ጁምአ ወይም አርብ የሳምንቱ ምርጥ ቀን ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በሙስሊም በተዘገበው ሐዲስ እንዲህ ብለዋል፡-
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ሙስሊም)
“ፀሐይ ከወጣችበት ሁሉ በላጩ ምርጡ ቀን ጁምአ ነው። በዚያ ቀን አደም ተፈጥሯል፤ ጀነት ገብቷል እናም በዚያው ቀን ከጀነት ተባሯል። ሰአቷ የምትቆመው በጁምአ ቀን ነው።”

ሙእሚኖች የጁምአ ሶላት እንዲሰግዱ አሏህ አዟቸዋል።
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ጁሙዓ 62፡9)
“እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በአርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ አሏህን ለማውሳት ኑ። መሸጥ መለወጣችሁንም ተው። ይህ የምታውቁ ብትሆኑ ለእናንተ የተሸለ ነው።”
ይህ የቁርአን አንቀፅ እንደሚያሳየው የጁምአ ሶላት ፈርዶል አይን መሆኑን ነው። ኢብን ሙንዚር በኢጅማኡ እንደገለፀው የጁምአ ሶላት መንገደኛ ባልሆኑና አሳማኝ ምክኒያት በሌላቸው በሁሉም ላይ ግዴታ መሆኑን ሊቃውንቶች ሙሉ በሙሉ ተስማምተዋል።
የጁምአ ሶላት ብዙ ትሩፋቶች አሉት። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
“በጁምአ ቀን ገላውን ታጥቦ ፣ የሚችለውን አፅድቶ ፣ ፀጉሩን ቅባት ቀብቶ ፣ ሽቶ ነስንሶ የመጣና በሁለት ሰዎች መካከል ሳይገባ እና እንዲሰግድ የተፃፈለትን የሰገደ ፣ ኢማሙ ሲናገር ዝም ያለ ሰው የለም ባለፈው እና በጁምአ ቀን መካከል ለሰራው ነገር የተማረለት ቢሆን እንጅ።”
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(አህመድ)
“በዚህ ቀን ከተከለከለው ውጭ ካልጠየቀ በቀር አሏህን ማንኛውንም ነገር የጠየቀ ሰው የሚሰጥበት ጊዜ አለች”

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ሙስሊም)
“ውዱእ አሳምሮ አድርጎ ወደ መስጅድ የሄደ ሰው ፣ ሁጥባውን ያደመጠ እና ዝም ያለ ሰው ከጁምአ እስከ ጁምአ የሰራው መጥፎ ነገር ይማርለታል።”
ኢብን ማጃ ባስተላለፈው ሌላ ዘገባ “ትልቅ ወንጀል እስካልፈፀመ ድረስ” ብለዋል።
ሙስሊም ሊቃውንቶች እንደገለፁት በዚህ ሐዲስ የተጠቀሰው የሃጢያቶች ምህረት ለትንንሾቹ ሃጢያቶች ነው ብለዋል። ትልልቆቹ ሃጢያቶች በዚህ አይካተቱም። ትልልቆቹን ወንጀሎች በተመለከተ ሙስሊሞች ከልብ የመነጨ ተውበት (ንሰሃ) ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።



