ዘካ ሶስተኛው የእስልምና ምሰሶ ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አሉ፡
የዘካ የሚያስከፍለውን ትንሿን መጠን (ኒሳብ) ለአንድ አመት ሙሉ በያዘ ሙስሊም ላይ ሁሉ ግዴታ ነው። ዘካ የሚሰጠው በተከታዩ የቁርአን አንቀፅ እንደተጠቀሰው ለስምንት አይነት ሰዎች ነው።

አል-ቁርአን
(ሱረቱ ተውባ 9፡60)
ለድሆች ፣ ለሚስኪኖች ፣ በእሷ ላይ ዘካ ለመሰብሰብ ለሚሰሩ ሰራተኞች ፣ ልቦቻቸው (ወደ እስልምና) ካጋደለ ፣ ምርኮኞችን (ባሮችን) ነፃ ለማውጣት ፣ በእዳ ላይ ላሉ ፣ በአሏህ መንገድ ለሚታገሉ እና ለመንገደኛ ሰው ነው። ከአሏህ የተደነገገች ግዴታ ናት። አሏህ ሁሉን አዋቂ ጥበበኛ ነው።
ዘካ የድሆችን እና የችግረኞችን ፍላጎት በማሟላት እና እዳቸውን በመክፈል ለእነሱ ያለንን ውዴታ መግለጫ ነው። ዘካ የአረብኛ የቃል በቃል ትርጉም ማጥራት የሚለው ነው።
ዘካ የከፋዩን ሰው ገንዘብ ያጠራል፤ አሏህ ይባርክለታል፤ ይጨምርለታል። ልብን ከራስ ወዳድነት ያፀዳል የሃብት ስስትን እና ጥማት ይቆርጣል።

እንዲሁም ዘካ የጠቀባዩን ሰው ልብ ከቅናት እና ከጥላቻ ያፀዳል ፣ ልብን ከራስ ወዳድነት ያፀዳል ፣ ስስትን ያርቃል። ለብዙ ማህበራዊ ችግሮች መፍትሄ እና መድሃኒት ነው። ቁርአን እንዲህ ይላል፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ሐሽር 59፡9)
ነፍሱን ከንፍገት (ከስስት) የጠበቀ ሰው፤ እነዚያ እነሱ ስኬታማ ናቸው።

ሀብት በጥቂት እጆች ላይ ብቻ እንዳይከማች እና ሁሌም በዝውውር ሂደት ውስጥ እንዲሆን ቅዱስ ቁርአን ያዛል (አል-ቁርአን 59፡7)። ለዚህም ነው እስልምና በወለድ ወይም በአራጣ ገንዘብን ማበደርን የከለከለው።
ጥቂት ብልጥ ሰዎች ትልቁን የማህበረሰብ የሃብት ክፍል በበላይነት መቆጣጠር ያስችላቸዋል። ፍትሃዊ የሆነ የሃብት ክፍፍል እንዲኖር ያስፈልጋል።
ድሃ የሆኑ የማህበረሰቡ ክፍሎች ህይወታቸው እንዲሻሻል ፣ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ እና ሁሉም የማህበረሰቡ አካል የሆነ ሰው በምጣኔ ሃብቱ የበለፀገ እንዲሆን ይፈልጋል።

አንድ ሙስሊም ዘካውን ሲከፍል ወይም ደግሞ ሌላ ማንኛውም ነገር ሶደቃ ሲሰጥ ተግባሩን በመጥፎ ምግባር ሊያስከትል ወይም ለቀጣዩ ስለልግስና (ስለቸርነት) ሊያስታውሰው አይገባም። አሏህ እንዲህ ይላል፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል በቀራ 2፡263)
መልካም ንግግር እና ምህረት ክፍት ከሚከተለው ምፅዋት የበለጠ ነው።
አንድ ሰው ለአሏህ ብሎ ሲከፍል ምላሹን ምንም ነገር መጠበቅም ሆነ መፈለግ የለበትም። ሃብት (ሲሳይ) የአሏህ ችሮታ ነው። ለፍተን ደክመን ያገኘነውን በፈቃዳችን መስጠት ይኖርብናል።
በእርግጥ አሏህ ባወጣነው ይተካልናል። ትዕዛዛቶቹን በማክበራችን እና በመከተላችን በመጭው አለም ህይወት ይመነዳናል። አሏህ እንዲህ ይላል፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ሰበዕ 34፡39)
ከማንኛውም ነገር የምትለግሱትን እሱ ይተካዋል። እሱ ከሰጭዎች ሁሉ በላጭ ነው።
እንዲህም ይላል፡
አል-ቁርአን
(አል-ቁርአን 35፡29)
እነዚያ የአሏህን መጽሐፍ የሚያነቡ ፣ ሶላትን የሚሰግዱ ፣ ከሰጠናቸውም በግልፅም ሆነ በድብቅ የሚለግሱ፤ በፍፁም የማትከስርን በንግድ ተስፋ ያደርጋሉ።
እስልምና ሃይማኖት ፣ ሪባእ እና ሶደቃ ተመልከቱ

Share