ቢሩል ዋሊደይን (ለወላጆች ደግ መሆን)

Author picture
ሙስሊሞች ለወላጆቻቸው ደግ ፣ ትሁት እና ታዛዥ እንዲሆኑ እስልምና ያዛል። ወላጆችን ያለ ማክበር ወይም ያለ መታዘዝ ምልክቶችን ማሳየት እንኳ አጥብቆ ያስጠነቅቃል።
ለወላጆች ደግ መሆን
ለወላጆች ደግ መሆን

ሙስሊሞች ለወላጆች ደግ መሆን ያዛል ፣ ትሁት እና ታዛዥ እንዲሆኑ እስልምና ያስተምራል።

ወላጆችን ያለ ማክበር ወይም ያለ መታዘዝ ምልክቶችን ማሳየት እንኳ አጥብቆ ያስጠነቅቃል። አሏህ እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

(ሱረቱል ኢስራዕ 17፡23)

“ጌታህ እሱን እንጅ ሌላን ላታመልኩ፤ ለወላጆቻችሁ መልካምን ነገር ልታደርጉ ደነገገ። በህይወትህ አንዳቸውን ወይም ሁለታቸውንም የእርጅና እድሜ ላይ በደረሱ ጊዜ ኦፍ አትበላቸው፤ አትገላምጣቸውም። ለእነሱም መልካምን ንግግር ተናገራቸው።”

ለወላጆች ደግ መሆን

ለወላጆች ደግ መሆን ፣ ትሁትና ታዛዥ መሆን አሏህ በጣም ከሚወዳቸው ስራዎች ውስጥ አንዱ የጀነት ቁልፍ ነው። ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም)

“አፍንጫው ከአፈር ውስጥ ይደባለቅ፤ አፍንጫው በአፈር ውስት ይደባለቅ፤ አፍንጫው በአፈር ውስጥ ይደባለቅ አሉ። ይህ ያልታደለ ሰው ማን እንደሆነ ተጠይቀው ሲመልሱ፤ አንዳቸውን ወይም ሁለታቸውንም ወላጆቹን በእርጅና አድሚያቸው አግኝቶ ጀነት ያልገባ ነው” ሲሉ መለሱ።

እንዲሁም አንድ ጊዜ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ሲናገሩ

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ)

“ለወላጆች አለመታዘዝን ማሳየት ትልቅ ወንጀል ሃጢያት ነው።” ብለዋል።

ወላጆቻቸውን ያልታዘዙ ሰዎችን አሏህ በፍርዱ ቀን አያያቸውም ብለዋል። (ነሳኢ)

አሏህ በትንሳኤው ቀን የሁሉንም ሃጢያቶች ቅጣት ደረጃ ይለያያል ወላጆችን ያለመታዘዝ ተግባር ሲቀር። ለዚህ ወንጀል ሃጢያተኛው የሚቀጣው በዚህም በመጭውም አለም ህይወት ነው። (አል-ሒከም)

ሙስሊሞች ወላጆቻቸው ከሞቱ በኋላ እንኳ ለእነሱ ደግ ተግባራትን ይሰሩ ዘንድ እስልምና ያዛል። አንድ ሰው ወላጆቹ ከሞቱ በኋላ ሊሰራላቸው ስለሚችለው ደግ ተግባራት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በጠየቁ ጊዜ

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(አቡ ዳውድ)

“አዎ! ዱአ አድርግላቸው፤ ለእነሱም በረካን ለምንላቸው ፣ ምህረትን ጠይቅላቸው ፣ ከሞቱ ቡኋላ የመጨረሻ ትዕዛዛቸውን ፈፅም ፣ ዝምደናቸውን ቀጥል ፣ ልጆቻቸውን አክብር” ሲሉ መልሰዋል።

ትልቅ ሃጢያት ተመልከቱ

Related posts

ስሞች እና ትርጉማቸው በእስልምና

ስሞች እና ትርጉማቸው በእስልምና

አደም (ዐ.ሰ) ከተፈጠሩ በኋላ የተሰጣቸው የመጀመሪያው ትምህርት የስሞች ዕውቀት ነበር። ይህም ከመላእክት የላቀ ደረጃ እንዲኖራቸው ያደረገ ሲሆን መላእክትም ለእርሳቸው ሱጁድ እንዲያደርጉ (እንዲሰግዱ) ምክንያት ሆኗል። ምንም

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share