ሸይጧን ሙእሚኖችን የሚቀርብባቸው መንገዶች

Author picture

ሸይጧን ሙእሚኖችን የሚቀርብባቸው መንገዶች : በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ሸይጧን የጅኖች ወይም የአጋንት አንዱ አካል ሲሆን የራሳቸው የሆነ አለም ወይም መኖሪያ አላቸው። እራሳቸውን ከሰው ልጅ እይታ ከመሰወር ብቃት ጋር የተፈጠሩም ናቸው። ሰይጣን እራሱን እንደ ሰው ልጆች ሁሉ የሚያበዛ ሲሆን የራሱ የሆኑም ዘሮች አሉት።

\”መላኢካዎችንም ለአደም ስገዱ ባልን ጊዜ የነበረውን አስታውስ። ለአደም ስገዱ አልን ኢብሊስ ሲቀር ሰገዱ። ከጅኖችም መካከል ነበር። የጌታውንም ትእዕዛዝ አሻፈረኝ አለ። እናም ከኔ ይልቅ ሸይጧንና ዘሮቹ ጠላቶቻችሁ ሆነው እያለ ጠባቂና ረዳት አድርጋችሁ ትይዛላችሁን?\”

{ሱረቱል ካኽፍ 18:50}

በዚህ መንገድ የሸይጧን ዘሮችና ተከታዮቹ የሰውን ልጅ ለማሳሳትና ትኩረቱን አለማዊ (ምደራዊ) እንዲያደርግ ይለፋሉ።

ሸይጧን እንዴት ወደ ሰው ልጅ ይቀርባል?

ሸይጧን ሙእሚኖችን የሚቀርብባቸው መንገዶች እና የሚለክፍባቸው መንገዶች ብዙ ናቸው። እነዚህ የሸይጧን ወጥመዶች እንደየስው ባህሪ እና ደካማ ጎን ይለያያሉ። በጣም የሚወዱት ነገር በመመልከት ቀስበቀስና ደረጃ በደረጃ ይቀርባል።

ዋና አላማው የሰው ልጆችን በማጥመም ሙሉ በሙሉ በአሏህ ላይ ያመፁ ማድረግ ነው። በእምነታቸው ጠንካራ ከሆኑበት በፈጠራዎችና በፍልስፍናዎች የተዘፈቁ እንዲሆኑ በማድረግና የአሏህን ህግጋቶች ችላ እንዲሉና እንዲቀናንሱ በማድረግ ይጀምራል።

  • ሸይጧን ፈተናውን ከተቋቋሙበት ከባባድ ወንጀሎችን እንዲሰሩ በማድረግ የአሏህን ህግጋት እንዲጥሱ በማድረግ ይፈትናቸዋል።
  • ሙእሚኖች ከባባድ (ከባኢር) ወንጀሎችን ሊሰሩ ባይችሉንኴ ሸይጧን እጅ አይሰጥም። እናም ወንጀሎችን ቀላል መስለው እንዲታያቸው በማድረግ እና ወንጀሎችን በማስጌጥና በማስዋብ ፈተናውን ይጀምራል።

ሰይጣን የሚከተለው ደረጃ በደረጃ የአሰራር ሂደትን ነው።

\”አሏህ ያስገኛችሁን ነገር ተመገቡ፤ የሸይጧንንም የእግር ኮቴ አትከተሉ፤ በእርግጥ እሱ ለእናንተ ግልፅ ጠላት ነው።\”

{አል-ቁርአን 6 : 142}

ሸይጧን ሰለባዎቹን የሚቀርብበት መንገድ እንደ ሰው ልጆች ፍላጐትና ዝንባሌ ይለያያል። ኡለማዎችን በኡለማዎች ያጠቃል መሃይሞችን በመሃይማን ያጠቃል።

  • በልቦቻችን ውስጥ ጥርጣሬና ጥላቻ እንዲኖር በማድረግ
  • ወንጀል ለሆኑ ነገሮች ነፍሲያችን የሚያስደስታትን ስም በመስጠት። ለምሳሌ:- የአልኮል መጠጥጦችን የመንፈስ እርካታ ሰጭ በማለት

በዚህ መንገድ ሰለባውን በቀላል መንገድ ያታልለዋል። የተከለከሉ ነገሮች ሐላል ናቸው ብሎ ንዲያምን ያደርገዋል። ይህ ዘዴው ከተሳካለት ስራዎቹ ቀጣይነት ይኖራቸው ዘንድ ሹክ ይለዋል። የበለጠ ይሰራና ይታገል ዘንድ ሊያሳምነው ይሞክራል። እንዲሁም የሚሰራው ስራ በቂ አለመሆኑን ምኞቱ ሰፊና ትልቅ መሆን እንዳለበት ይነግረዋል። ትልቅ ወንጀሎችን ባትሰራ አንዳንድ ትንንሽ ወንጀሎችን የሚሠሩ ሞልተዋል ሲል ያስተምረዋል።

ሃይማኖታዊ ግዴታዎች በተለያየ መልኩ እንዲያከናውን ለማድረግ መሰናክሎችን እንዲጋፈጥ ያደርገዋል። ለምሳሌ:

  • አንድ ሰው ወደ አሏህ በተውባ እመለሳለሁ ሊልይችላል። ነገርግን መልሶ ትምህርቴን ስጨርስ ፣ ሳገባ ፣ ስራ ሳገኝ የሚሉትን መሠናክሎች አስቀድሞ ጥሎበት ያልፋል።
  • አንድ ሰው እኔ ሙሉና በማንኛውም ነገር ትክክለኛ ነኝ ብሎ ማሰብ ሲጀምር
  • በሚያምኑበት ነገር ላይ እንዲጠራጠሩ በማድረግ

\”ኢብሊስም አለ: በሃያልነትህ ይሁንብኝ ሁሉንም አሳስታቸዋለሁ የተመረጡ ባሮችህ ሲቀሩ።\”

{አል-ቁርአን 38:82-83}
  • መጥፎ የሆኑ ነገሮችን ለአይናችን ያማረ በማስመሰል
  • ሃጢያት የሆኑ ነገሮችን አቅለን እንድናይና እንድንመለከት በማድረግ
  • መክሩህ የሆኑ ነገሮች ላይ እንድናዘወትር በማድረግ
  • በልቦቻችን ውስጥ ጥርጣሬ እንዲኖር በማድረግ
  • ስራውን የሚያቀልለተን ነገር በመጠቀም
  • ከችግሮቻችን በመነሳት

መድሃኒቱ

  • በአሏህ ማመን

\”በእርግጥ እሱ (ሸይጧን) በነዚያ ባመኑትና ተስፋቸውንም በጌታቸው ላይ ባደረጉት ሃይል የለውም።\”

{አል-ቁርአን 16:99}
  • ኢስላማዊ እውቀትን ከትክክለኛ አሊም መሻት
  • ጥበቃንና ከለላን ከአሏህ ብቻ መሻት

\”ከሸይጧንም በኩል ጉትጐታ ቢያጋጥምህ በአሏህ ተጠበቅ። በእርግጥ እሱ ሁሉን አዋቂ ሁሉን ሰሚ ነው።\”

{አል-ቁርአን 7 : 200}
  • ቁርአን አብዝቶ መቅራት ወዘተ

Share

More Posts

Send Us A Message

Scroll to Top