ነብዩ ሙሳ “ከቁርጥ ውሳኔ መልዕክተኞች” አንዱ ሲሆኑ ከሊሙሏህ (አሏህ ያናገራቸው) ተብለውም ይታወቃሉ። ሃያሉ አሏህ በሲና ተራራ አናግሯቸዋልና።
ነብዩ ሙሳ

ነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) “ከቁርጥ ውሳኔ መልዕክተኞች” አንዱ ሲሆኑ ከሊሙሏህ (አሏህ ያናገራቸው) ተብለውም ይታወቃሉ። ሃያሉ አሏህ በሲና ተራራ አናግሯቸዋልና።

ጨቋኙ የግብፅ ንጉስ የነበረው ፊርኦን ከእስራኤል ልጆች አነዱ ሲያሸንፈው በህልሙ አየ፡፡ ሆኖም ቀሳውስቱን እና ድግምተኞቹን ሰበሰበ።

“ከእነሱ መካከል አንድ ወንድ ልጅ  ይወለዳል፤ የግብፅ ህዝቦችም በእጆቹ ይጠፋሉ” ሲሉ አብራርተው አስረዱት።

በዚህም ምክኒያት አዲስ የሚወለዱ ሁሉም የእስራኤል ወንድ ልጆች እንዲገደሉ ፊርአውን አዘዘ።

ነብዩ ሙሳ መወለድ

ወንድ ልጆች በሚገደሉበት በዚህ ጊዜ ነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) ተወለዱ። እናት ልጄን ይገሉብኛል ብላ ፈራች ፣ ተጨነቀችም።

እናም በሚስጥር ማጥባት ጀመረች። ለልጇ ሳጥን እንድታበጅ ፣ ሳጥኑ ውስጥ ልጇን እንድታስገባ እና ወደ አባይ ወንዝ ወስዳ ወንዙ ላይ ሳጥኑን እንድታስቀምጥ አሏህ (ሱ.ወ.ተ) አሳወቃት።

ይህን እንዳደረገችም በጣም አዘነች። ነገርግን በእርግጠኝነት አሏህ እንደሚጠብቀው ታውቅ ነበር።

ቅርጫቱ የቤተ-መንግስቱ የወንዝ ዳርቻ ላይ ባረፈ ጊዜ ጠባቂዎች ወደ ቤተመንግስት ወሰዱት። የፊርአውን ሚስት አማኝ ነበረች።

ቆንጅየውን ልጅ እንዳየች ወዲያውኑ በጣም ወደደችው። መፀነስ አትችልም ነበርና “ልጁን ተንከባክበን እናሳድገው” ስትል ባሏን ተማፀነች።

ሆኖም ነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) የፊርአውን ቤተመንግስት ውስጥ ሆኖ አደገ። ነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) የሌሎች እናቶችን ጡት አልጠባም በማለቱ አሏህ የእናቱን ጡት እንዲያገኝ አደረገ።

አሏህ ለሙሳ (ዐ.ሰ) ጤና ፣ ጥንካሬ ፣ እውቀት እና ጥበብ ሰጥቶታል። ደካሞች እና ጭቁኖች የእሱን መጠለያ እና ፍትህ ይፈልጉ ነበር።

አንድ ቀን አንድ እስራኤላዊ በአንድ ግብፃዊ ሲደበደብ ደርሶ እንዲረዳው ይለምነዋል።

ነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) በጠባቸው መሃል ይገባል፤ ወዲያውም በቁጣ አንድ ጊዜ ከባድ ምት ይመታውና ይሞታል። እንደገደለው ሲያውቅ ሙሳ (ዐ.ሰ) በሃዘን ተውጦ ወዲያውኑ የአሏህን ምህረት ለመነ።

የነብዩ ሙሳ ስደት

ሙሳ (ዐ.ሰ) ግብፃዊውን ሰው በመግደሉ ቅጣቱ ሞት እንደሆነ ያውቃል። ሆኖም በጣም ፈራ። የከተማው ሹማምንት እሱን ለመግደል መከሩ። በአንድ ቅን ሰው ምክር ምክኒያት ከተማዋን ለቆ ሊወጣ ወሰነ።

የነብዩ ሙሳ ስደት

ነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) ግብፅን ለቆ በመውጣት ጉዞውን ወደ ሚድያን ሐገር አደረገ። ሚድያን እንደደረሰም ከአንድ ዛፍ ጥላ ስር አረፈ።  

