ኡመሃተል ሙዕሚኒን (የሙዕሚኖች እናት) የነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶች ናቸው። እያንዳንዳቸውም የእናትነት ደረጃ አላቸው። ሆኖም ላቅ ያለ ክብር ይገባቸዋል። ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሞት በኋላ አንዳቸውንም ማግባት የተከለከለ ነው።

ኡመሃተል ሙዕሚኒን (የሙዕሚኖች እናት) የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ሚስቶች ናቸው። እያንዳንዳቸውም የእናትነት ደረጃ አላቸው። ሆኖም ላቅ ያለ ክብር ይገባቸዋል። ከነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሞት በኋላ አንዳቸውንም ማግባት የተከለከለ ነው።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) የአሏህን ራዕይ (ወህይ) ከመቀበላቸው በፊት ያገቧት የመጀመሪያ ሚስታቸው ኸድጃ (ሰ.ዐ.ወ)  ናት። በመልዕክታቸው ያመነች የመጀመሪያ ሴት ናት። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሲያገቧት እድሜዋ 40 አመት ሲሆን እሳቸው ደግሞ የ25 አመት ወጣት እያሉ ነው።

በቅፅል ስማቸው አጦይብ መልካሙ እና ጧሂር ንፁሁ ተብለው የሚጠሩ አብዱሏህ እና ቃሲም የተባሉ ሁለት ወንድ ልጆች፤ ዘይነብ ፣ ፋጡማ ፣ ሩቂያ እና ኡሙ ኩልሱም የተባሉ አራት ሴት ልጆችን ወልዳላቸዋለች።

ከኸድጃ (ሰ.ዐ.ወ) ሞት በኋላ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ያገባችው ሌሎች ሚስቶች፡ ሰውዳ ቢንት ዘማህ ፣ አኢሻ ቢንት አቡበክር ፣ ሐፍሷ ቢንት ኡመር ፣ ዘይነብ ቢንት ጀዕሽ ፣ ዘይነብ ቢንት ኹዘይማ ፣ ኡሙ ሰላማ ሂንድ ቢንት ኡመያ ፣ ኡሙ ሃቢባ ረምላ ቢንት አቡ ሱፍያን ፣ ጀወይሪያ ቢንት አል-ኸሪስ ፣ ሳፊያ ቢንት ሁየይ ኢብን ኸጧብ እና መይሙና ቢንት አል-ኸሪስ ናቸው።

Related posts

ነብዩ ዩኑስ

ነብዩ ዩኑስ

ነብዩ ዩኑስ (ዐ.ሰ) ወይም ነብዩ ዩሃንስ ህዝባቸው የጣኦት አምልኮትን እንዲተው ፣ አሏህን ብቻ እንዲያመልኩ እና ወንጀል ከመፈፀም እንዲቆጠቡ ጥሪ እንዲያደርጉ አሏህ ለአሲርያዎች የላካቸው ነብይ ናቸው።

Read More »
የዘምዘም ውሃ

የዘምዘም ውሃ

የዘምዘም የውሃ ጉድጓድ የሚገኘው ከካዕባ ቀጥሎ ነው። ውሃው ምድር ላይ ካለ ውሃ ሁሉ ቅዱስ እና ድንቅ ውሃ ነው። በምድር ላይ በላጩ ውሃ የዘምዘም ውሃ ነው።

Read More »
እስልምና በኢትዮጵያ፡

እስልምና በኢትዮጵያ፡ ከጥንታዊ ሥረ-መሠረቱ እስከ ዘመናዊ ስርጭቱ

ኢትዮጵያ ከዓለም ጥንታዊ ሥልጣኔዎች አንዷ ስትሆን በርካታ እምነቶች ያስተናገደች ምድርም ነች። ከእነዚህም መካከል እስልምና እና ክርስትና ይገኙበታል። እስልምና በኢትዮጵያ ታሪክ የራሱን ጉልህ አሻራ ያሳረፈ ሃይማኖት

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share