› (ሙስሊም 804)

6 ቁርአን ከመላኢኮች ጋር መቅራት የተካነ እና ሲያነብ የሚንተባተብ ሰው ሁለት ምንዳ (ሽልማት) አለው

አኢሻ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈችው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹በቁርአን የተካነ (የሰለጠነ) ሰው ከተከበሩት እና ቀጥ ካሉት ነው። ቁርአን ሲያነብ የሚንተባተብ እና የሚከብደው ሰው ለእሱ ሁለት ምንዳ ሽልማት አለው።›› (ሙስሊም 798)

7 ቁርአን ወዳጆቹን ከፍ ያደርጋል

ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ ‹‹በእርግጥ! በዚህ ቁርአን አሏህ ሰዎችን ከፍ ያደርጋል፤ ከፊሉን ደግሞ ዝቅ ያደፈርጋል።›› (ሙስሊም 817)

8 ቁርአንን የሀፈዘ (የሸመደደ) ሰው ከቁርአን በልቡ የያዘውን ያህል ጀነት ውሰጥ ደረጃው ከፍ ይላል

አብዱሏህ ቢን ኡመር ቢን አል-አስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡ “ለቁርአን ወዳጅ እንዲህ ይባላል፡ አንብብ፤ ከፍ በልም። በዱንያ ስታነብ እንደነበረው አንብብ፤ መኖሪያህ በምታነበው የመጨረሻው አንቀፅ ላይ ነውና።” (አቡዳውድ 1464)

0%
13
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ቁርአን እና ሐዲስ

የቁርአን ጥያቄና መልስ

1 / 10

Bookmark question icon

1 ቁርአን የተገለጠው (የወረደው) በስንት ዓመታት ውስጥ ነው?

2 / 10

Bookmark question icon

2 ከነብዩ ሰሃቦች (ባልደረቦች) መካከል በቁርአን ውስጥ በስም የተጠቀሰው ብቸኛው ሰሃባ ማን ነው?

3 / 10

Bookmark question icon

3 በቁርአን ውስጥ “ቢስሚላሂ-ራህማኒ-ራሂም” (በስመ አላህ እጅግ በጣም ሩኅሩኅ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው) ብላ የማትጀምረው ብቸኛዋ ሱራ (ምዕራፍ) የትኛዋ ናት?

4 / 10

Bookmark question icon

4 በቁርአን ውስጥ እያንዳንዱ አንቀጽ (አያህ) “አላህ” የሚለውን ስም የያዘው ሱራ የትኛው ነው?

5 / 10

Bookmark question icon

5 በአጠቃላይ በቁርአን ውስጥ ስንት ሱራዎች አሉ?

6 / 10

Bookmark question icon

6 “ሰጅደቱ-ቲላዋ” (የንባብ ስግደት) በቁርአን ውስጥ በስንት ቦታዎች ላይ ይገኛል?

7 / 10

Bookmark question icon

7 በቁርአን ውስጥ በብዛት የተጠቀሰው ነብይ ማን ነው?

8 / 10

Bookmark question icon

8 በቁርአን ውስጥ በነብይ ስም የተሰየሙ ስንት ሱራዎች አሉ?

9 / 10

Bookmark question icon

9 “አያተል ኩርሲ” (የዙፋኑ አንቀጽ) የሚገኘው በየትኛው የቁርአን ሱራ ውስጥ ነው?

10 / 10

Bookmark question icon

10 ከቁርአን አንድ ሶስተኛ (1/3) ጋር እኩል እንደሆነች የሚነገርላት ሱራ የትኛዋ ናት?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 24%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

9 የቁርአን ባለቤት በትንሳኤው ቀን ልብስ እና የክብር አክሊል ይለብሳል

አቡ ኹረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

“በፍርዱ ቀን ቁርአን ይመጣና ‹‹ጌታየ ሆይ! አስውበው›› ይላል። ከዚያም የክብር አክሊል ይደፋለታል። ይለብሳልም። ከዚያም ‹‹ጌታየ ሆይ! ብዙ ስጠው›› ይላል። ከዚያም የመኳንንት ልብስ ይለብሳል። ከዚያም ‹‹ጌታየ ሆይ! ተደሰትበት›› ይላል። በእሱ (በባሪያው) ይደሰትና ‹‹አንብብ፤ ከፍበልም። በእያንዳንዷ አያም ሽልማትህ ይጨምራል›› ይላል።” (ትርሚዚ 2915)