በጎቻቸውን ውሃ የሚያጠቱ እረኞችንም ከርቀት ተመለከቶ ወደ ምንጩ የውሃ ጉድጓድ ሄደ። ሁለት ሴቶች በጎቻቸው ከሌሎች በጎች ጋር እንዳይቀላቀሉ ሲከላከሉ ተመለከተ።

ሴቶቹ እርዳታ እንደሚሹ ተሰማውና በጎቻቸውን ውሃ አጠጣለቸው። ወጣቶቹ ሴቶች ወደ ቤታቸው እንደ ተመለሱ ከቀድሞው ጊዜ በተለየ ፈጠን ብለው የተመለሱበትን ምክኒያት ከውሃው ጉድጓድ ያጋጠማቸውን ክስተት ለአባታቸው አጫወቱት። ይህን ደግ እንግዳ ወደ ቤት እነድትጠራው ከሴት ልጆቹ አንዷን ላካት።

የነብዩ ሙሳ እረኝነት

አንደኛዋ ልጅ ጠንካራና ታማኝ ነው ሙሳን ቅጠረው ስትል ለአባቷ ሃሳብ አቀረበች። ሽማግሌው ይህን በመስማቱ ደስ ተሰኘ።

ለስምንት አመት ያህል ካገለገልከኝ ከሁለቱ ሴት ልጆቼ አንዷን እድርልሃለሁ አለው። አስር አመት ልሙላ ካልክ ውለታው ከአንተ ነው።

ሙሳ (ዐ.ሰ) በዚህ በመስማማቱ የሽማግሌውን አንደኛዋን ልጅ አግብቶ ሽማግሌውን እያገለገለ ለአስር አመት ያህል ተቀመጠ።

ነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) ግብጽ ያሉ ቤተሰቦቹን ለመጠየቅ ከቤተሰቡ ጋር ሚዲያን ለቆ በደቡብ በኩል በረሃውን አቋርጦ ሄደ። አንድ ቀን ድቅድቅ ጨለማ እና ብርድማ በሆነ ሌሊት ላይ መንገዱ ጠፋባቸው።

ወዲያውም በጡር ተራራ አቅጣጫ በኩል ከርቀት እሳት አየ። የምንሞቀው እና ለመንገዳችን መሪ የሚሆነን እሳት ይዜ ልምጣ፤ እናንተ እዚሁ ጠብቁኝ ብሎ ሄደ።

ወደ እሳቱ እንደቀረበም ከጡዋ ሸለቆ በስተቀኝ በኩል ከምትገኝ አንዲት ዛፍ ላይ ከፍ ባለ ድምፅ ሲጠራው ሰማ “ሙሳ ሆይ! እኔ አሏህ ነኝ፤ የፍጥረተ አለሙ ጌታ።” እዚህ ቦታ ላይ አሏህ ሁለት ተአምራትን ለሙሳ (ዐ.ሰ) ሰጠው።

በትሩ ወደ ሚያስፈራ እባብ ይቀየር ነበር። እንዲሁም እጁን ከልብሶቹ እጥፋት ሲያወጣ ነጭ እና የሚያፀባርቃል ይሆን ነበር።

የነብዩ ሙሳ ተአምራት

የነብዩ ሙሳ ተአምራት

ነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) ከወንድሙ ሐሩን (ዐ.ሰ) ጋር በመሆን ፊርአውን አሏህን ብቻ እንዲያመልክ እንዲጠራው እና የእስራኤል ልጆችን ይዞ እንዲወጣ አሏህ አዘዘው።

የነብዩ ሙሳ ተአምራት

ሙሳ (ዐ.ሰ) ለፊርአውን ተአምራዊ ምልክቶቹ ባሳየው ጊዜ በእብሪተኝነት እውነቱን ካደ። ፈርኦንም “እንዲህ አይነቱን መተት በደጋሚዎቼ እፈጥራለሁˮ አለ።

ይህን ለማስተባበል ህዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ላይ እንዲሆን ተስማሙ። ነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) በጣም ብዙ ሰዎች የሚሰባሰቡበትን የቤተመቅደሱን ታላቅ ቀን መረጠ። በዚህ ታሪካዊ ቀን ሙሳ (ዐ.ሰ) የደጋሚዎቹን መተት አጋለጠ።

