ኢህራም ሐጅ ወይም ኡምራ ለማድረግ ወይም ደግሞ ሁለቱንም ለማድረግ መነየት ነው። ኒያ (ማሰብ) ለሁለቱም ጠቃሚ ነገር ነው። ምክኒያቱም ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ ባስተላለፈው ሐዲስ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) “የስራዎች ሁሉ ምንዳ መሰረቱ ኒያ (ማሰብ) ነው” ብለዋልና። አንድ ሰው በኢህራም ሁኔታ ላይ በሆነ ጊዜ የሚከተሉትን ነገሮች ማድረግ የለበትም።

- ጥፍርን መቁረጥ
- ፀጉርን መላጨት ፣ መቁረጥ ወይም ሆን ብሎ መንጨት
- ሽቶ መነስነስ እና ሽታ ያለው ሳሙና መጠቀም
- ከትዳር አጋር ጋር ግብረ ስጋ ግኑኝነት ማድረግ
- ለእራስም ይሁን ለሌሎች የጋብቻ ጥያቄ ማቅረብ ወይም ጋብቻ መፈፀም
- የእጅ ጓንት መልበስ (ለሴቶች)
- ራስን በሚነካ ነገር ራስን መሸፈን (ለወንዶች)፤ እራስን የሚነካ ነገር እስካልሆነ ድረስ ጥላ እና ተመሳሳይ ነገር መጠቀም ይቻላል።
- ቲሸርት ፣ ጥምጣም ፣ ጃኬት ፣ ሱሪ ወይም ደግሞ የተሰፋ ልብሶች መልበስ (ለወንዶች) እና ሰንደል ያልሆነ ጫማ መልበስ ለወንዶችም ለሴቶችም
- ፊትን በኒቃብ መሸፈን፤ ወንዶች በዙሪያዋ ካልኖሩ በቀር
- በአደን ማደን
አንድ ሰው በኢህራም ሁኔታ ላይ በሚሆን ጊዜ አሏህ ከከለከለው ነገር ለመራቅ የበለጠ ጥረት ማድረግ አለበት። ሙስሊሞችን በንግግም በስራውም ከመጉዳት መጠበቅ አለበት።




Share