የሙስሊም ሴት ሂጃብ ፡ 8ቱ ወሳኝ መስፈርቶች

Author picture
የሙስሊም ሴት ሂጃብ ትክክለኛ መስፈርቶች ምንድን ናቸው? ይህ ጽሑፍ 8ቱን የሂጃብ መስፈርቶች፣ የጌጣጌጥ ህግጋትን እና ሸሪአዊ አለባበስን ከቁርአንና ከሐዲስ አንጻር ይተነትናል።
የሙስሊም ሴት ሂጃብ ፡ 8ቱ ወሳኝ መስፈርቶች

መግቢያ

ልብስ የአላህ (ሱ.ወ) ታላቅ ጸጋ ፣ የሀፍረተ ገላ መሸፈኛና የክብር መገለጫ ነው። በተለይ የሙስሊም ሴት ሂጃብ ከዚህም የላቀ ትርጉም አለው፤ እሱም የመታዘዝ ፣ የጥበቃና የማንነት መግለጫ ነው። ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት “ሂጃብ” በሚል ስም የሚለበሱ ሁሉ ሸሪዓው ያስቀመጠውን መስፈርት ያሟላሉ?

ይህ ጽሑፍ የሂጃብን ትክክለኛ ዓላማ ፣ ለማህበረሰብ የሚሰጠውን ጥበቃ እና አንድ አለባበስ “ሸሪአዊ ሂጃብ” ተብሎ እንዲጠራ ሊያሟላቸው የሚገቡ 8 ወሳኝ መስፈርቶችን ከቁርአንና ከሐዲስ ማስረጃ ጋር በዝርዝር ይተነትናል። አለባበስሽ የአላህን ትዕዛዝ ያሟላ መሆኑን እዚህ አረጋግጪ።

ልብስ ፡ የአላህ ጸጋ እና የሸሪዓ ዓላማዎች

ልብስ አላህ (ሱ.ወ) ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ታላላቅ ጸጋዎች (ኒዕማዎች) አንዱ ነው። በልብስ አማካኝነት የሰው ልጅ ሀፍረተ ገላውን ይሸፍናል ፣ ከሙቀትና ከቅዝቃዜ ራሱን ይከላከላል፤ እንዲሁም ለመዋቢያና ማጌጫ ይጠቀምበታል።

አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ብሏል፡-

አል-ቁርአን

ሱረቱል አዕራፍ 26

“የአደም ልጆች ሆይ! ሀፍረተ ገላችሁን የሚሸሽግን ልብስ ጌጥንም በእርግጥ በእናንተ ላይ አወረድን። አሏህንም የመፍራት ልብስ የተሻለ ነው። ይህ ከአሏህ ተአምራቶች ነው። ይገሰፁ ዘንድ (አወረደላቸው)።”

ልብስ ለሁሉም ወንድ እና ሴት በጣም አስፈላጊ ነገር ነው። ሃፍረተ ገላን የሚሸፍነው ይሄው ነው። ለተለያዩ አጋጣሚዎች እና ሁነቶች ማለትም ለሰርግ ፣ ለድግስ እና መሰል ነገሮች የምንገለገልበት ማጌጫ እና መዋቢያ የሚመጣው ከዚሁ ነው።

በተለይ ከሴቶች አልባሳት ጋር በተያያዘ ሸሪዓችን ያስቀመጣቸው ውሳኔዎች ትልቅ ግቦችን ያሳካሉ።

ለሴቷ፡ የግል ክብሯ እንዲጠበቅ ፣ ከወንዶች አላስፈላጊ እይታ እንድትከለል እና ከባለጌዎች ጥቃት እንድትድን ያደርጋታል።

ሸሪዓውን የተከተለ አለባበስ ሰላም ፣ መረጋጋት እና ክብርን ያጎናጽፋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ ለአላህ ትዕዛዝ መተናነስንና ባርነትን መግለጫ ነው።

ለማህበረሰቡ፡ የሙስሊም ሴት ሂጃብ ማህበረሰቡን ከፈተና ይጠብቃል ፣ ለሁሉም አባላት መረጋጋትንና ደህንነትን ያሰፍናል። የሂጃብ መጥፋት የቤተሰብን አወቃቀር ያናውጣል፤ ይህ ደግሞ ዛሬ በብዙ ሐገራት የሚታይ አሳዛኝ ክስተት ነው።

