የእስልምና ሃይማኖት

Author picture
እስልምና የአብዱሏህ ልጅ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ለሰው ልጆች ሁሉ እንዲያደርሱ ከጌታቸው የተላኩበት የመጨረሻው ሃይማኖት ነው። እስልምና ማለት ‹ሰላም እና እጅ› መስጠት ማለት ነው።
እስልምና

እስልምና የአብዱሏህ ልጅ ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ለሰው ልጆች ሁሉ እንዲያደርሱ ከጌታቸው የተላኩበት የመጨረሻው ሃይማኖት ነው። እስልምና ማለት ‹ሰላም እና እጅ› መስጠት ማለት ነው።

እራስን ለአሏህ ፈቃድ በማስገዛት የሚገኝ ሰላም ነው። ለአሏህ ፈቃድ ሙሉ በሙሉ እራሱን የሰጠ ሰው ደግሞ ሙስሊም ተብሎ ይጠራል።

ስለዚህ ለኑህ ፣ ለኢብራሂም ፣ ለነብዩ ሙሳ ፣ ኢሳ ወይም ለሙሐመድ የተሰጠው መሰረቱ አንድ አይነት ነው። ሰዎችን የሚጠሩበት መልዕክትም አንድ ነው።

እሱም አሏህ ብቻ ተገዙ፤ በእሱም ላይ አታጋሩ የሚለው ነው።

እስልምና እንከን የለሽ ሙሉ ሃይማኖት ነው።

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ሹራ 42፡13)

ለኑህ እንደደነገገው ያለ አንድ ሃይማኖት ደነገገላችሁ። ያ ወደ አንተ የተገለፅነው ለኢብራሂም ፣ ለሙሳ እና ለኢሳ ሃይማኖትን አቋቁሙ (ቆርቆሩ) ብለን ደነገግን በእሱም (በሃይማኖቱ) ልዩነትን እና መከፋፈልን አታድርጉ።

እውነተኛ ሃይማኖት

እስልምና እንከን የለሽ ሙሉ እና እውነተኛ ሃይማኖት ነው። መቀነስንም ሆነ መጨመርን አይፈልግም። አሏህ በቁርአኑ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ማኢዳ 5፡3)

ዛሬ ሃይማኖታችሁን ሞላሁላችሁ፤ ፀጋየንም በእናንተ ላይ ፈፀምኩ፤ ለእናንተም ከሃይማኖት እስልምናን ወደድኩ።

እስልምና የመጨረሻው ሃይማኖት በመሆኑ ከእሱ በፊት የነበሩ ሃይማኖቶችን ሁሉ ሽሯል። አሏህ የሚቀበለው ብቸኛው ሃይማኖት እስልምና ነው።

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ኢምራን 3፡85)

ከእስልምና ውጭ ሌላ ሃይማኖት የሚሻ ሰው ከእሱ ተቀባይነት የለውም። እሱም በመጭው አለም ከከሳሪዎች ነው።

ሶላት መስገድ ፣ ዘካ መስጠት ፣ ረመዷን መፆም እና ሐጅ ማድረግ

መልአኩ ጅብሪል ስለ እስልምና ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በጠየቃቸው ጊዜ እንዲህ ሲሉ መለሱ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም)

“እስልምና ከአሏህ ውጭ አምላክ አለመኖሩን እና ሙሐመድ የአሏህ መልዕክተኛ መሆናቸውን መመስከር ነው። ሶላት መስገድ ፣ ዘካ መስጠት ፣ ረመዷን መፆም እና ሐጅ ማድረግ ለሚችል ሰው ሐጅ ማድረግ ነው”

በእስልምና ሃይማኖት ለግለሰብ ወይም ለማህበረሰቡ ደህንነት የሚሆን ነገር እንደ ጥሩና ህጋዊ የሚታይ ሲሆን ለማህበረሰቡ ወይም ለግለሰብ መጥፎ ወይም ጎጅ የሆነ ነገር ደግሞ ሐራም (ክልክል) ነው።

ፈጣሪያችን አሏህ ነው፤ ለእኛ የተሻለውን ነገር እሱ ያውቃል። የእሱ ትዕዛዛትና ክልከላዎች ለሰው ልጆች መንፈሳዊ ፣ ስነልቦናዊ እና አካላዊ ደህንነት እንዲሁም ቁሳዊ ጥቅሞች አሉት። አሏህ እንዲህ ይላል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አዕራፍ 7፡157)

