ተስቢህ ማለት ሱብሃን አሏህ (ለአሏህ ጥራት ይገባው) ማለት ነው። ሙእሚኖች ተስቢህ እንዲያደርጉ አሏህ አዟል።
አል-ቁርአን
(ሱረቱል አዕላ 87፡1)
ከሁሉ በላይ የሆነው የጌታህን ስም አወድስ።
አል-ቁርአን
(አል-ቁርአን 33፡41-42)
እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አሏህን ብዙ ማውሳትን አውሱት። በቀኑ መጀመሪያና መጨረሻም አወድሱት (አጥሩት)።
ተስቢህ ብዙ ጥቅሞች ያሉት የዚክር አይነት ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
“አንድ መቶ ጊዜ ሱብሃነሏህ ወቢሃምዲ ያለ ሰው ሁሉም ወንጀሎቹ ይማሩለታል ልክ እንደ ባህር አረፋ ቢሆን እንኳ።”
እንዲህም አሉ፡
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪ)
“ለምላስ የሚቀሉ ፣ ለሚዛን የሚከብዱ ፣ አሏህ ዘንድ ተወዳጅ የሆኑ ሁለት ንግግሮች አሉ። (እነሱም) ሱብሃነሏህ አል-አዚም እና ሱብሃን አሏህ ወቢሃምዲ ናቸው።”

ዚክር እና ተክቢር ተመልከቱ




Share