የሙስሊም ሴት ሂጃብ 8ቱ ወሳኝ መስፈርቶች

አንድ አለባበስ ትክክለኛ “ሸሪአዊ ሂጃብ” ተብሎ እንዲጠራ የሚከተሉትን ስምንት ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት ይኖርበታል፡-

1. ሙሉ አካልን የሚሸፍን መሆን

የሂጃብ መስፈርት የመጀመሪያው መላ ሰውነትን መሸፈን ነው። አላህ (ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

አል-ቁርአን

ሱረቱል አህዛብ፡ 59

“ነብዩ ሆይ! ለሚስቶችህ፣ ለሴት ልጆችህ፣ ለምዕመናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው። ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመሆን በጣም የቀረበ ነው።”

ማሳሰቢያ፡ ፊትን እና እጅን መሸፈንን በተመለከተ በኢስላም ሊቃውንት (ዑለማኦች) መካከል ልዩነት አለ። አንዳንዶቹ እንደሌላው ሰውነት ሁሉ ግዴታ ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ ግዴታ ባይሆንም እጅግ የተወደደ (ሙስተሐብ) ተግባር እንደሆነ ይገልጻሉ።

2. በራሱ ጌጥ ያልሆነ መሆን

የሂጃቡ ዓላማ ጌጥን መሸፈን እንጅ እሱ ራሱ አይን የሚስብ ጌጥ መሆን የለበትም። አላህ (ሱ.ወ) “ጌጣቸውንም አይግለጡ” (ሱረቱ ኑር፡ 31) ብሏል። ይህ ትዕዛዝ በሂጃቡ ላይም ተፈጻሚ ይሆናል።

3 & 4. ብርሃን የማያስተላልፍ (ወፍራም) እና ሰፊ መሆን

ሂጃቡ ከስር ያለውን የሰውነት ቅርፅ የሚያሳይ (ብርሃን የሚያስተላልፍ) መሆን የለበትም። እንዲሁም የሰውነትን ቅርጽ የሚያሳይ የሚያጣብቅ ሳይሆን ሰፋ ያለና ቅርጽን የሚደብቅ መሆን አለበት።

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ሙስሊም 2128)

“ያላየኋቸው ሁለት አይነት የጀሃነም ሰዎች አሉ… (ሁለተኛዎቹ) የለበሱ የሚመስሉ ነገር ግን የተራቆቱ… ሴቶች ናቸው።… ጀነት አይገቡም፤ ማዕዛዋንም አያሸቱም…”

ኡሳማ ቢን ዘይድ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለሚስታቸው የሰጧትን ወፍራም ካባ አስመልክተው

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(አህመድ 21786)

“ከስር ቀሚስ እንድታደርግ ንገራት፤ የአጥንቷ ፍላጫ (የሰውነቷ ቅርፅ) እንዳይገለጥ እፈራለሁና” ብለዋል።

5. ሽቶ ያልተነሰነሰበት መሆን

አንዲት ሴት ከቤቷ ስትወጣ አጅነቢ (መህረም ያልሆነ) ወንድ ጋር የምትገናኝ ከሆነ፤ የወንዶችን ስሜት የሚቀሰቅስ ሽቶ መቀባት የለባትም።

የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡-

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

ነሳኢ 5126

“ሰዎች ጠረኗን ያሸቱ ዘንድ ሽቶ ነስንሳ በሰዎች በኩል የምታልፍ ሴት አመንዝራ (ዝሙተኛ) ናት።”

6. ከወንዶች አልባሳት ጋር የማይመሳሰል መሆን

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ቡኻሪ 5885)

ኢብን አባስ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፉት “የአላህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ሴቶችን የሚመሳሰሉ ወንዶችን እና ወንዶችን የሚመሳሰሉ ሴቶችን ረግመዋል።”

7. ከከሃዲያን ሴቶች አልባሳት ጋር የማይመሳሰል መሆን

ሙስሊሞች (ወንድም ሆኑ ሴት) በአምልኳቸውም ሆነ በአለባበሳቸው ከከሃዲያን ጋር መመሳሰል የለባቸውም።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(አቡዳውድ 4031)

ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) “ከሰዎች የተመሳሰለ እሱ እራሱ ከእነሱ አንዱ ነው” ብለዋል።

8. መጥፎ ስምና ዝና ያላቸው ሰዎች መገለጫ ያልሆነ መሆን አለበት

ይህ ማለት በሰዎች መካከል ለመታወቅ ፣ ለመኩራራት ወይም በእብሪት ለመታየት ተብሎ የሚለበስ እንግዳ የሆነ ወይም እጅግ ውድ የሆነ አለባበስን ይመለከታል።

ይህ የዝና ልብስ ከሰዎች መካከል ዝነኛ ተብለው በመጥፎ ስራቸው የሚታወቁ ሰዎች ልብስ ሁሉ ነው።

ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)

(ኢብን ማጃ 3607)

የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል፡ ‹‹በዚህ አለም ውስጥ (የኩራት እና የእብሪት ልብስን የተከናነበ ሰው በትንሳኤው ቀን አሏህ የውርደት ልብስን ያከናንበዋል። ከዚያም በእሳት ያያይዘዋል።››

ሸሪአዊ አለባበስ ፡ ለማን እና የት?

ከላይ የተገለጹት 8ቱ የሂጃብ መስፈርቶች አንዲት ሙስሊም ሴት ከቤት ስትወጣ ወይም መህረሞቿ ካልሆኑ (አጅነቢ) ወንዶች ፊት ስትሆን ልትከተለው የሚገባ የአለባበስ ስርዓት ነው።

አንዲት ሴት መህረሟ ካልሆኑ ሰዎች ፊት ጌጧን እና ውበቷን ከእነሱ መደበቅ አለባት።

የሙስሊም ሴት አለባበስ ከፊቷ ያሉትን ሰዎች ከግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት

  1. ከእንግዶች ፊት ስትሆን የሚኖራት አለባበስ (መህረም ያልሆኑ)
  2. ከወንድ ዘመዶቿ ፊት ስትሆን የምትለብሰው አለባበስ
  3. ከሌሎች ሙስሊም ሴቶች ጋር ስትሆን የሚኖራት አለባበስ
  4. ከአህለል ኪታብ (ከመጽሐፉ ሰዎች) ሴቶች ጋር ስትሆን የሚኖራት አለባበስ

ከእንግዶች ፊት ስትሆን የሚኖራት አለባበስ

አንዲት ሴት በመህረሞቿ (ለጋብቻ ከተከለከሉባት) ፊት ወይም ከሌሎች ሙስሊም ሴቶች ጋር በምትሆን ጊዜ እነዚህን ጥብቅ መስፈርቶች ማሟላት አይጠበቅባትም።

ብዙውን ጊዜ በስራ ወቅት ግልጽ የሚሆኑትን ክፍሎች (እንደ ፊት ፣ እጅ ፣ አንገት ፣ ፀጉር እና እግር) መግለጥ ይፈቀድላታል።

አንዲት ሴት ልትከተለው የሚገባ የአለባበስ ስርአት ሃያሉ አሏህ እና መልዕክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) ያዘዙት እና ቅድመ ሁኔታዎቹ ቀደም ብሎ የተገለፁት ሸሪአዊ የሂጃብ የአለባበስ ስርአት ነው።

አንዲት ሙስሊም ሴት ከወንድ ዘመዶቿ ፊት ስትሆን ሊኖራት የሚገባ አለባበስ

ከወንድ ዘመዶቿ ፊት በምትሆን ጊዜ ባብዛሃኛው ግልፅ ከሚሆነው ለምሳሌ አንገቷ ፣ ፀጉሯ እና እግሮቿ እንዲሁም ፊቷ እና እጆቿ በቀር ሙሉ አካሏን መሸፈን አለባት። አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

ሱረቱ ኑር 31

“ለምዕመናን ንገራቸው! አይኖቻቸውን ይከልክሉ። ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ። ጌጣቸውንም ከእሷ ግልፅ ከሆነው በስተቀር አይግለጡ። ጉፍታዎቻቸውንም በአንገታቸው ላይ ያጣፉ። (የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንድ ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንድ ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንድ ልጆች…አይግለጡ።”