(በመልካም) ነገር ያዛቸዋል፤ ሙንከር (ከመጥፎ) ነገር ይከለክላቸዋል። መልካም ነገሮችን ይፈቅድላቸዋል። መጥፎ ነገሮችን ይከለክላቸዋል።

እስልምና ወደ  በጎ ተግባራቶች ሁሉ ይጣራል። ለምሳሌ እውነተኛነት ፣ ፍትሃዊነት ፣ እዝነት ፣ ፍቅር ፣ ሰላም ፣ መተሳሰብ ፣ መረዳዳት ፣ ለወላጆች ደግ መሆን ፣ ደግነት ፣ ልግስና ፣ ጠንካራ ሰራተኛነት ወ.ዘ.ተ ናቸው።

እንዲሁም ከመጥፎ ተግባራቶች ሁሉ ይከለክላል። ለምሳሌ ኢፍትሃዊነት ፣ ክፉነት ፣ ጋጠወጥነት ፣ ማጭበርበር ፣ የቅናት በሽታ ፣ ምቀኝነት ፣ ስርቆት ወ.ዘ.ተ ናቸው።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ)

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “እውነተኛ ሙስሊም ሙስሊሞችን በምላሱና በእጁ ከመጉዳት የተቆጠበ ነው። ሙሐጅር (ስደተኛ) ብሎ ማለት ደግሞ አሏህ የከለከለውን ነገር ሁሉ የተወ ነው” ብለዋል።

እውነተኛ ሙስሊም ሙስሊሞችን በምላሱና በእጁ ከመጉዳት የተቆጠበ ነው። ሙሐጅር (ስደተኛ) ብሎ ማለት ደግሞ አሏህ የከለከለውን ነገር ሁሉ የተወ ነው

አቡ ኹረይራ ባስተላለፉት ሐዲስ የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህም ብለዋል፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ትርሚዚ)

“አንድ ሰው በጎ ሙስሊም የመሆኑ ምልክት ያማይመለከተውን ነገር መተው ነው።”

በአንድ ወቅት ሱፍያን ኢብን አብዱሏህ ለነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ አለ፡

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም)

“የአሏህ መልዕክተኛ ሆይ! እሰዎን እንጅ ሌላ አንድንም ሰው ልጠይቅ የማልችልበትን ንግግር ስለ እስልምና የሆነነገር ንገሩኝ። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሲመልሱ “በአሏህ አምናለሁ በል፤ በእሱም ላይ ቀጥ በል” አሉት።

ሶላት ፣ ዘካ ፣ ሐጅ ፣ ፆም ፣ ረመዷን እና ሸሐዳ ተመልከቱ

Related posts

እስልምና እና እውቀት

የእስልምና ሃይማኖት ሁሉም ሰዎች እውቀት እንዲፈልጉ እና እውቀታቸውን እንዲጨምሩ ያበረታታል። ድንቁርናን ያወግዛል እንዲሁም ያስጠነቅቃል። አላህ እንዲህ ይላል፡- እውቀት መፈለግ ፣ መማር እና ማስተማር ወደ ጀነት

Read More »

እስልምና የሰላም ሃይማኖት

እስልምና ማለት ለአላህ መታዘዝ ፣ ትዕዛዙን በመፈጸም ላይ ጽናት ማሳየት፣ ከአላህ ሌላ ማንኛውንም አካል ከማምለክ ነፃ መሆን ማለት ነው።

Read More »
እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና እና ማህበረሰብ

እስልምና አካባቢን እንድንከባከብና እንድንጠብቅ ያዛል። በዚህም ምክንያት እስልምና በምንም መልኩ አካባቢን መበከል ይከለክላል። ጠቃሚ እፅዋት እና ዛፎችን መትከል ያበረታታል።

Read More »
እስልምና እና ጅሃድ

እስልምና እና ጅሃድ

በእስልምና ውስጥ በብዛት ሰዎች ከሚሳሳቱባቸው ቃላት አንዱ “ጅሃድ” የሚለው ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ “ጅሃድ” የሚለው ቃል አላግባብ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች ከጦርነት እና

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share