እውነትን ይዞ የመጣ መሆኑን በመረዳት ደጋሚዎቹ ሱጁድ አደረጉ (ሰገዱ)። በፍጥረተ አለሙ ጌታ ያመኑ መሆኑን አወጁ።

ጊዜ እንዳለፈ ሙሳ (ዐ.ሰ) ህዝቦቹን ይዞ ግብፅን ለቆ ወደ ፈለስጢን በሌሊት እንዲሄድ አሏህ (ሱ.ወ.ተ) አዘዘው። ሆኖም ግብፅን ለቀው ሄዱ። ፈርኦንና ወታደሮቹም ተከተሏቸው።

ሁለቱ አካል ጠዋት ማለዳ ላይ እርስ በርስ በተያዩ ጊዜ የሙሳ ሰዎች “በእርግጥ ተያዝን፤ አለቀልንˮ አሉ። በፊርአውን እና በወታደሮቹ ላይ አሏህ ይረዳናል ሲል ሙሳ (ዐ.ሰ) አረጋገጠላቸው።

እናም ሙሳ (ዐ.ሰ) ባህሩን በበትሩ እንዲመታ አሏህ ገለፀለት። ባህሩ ልክ እንደ ትልቅ ግዙፍ ተራራ ሆኖ ተከፈለ። ሙእሚኖችም በሰላም ተሻግረው አለፉ።

ፊርአውን እና ወታደሮቹ መካከል ላይ እንዳሉ ውሃው ሙሉ በሙሉ አጥለቀለቃቸው። ሁሉም ሰጠሙ፤ ጠፉም። አሏህ ሙሳን ተከታዮቹን አዳናቸው።

0%
3
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

የታሪክ ጥያቄና መልስ

ነብዩ ሙሳን (ዐ.ሰ) ምን ያህል ያውቋቸዋል?

የነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) ታሪክ በቁርአን ውስጥ በብዛት ከተጠቀሱ ታሪኮች አንዱ ሲሆን በሚያስደንቁ ክስተቶች እና ትምህርቶች የተሞላ ነው። ነገር ግን ስለ ታሪካቸው ምን ያህል እውነታዎችን ያውቃሉ? ከታች ያለውን ጥያቄና መልስ በመሞከር እራስዎን ይፈትሹ! ስንት መልሶችን በትክክል እንዳገኛችሁ በአስተያየት መስጫው ላይ ያሳውቁን።

1 / 20

1 ነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) በሕፃንነታቸው በእናታቸው ወደ ወንዝ የተጣሉት በምን ዓይነት ዕቃ ውስጥ ነበር?

2 / 20

2 ሙሳን (ዐ.ሰ) ከወንዙ ውስጥ ያገኘቻቸው የፊርዐውን (ፈርዖን) ሚስት ነበረች። ስሟ ማን ነበር?

3 / 20

3 ሕፃኑ ሙሳ (ዐ.ሰ) ሌሎችን (አጥቢዎችን) እንቢ ካለ በኋላ በአቅራቢያው ጥሩ የሆነች አጥቢ እንዳለች ለፈርዖን ቤተሰቦች በብልሃት የነገረችውና ከእናቱ ጋር እንዲገናኝ ያደረገችው ማን ነበረች?

4 / 20

4 ሙሳ (ዐ.ሰ) ከግብፅ እንዲሸሹ ያደረጋቸው ክስተት የትኛው ነው?

5 / 20

5 ከግብፅ ከሸሹ በኋላ ሙሳ (ዐ.ሰ) በመጨረሻ አዲስ ቦታ ደረሱ። ይህ ቦታ ምን ተብሎ ይጠራ ነበር?

6 / 20

6 በዚህ ቦታ ሲደርሱ ሙሳ (ዐ.ሰ) በውኃ ጉድጓድ አጠገብ ሁለት ሴቶች ሲታገሉ አዩ። በምን ነበር የሚታገሉት?

7 / 20

7 ሙሳ (ዐ.ሰ) በመጨረሻ ከእነዚህ ሁለት ሴቶች አንዷን አገቡ። ስሟ ማን ነበር?

8 / 20

8 ከቤተሰቦቻቸው ጋር በሚጓዙበት ጊዜ ሙሳ (ዐ.ሰ) በጡር (ጡር) ተራራ አቅጣጫ አንድ ነገር ተመለከቱ፤ ይህም ሄደው እንዲያጣሩ አደረጋቸው። ይህ ቦታ በመጨረሻ አላህን (ሱ.ወ) ያነጋገሩበት እና ነብይነትን የተቀበሉበት ነው። ያዩት ነገር ምን ነበር?

