ሰኢ ከካዕባ በስተ ሰሜን እና በደቡብ በኩል በሚገኙት የሶፋና መርዋ አለታማ ኮረብታዎች መከካከል ሰባት ጊዜ መመላለስ ሲሆን የሐጅ እና የኡምራ ግዴታ ተግባር ነው።
ሰኢ

ሰኢ ከካዕባ በስተ ሰሜን እና በደቡብ በኩል በሚገኙት የሶፋና መርዋ አለታማ ኮረብታዎች መከካከል ሰባት ጊዜ መመላለስ ሲሆን የሐጅ እና የኡምራ ግዴታ ተግባር ነው። ሰኢ የነብዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) ሚስት የሆነችው ሐጀር ባሏ ጭር ያለ በረሃ ላይ እሷና ልጇን ነብዩ ኢስማኤል (ዐ.ሰ) ትቷቸው በሄደ ጊዜ የልጇን ጥም ለመቁረጥ ውሃ በመፈለግ በኮረብታዎቹ መሃል የተመላለሰችበትን ክስተት ያስታውሰናል። አሏህ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል በቀራ 2፡158)

በእርግጥ ሶፋና መርዋ ከአሏህ ተአምራቶች መካከል ናቸው።

 የሶፋና መርዋ አለታማ ኮረብታዎች

ሰኢ በሶፋና መርዋ መካከል ሰባት ጊዜ የመመላለስ ተግባር ነው። አንደኛው ዙር የሚጠናቀቀው ከሶፋ በመጀመር መርዋ ላይ በመጨረስ ሲሆን ከመርዋ ወደ ሶፋ ሲመለሱ ደግሞ ሁለተኛው ዙር ይጠናቀቃል። ሌሎቹ ዙሮችም እንደዚሁ ይፈፀማሉ።

መስጅደል ሐረም

ሰኢ የሚፈፅመው

  1. ለኡምራ ከጠዋፍ ቡኋላ
  2.  ከጠዋፈል ቁዱም በኋላ እና
  3. ከጠዋፈል ኢፍዷ

ከላይ ላለው ለ1ኛው እና ለ2ኛው በኢህራም ሁኔታ ላይ መሆን ያስፈልጋል። ለ3ኛው ግን ኢህራም አያስፈልግም። እራስን ከመላጨቱ ወይም ፀጉርን ከማሳጠር በፊት የተፈፀመ ካልሆነ በቀር።

አንድ ሑጃጅ ሰኢ ሲያደርግ ከሶፋ ጀምሮ መርዋ ላይ መጨረስ አለበት። የማይረባ ከንቱ ንግግርን እና ማንኛውንም አይነት ንግድ ወይም ግብይት መፈፀም አይገባም። ይልቁንም የተለያዩ የኢባዳ አይነቶችን አብዝቶ ሊፈፅም ይገባል።

ለምሳሌ ዱአ ፣ ዚክር ፣ ተስቢህ እና ቅዱስ ቁርአን መቅራት ወ.ዘ.ተ ድምፅን ከፍ ማድረግ ወይም ሌሎችን መጉዳት አይገባም። ከተቻለ ወንዶች በአረንጓዴ መብራቶቹ መካከል በፍጥነት መጓዝ ይኖርባቸዋል።

ሶፋ እና መርዋ

ንፅህና (ጦሃራ) ለሰኢ ቅድመ ሁኔታ አይደለም። ሆኖም የወር አበባ ላይ የሆነች ሴት ሰኢ መፈፀም ትችላለች። በእርግጥ በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ከማድረግ በቀር ሁሉንም የሐጅ ስርአት መፈፀም ትችላለች። ንፁህ በሆነች ጊዜ ወይም የወር አበባዋ በቆመ ጊዜ ደግሞ ጠዋፍ ማድረግ ትችላለች።

ለጀመአ ሶላት ሰኢው መቋረጥ አለበት። ይሁንእንጅ ሶላቱ ካበቃ በኋላ ሰኢውን ካቆመበት ቦታ መቀጠል ይኖርበታል።

ጠዋፍ ፣ ሐጅ እና ኡምራ ተመልከቱ

Related posts

የተውሒድ በይድ

“የተውሒድ በይድ” ቢላን ሱም በስልጥኘ አፍ በደኑሪ ሙሰ የትስናጄይ ክታብ ያለሃነ ሀድነተ በሱትዋ በቀሊሎ ኡንገ ለቻሎትዋ ለትፈሀሞት ጥሽተ ያትኬሻነን ክታብ። የክታበይ ሱመ “የተውሒድ በይድ” የባሉዪ

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share