አንዲት ሙስሊም ሴት ከሌሎች ሙስሊም ሴቶች ጋር በምትሆን ጊዜ የሚኖራት አለባበስ

መህረም ወንዶች በሚኖሩበት ጊዜ እንደምታደርገው ሁሉ መላ አካላቷን ትሸፍናለች። ያ ብዙ ጊዜ የሚገለጠው ወይም የሚታየው አንገቷ ፣ ፀጉሯ ፣ እግሮቿ እና እንዲሁም ፊቷ እና እጆቿ ሲቀሩ። አሏህ እንዲህ አለ፡

አል-ቁርአን

ሱረቱ ኑር 31

“ለምዕመናን ንገራቸው! አይኖቻቸውን ይከልክሉ። ብልቶቻቸውንም ይጠብቁ። ጌጣቸውንም ከእሷ ግልፅ ከሆነው በስተቀር አይግለጡ። ጉፍታዎቻቸውንም በአንገታቸው ላይ ያጣፉ። (የውስጥ) ጌጣቸውንም ለባሎቻቸው ወይም ለአባቶቻቸው ወይም ለባሎቻቸው አባቶች ወይም ለወንድ ልጆቻቸው ወይም ለባሎቻቸው ወንድ ልጆች ወይም ለወንድሞቻቸው ወይም ለወንድሞቻቸው ወንድ ልጆች ወይም ለእህቶቻቸው ወንዶች ልጆች ወይም ለሴቶቻቸው… አይግለጡ።”

አንዲት ሙስሊም ሴት ከመጽሐፉ ሴቶች ጋር በምትሆን ጊዜ የሚኖራት የአለባበስ ስርአት

ከሙስሊም ሴቶች ጋር በምትሆን ጊዜ እንደሚኖራት የአለባበስ ስርአት መላ አካላቷን ትሸፋፍናለች። ያ ግልፅ የሆነው ሲቀር። ለምሳሌ አንገቷ ፣ ፀጉሯ ፣ እግሮቿ ፊቷ እና እጆቿ ናቸው።

ይህ ምክኒያቱም የመጽሐፉ ሰዎች ሴቶች ከምዕመናን እናቶች ቤት ይገቡ የነበረ መሆኑ እና ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ከእነሱ እንዲሸፋፈኑ ስላላዘዙ ነው።

ስለ ጌጣጌጥ እና ሜካፕ የተሰጡ ህግጋት (ሴቶች እና ጌጣጌጥ በእስልምና)

አንዲት ሴት መህረሟ ካልሆኑ ሰዎች ፊት ጌጧን እና ውበቷን (ሜካፕን ጨምሮ) ከእነሱ መደበቅ አለባት።

1. የተፈቀዱ (ሙባህ) አልባሳት እና ጌጣጌጦች

በሸሪዓችን መሰረት ሁሉም የአልባሳት እና የጌጣጌጥ አይነቶች የተከለከለ መሆኑን የሚገልጽ መረጃ እስካልመጣ ድረስ የተፈቀዱ (ሙባህ) ናቸው።

  • ሴት ማንኛውንም አይነት ቀለም እና የጨርቅ አይነት መልበስ ትችላለች (ከላይ ያሉትን 8 መስፈርቶች እስካሟላ ድረስ)።
  • በተፈቀዱ ጌጣጌጦች ፣ ሽቶ እና ኮስሞቲክሶች እራሷን ማስዋብ ትችላለች።
  • እነዚህ ነገሮች እሷን የማይጎዱ ፣ ከከሃዲያን ጋር የማያመሳስሉ እና ከተከለከሉ ነገሮች (እንደ አሳማ ስብ) ያልተሰሩ መሆን አለባቸው።

2. የተወደዱ (ሙስተሐብ) አልባሳት እና ጌጣጌጦች

ይህ ሸሪአ ያበረታታው እና የተወደደ ነው ብሎ የጠቀሰውን ማንኛውንም ነገር እና አንዲት ሴት ባሏን ለማስደሰት እና ለማማለል የምትለብሰው እና የምትዋብበትን ያልተከለከለ ማንኛውም ነገር ነው።

