ጠዋፍ ዱአ እያደረጉ ካዕባን የመዞር ተግባር ነው። ከዕባን አንድ ሙሉ ዙር መዞር ሸውት ይባላል። የጠዋፍ ተግባር የሚፈፀመው ካእባን ሰባት ጊዜ በመዞር ነው። ልክ እንደ ሶላት አንዱ የአምልኮ ተግባር ነው።
ጠዋፍ

ጠዋፍ ዱአ እያደረጉ ካዕባን የመዞር ተግባር ነው። ከዕባን አንድ ሙሉ ዙር መዞር ሸውት (ብ.ቁ አሽዋት) ይባላል። የጠዋፍ ተግባር የሚፈፀመው ሰባት አሽዋት በመፈፀም ነው። ወይም ካእባን ሰባት ጊዜ በመዞር ነው። ልክ እንደ ሶላት አንዱ የአምልኮ ተግባር ነው።

ብዙ የጠዋፍ አይነቶች አሉ።

  1. ጠዋፈል ቁዱም (የመድረስ ጠዋፍ)፡ ሐጅ ለማድረግ በማሰብ መካ መስጅደል ሐረም እንደገቡ የሚደረግ የሱና ተግባር ነው።
  2. ጠዋፉል ኢፍዷ፡ ይህ መሰረታዊ ስርአተ ሐጅ ተግባር ሲሆን ሁሉም ሁጃጅ ይህን መፈፀም አለበት። እሱን የተወ ሐጁ ዋጋ የለውም።
  3. ጠዋፈል ወዷእ (የስንብት ጠዋፍ)፡ ሁጃጆች ከመካ ተመልሰው ወደ ቤታቸው ከመሄዳቸው በፊት የሚፈፅሙት የስንብት ጠዋፍ ነው። መካ ውስጥ ለሚኖሩ ሰዎች ይህ ስርአተ ሐጅ ተግባር ግዴታ ነው። የሚተወው ሰው ደግሞ ማካካሻውን  አንድ እንስሳ መስዋዕት ማድረግ አለበት።
  4. ጠዋፍ አተታውእ (በራስ ፈቃድ የሚደረግ ጠዋፍ)፡ መካ ውስጥ በሚቆዩበት በማንኛውም ጊዜ ይህን ማድረጉ ይወደዳል።

ጠዋፍ ለማድረግ ሙስሊሞች ከሁሉም አካላዊ ቆሻሻዎች መፅዳት አለባቸው። ይህን ተግባር ከመፈፀም በፊት ኒያ ማድረግ (ማሰብ) ፣ አውራን መሸፈን ፣ ጠዋፉን ከጥቁሩ ድንጋይ ጀምሮ መጨረስ ያስፈልጋል።

ካዕባ በግራ ጎን በኩል በመሆን ከቀኝ ወደ ግራ አቅጣጫ በመሄድ በካዕባ ዙሪያ ሰባት ጊዜ መዞር ያስፈልጋል። ከካዕባ ውጭ እና በካዕባ ዙሪያ ዙሩ ሳይቋረጥ መፈፀም አለበት። ይህን ለማድረጉ በቂ ምክኒያት ከሌለው በቀር። ካልሆነ ተቀባይነት አይኖረውም።

የጠዋፍ ሱና ተግባራቶች የሚከተሉትን ይይዛል። ከተቻለ ከጠዋፉ መጀመሪያ ላይ ሐጀረል አስወድ (ጥቁር ድንጋይ) መሳም ወይም መንካት ወይም ካልተቻለ ደግሞ አሏህ አክበር በማለት በእጅ መጠቆም ፣ የየመኒ ጠርዝ መንካት እና በእያንዳንዱ የጠዋፍ ዙር ሐጀረል አስወድን መሳም ፣ ጠዋፍን ከጨረሱ ቡኋላ ከተቻለ ከመቃመ ኢብራሂም (ከኢብራሂም ስፍራ) ጀርባ ሆኖ ሁለት ረከአ መስገድ ፣ ካልተቻለ ግን እዛው መስጅድ ውስጥ ማንኛውም ቦታ ላይ መስገድ ይቻላል።

በሶላቱ በመጀመሪያው ረከአ ሱረቱል ካፊሩን መቅራት እና በሁለተኛው ረከአ ደግሞ ሱረቱል ኢህላስን መቅራት ናቸው።

ጠዋፍ ብዙ ጥቅሞች አሉት። ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ትርሚዚ)

“አንድ ሰው (በጠዋፍ ወቅት) እግሩን ወለሉ ላይ በሚያነሳበት እና በሚያሳርፍበት በእያንዳንዷ እርምጃ ልክ ወንጀሉ ይማርለታል፤ መዝገቡም ላይ ምንዳው ይፃፍለታል።”

ሐጅ ፣ ኡምራ እና መስጅደል ሐረምን ተመልከቱ

Related posts

የተውሒድ በይድ

“የተውሒድ በይድ” ቢላን ሱም በስልጥኘ አፍ በደኑሪ ሙሰ የትስናጄይ ክታብ ያለሃነ ሀድነተ በሱትዋ በቀሊሎ ኡንገ ለቻሎትዋ ለትፈሀሞት ጥሽተ ያትኬሻነን ክታብ። የክታበይ ሱመ “የተውሒድ በይድ” የባሉዪ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share