10 ሃያሉ አሏህ በታላቅ የአክብሮት አይነት ወላጆችን እና የቁርአን ጽሐፊን ያከብራል

ሰሃል ቢን ሙአዝ ከአባቱ ይዞ እንዳስተላለፈው (ረ.ዐ) የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡

‹‹ቁርአንን ያነበበ እና በእሱም የሰራበት ሰው በፍርዱ ቀን ለወላጆቹ አክሊል ይደፋላቸዋል (ይለበሳሉ)። ብርሃኑም ከፀሐይ ብርሃን ይበልጣል። በዱንያ ውስጥከላችው የፀሐይ ብርሃን የበለጠ ብርሃንን ይጎናፀፋሉ።›› (አቡዳውድ 1453)

እናም በዚህ (ቁርአን) ስለሚሰራበት ሰው ምን ታስባላችሁ?

11 ቁርአን መማር እና መሸምደድ ዱንያ እና ዱንያ በውስጧ ከያዘችው ነገር ሁሉ ይበልጣል

ኡቅባ ቢን አምር (ረ.ዐ) እንዳስተላለፈው እንዲህ አለ፡ “በሱፋ ውስጥ ሆነን እያለ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ወጥተው ሄዱ። ከዛም እንዲህ አሉ፡

‹‹ከእናንተ መካከል በየቀኑ ጧት ጧት ወደ ቡሳን እና አል-አቂቅ ሄዶ ሁለት ሴት ግመሎችን ያለ ሃጢያት እና ዝምድናን ሳትቆርጡ ማምጣት የምትፈልጉ ማንኛችሁ ናችሁ? አሉ። እኛም አልን፡ የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! እኛ እንፈልጋለን አልናቸው። እሳቸውም፡ ‹‹ከእናንተ መካከል አንዳችሁ ወደ መስጅድ ሄዶ ከሃያሉ አሏህ መጽሐፍ ለመማር እና ሁለት አንቀፆን ለማንበብ አይሄድም፤ ያ ከሁለት ሴት ግመሎች የሚበልጥ ቢሆን አንጅ። ሶስት አንቀፅ ደግሞ ከሶስት ግመሎች ይበልጣል። አራት አንቀፆ ከአራት ግሞሎች ይበልጣል። እንዲሁ ከግመል እንደ ቁጥራቸው አሉ።” (ሙስሊም 803)

0%
2
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ቁርአን እና ሐዲስ

ጥያቄና መልስ፡ የቅዱስ ቁርአን ሽልማት

‹‹የቅዱስ ቁርአን ትሩፋት›› የሚለው ትምህርት ፈተና 5 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 4 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 5

Bookmark question icon

1 ከሰዎች ሁሉ በላጩ ማን ነው?

2 / 5

Bookmark question icon

2 ቁርአንን ያነበበ ፣ የሸመደደ እና በእሱም የሰራበት ሰው በፍርዱ ቀን አሏህ _______ አክሊልን ያለብሳል።

3 / 5

Bookmark question icon

3 ቁርአን የሚያነብ ሰው መልካም ስራን ይቀበላል፤ መልካም ስራውም በአስር እጥፍ የሚባዛው _____ ነው።

4 / 5

Bookmark question icon

4 ቁርአን የሚያነብ እና ሲያነብ የሚንተባተብ ሰው

5 / 5

Bookmark question icon

5 ሃያሉ አሏህ _______

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 40%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

ሐዲሰል ቁድሲ

ሐዲሰል ቁድሲ

ሐዲሰል ቁድሲ (ቅዱስ ወይም መለኮታዊ ንግግር) ማለት ትርጉሙ ከአሏህ የሆነ፤ የቃላት አቀማመጡ ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የሆነ ንግግር ነው። የሚከተለው ሐዲስ የሐዲሰል ቁድስ አንድ ማሳያ ምሳሌ ነው።

Read More »

የነብዩ ሱና

የእስልምና ሃይማኖት በሁለት ምንጮች ላይ የተመሰረተ ነው። እነሱም ቅዱስ ቁርአን እና የነብዩ ሱና ናቸው። በዚህ ትምህርት ውስጥ ስለ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሱና እውነት እና በኢስላም ውስጥ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share