3. የተከለከሉ አልባሳት እና ጌጣጌጦች

ይህ ማለት ሸሪአ የከለከለው እና በእሱ ላይ ያስጠነቀቀው ማንኛውም አይነት አልባሳት እና ጌጣጌጥ ነው። አሏህ ያዘዘውን መታዘዝ ፣ የከለከለውን መከልከል አለባት።

ይህ ደግሞ አይሁዶች እና ክርስቲያኖች ከሚያደርጉት የተለየ ነገር ማድረግ እና ከወንዶች ጋር አለመመሳሰል ወ.ዘ.ተ ነው።

ማጠቃለያ

የሙስሊም ሴት ሂጃብ የአላህን ትዕዛዝ መፈጸሚያ ፣ የክብር ጥበቃና የማህበረሰብ መረጋጊያ ነው። ሸሪዓው ያስቀመጣቸውን 8 መስፈርቶች ማሟላቱ ፣ ከአለባበስ ባለፈ የመታዘዝ ተግባር ነው።

ይህ ማለት ሂጃቡ ሰፊ ፣ ወፍራም ፣ ጌጥ ያልሆነ ፣ ሽቶ የሌለው ፣ ከወንዶችም ሆነ ከካፊሮች ልብስ ጋር የማይመሳሰል መሆን አለበት።

እውነተኛውን ሸሪአዊ የአለባበስ ስርዓት መረዳት እያንዳንዷ ሙስሊም እህት ክብሯን እንድትጠብቅና የአላህን ውዴታ እንድታገኝ ይረዳታል።

እርስዎስ በዘመናችን ያሉ አለባበሶች ከእነዚህ ሸሪአዊ መስፈርቶች አንጻር እንዴት ይመለከቷቸዋል? አስተያየትዎን ከታች ያጋሩን።

0%
7
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ሙስሊም ቤተሰብ

ጥያቄና መልስ፡ የሙስሊም ሴት አልባሳት

‹‹የሙስሊም ሴት አልባሳት›› የሚለው ትምህርት ፈተና 6 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 5 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 6

Bookmark question icon

1 ተበሩጅ ማለት መህረም ካልሆኑ ወንዶች ፊት መደበቅ (መሸሸግ) የምትገደደውን ውበቷን እና ጌጧን ገልጣ ማሳየት ነው።

2 / 6

Bookmark question icon

2 ሴቶች ፊታቸውን እና እጃቸውን መህረም ካልሆኑ ወንዶች ፊት ስትሆን መሸፈን የሚገባቸው ስለመሆኑ በተመለከተ ሊቃውንት በዚህ ሃሳብ ተለያይተዋል። በዚህ ዙሪያ ሁለት ሃሳቦች አሉ። እነሱም፡-

3 / 6

Bookmark question icon

3 የሙስሊም ሴት አልባሳት በተመለከተ ሊከተሏቸው ከሚገቡ ሸሪአዊ ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ

4 / 6

Bookmark question icon

4 ትክክለኛውን መልስ ወይም መልሶች ምረጥ፡ የእስልምና ህግ ከሙስሊም ሴቶች አለባበስ ጋር በተያያዘ በህጋዊ ድንጋጌዎች እና ደንቦች አማካኝነት ______ ይፈልጋል።

5 / 6

Bookmark question icon

5 ትክክለኛውን መልስ ወይም መልሶች ምረጥ፡ ሙስሊም ሴቶች መልበስ ከማይፈቀድላቸው አልባሳት መካከል የትኞቹ ናቸው?

6 / 6

Bookmark question icon

6 አንዲት ሙስሊም ሴት ከአህሉል ኪታብ (ከመጽሐፉ ሰዎች) ሴቶች ጋር በምትሆን ጊዜ ማሳየት የሚፈቀድላት የአካል ክፍል

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 14%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

ሴቶች እና እስልምና

ሴቶች እና እስልምና

በእስልምና ወንዶች እና ሴቶች የተለያየ ባህሪ ያላቸው ሲሆን እያንዳንዳቸውም የራሳቸው ሚና አላቸው። በእስልምና ሴቶችን ማክበር መልካም እና ምስጉን ባህሪ እንዲሁም ያልተበረዘ ተፈጥሮ ምልክት ነው።

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share