9 / 20

9 አላህ (ሱ.ወ) ሙሳ (ዐ.ሰ) መሬት ላይ እንዲጥሉት ያዘዛቸውና ወደ እባብነት የተቀየረው የሙሳ (ዐ.ሰ) ንብረት የትኛው ነው?

10 / 20

10 አላህ (ሱ.ወ) ሙሳን (ዐ.ሰ) እጃቸውን በልብሳቸው (በብብታቸው) ውስጥ እንዲያስገቡ ባዘዛቸው ጊዜ ምን ሆነ?

11 / 20

11 ሙሳ (ዐ.ሰ) ሄደው ፈርዖንን እንዲጋፈጡ ሲታዘዙ አላህን (ሱ.ወ) ምን ብለው ጠየቁ?

12 / 20

12 የፈርዖን ድግምተኞች ሙሳ (ዐ.ሰ) በፊታቸው ያከናወኗቸውን ተአምራት ሲመለከቱና ሲሸነፉ ምን ምላሽ ሰጡ?

13 / 20

13 ፈርዖን በሙሳ (ዐ.ሰ) መልእክት ለማመን ፈቃደኛ ካልሆነ በኋላ ግብፅን ከመቷቸው መቅሰፍቶች መካከል ያልሆነው የትኛው ነው?

14 / 20

14 ሙሳ (ዐ.ሰ) በትራቸውን በቀይ ባህር ላይ ባደረጉ ጊዜ አላህ (ሱ.ወ) ምን ተአምር እንዲከሰት አደረገ?

15 / 20

15 የሙሳ (ዐ.ሰ) ሕዝቦች በሌላ ስማቸው ምን በመባል ይታወቃሉ?

16 / 20

16 በሙሳ (ዐ.ሰ) ሕዝቦች መካከል ሕዝቡን ለማሳሳት (ማለትም ከአንድ አምላክ አምልኮ ለማውጣት) የሞከረ አንድ ዓመፀኛ ሰው ነበር። ስሙ ማን ነበር?

17 / 20

17 ይህ ዓመፀኛ ሰው የሙሳን (ዐ.ሰ) ተከታዮች ወደ ጣዖት አምልኮ እንዲወድቁ ለማበረታታት ምን አደረገ?

18 / 20

18 ይህን ለማድረግ ዕድሉን ያገኘው መቼ ነበር?

19 / 20

19 አላህ (ሱ.ወ) በኑ ኢስራኢልን ይቅር ማለቱን እና መርዳቱን በመቀጠል ባለፉት ዓመታት ሲሳይን ልኮላቸዋል፤ ይህም ውሃን ፣ ጥላን እና ሁለት ዓይነት ምግቦችን ይጨምራል። እነዚህ ምግቦች ምን ይባሉ ነበር?

20 / 20

20 ነብዩ ሙሳ (ዐ.ሰ) ትእዛዛቱን ከአላህ (ሱ.ወ) የተቀበሉት በምን ዘዴ ነበር?

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 8%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

ነብዩ ዩኑስ

ነብዩ ዩኑስ

ነብዩ ዩኑስ (ዐ.ሰ) ወይም ነብዩ ዩሃንስ ህዝባቸው የጣኦት አምልኮትን እንዲተው ፣ አሏህን ብቻ እንዲያመልኩ እና ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ ጥሪ እንዲያደርጉ አሏህ ለአሲርያዎች የላካቸው ነብይ ናቸው።

Read More »
ነብዩ ሱለይማን

ነብዩ ሱለይማን

ነብዩ ሱለይማን (ዐ.ሰ) የነብዩ ዳውድ (ዐ.ሰ) ልጅ ነው። ጠንካራ ንጉስ ሲሆን ከአሏህ ታላላቅ ነብያትም ውስጥ አንዱ ነው። አሏህ ሃይልን ፣ ጥበብ እና እውቀት ሰጥቶታል።

Read More »
ነብዩ ሷሊህ (ዐ.ሰ)

ነብዩ ሷሊህ (ዐ.ሰ)

ነብዩ ሷሊህ (ዐ.ሰ) አሏህ የላካቸው በሰሜን ምዕራብ አረቢያ ፣ በመዲና እና በሶሪያ መካከል ይኖሩ ለነበሩ የሰሙድ ህዝቦች ነው። ይህ ቦታ አለታማ እና ትልቅ ለም ሸለቆ

Read More »

Share