እስልምና ሴትን ልጅ ከጉዳት እና ከወንዶች የዥሙት እይታ ሊከላከላት ይሻልና ሙሉ ሰውነቷን የሚሸፍን ሂጃብ በመልበስ ጨዋነቷን እንድትጠብቅ አዟል። ሙስሊም ሴት ሂጃብ የምትለብሰው አሏህ በቁርአኑ ስላዘዛት ነው።
ሂጃብ

እስልምና ሴትን ልጅ ከጉዳት እና ከወንዶች የዥሙት እይታ ሊከላከላት ይሻልና ሙሉ ሰውነቷን የሚሸፍን ሂጃብ በመልበስ ጨዋነቷን እንድትጠብቅ አዟል። አሏህ በቁርአኑ እንዲህ ብሏል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱል አህዛብ 33፡59)

አንተ ነብይ ሆይ! ለሚስቶችህ ፣ ለሴት ልጆችህ እና ለሙእሚኖች ሴቶች መከናነቢያ አይነ እርግባቸውን በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው። ይህ እንዲታወቁና እንዳይደፈሩ ለመሆን በላጭ ነው።”

እንዲህም ብሏል፡

አል-ቁርአን

(ሱረቱ ኑር 24፡31)

ጌጣቸውን ያ ግልፅ ከሆነው በቀር አይግለጡ

ሙስሊም ሴት ሂጃብ የምትለብሰው አሏህ በቁርአኑ ስላዘዛት ነው፤ እንዲሁም ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) እንድትለብስ በማዘዛቸው ምክኒያት ነው። ሂጃብ መልበስ አሏህን መታዘዝ ነው። የንፅህና ፣ የጨዋነት እና የኢማን ምልክት ነው። ሒጃብ የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት አለበት።

ሂጃብ
  1. ሙሉ አካልን መሸፈን አለበት
  2. ሰውነትን የሚያጣብቅ ወይም አካልን የሚያሳይ መሆን የለበትም
  3. የአካል ክፍል እንዳይታይ ላላ ብሎ መንጠልጠል አለበት
  4. የወንዶችን ልብስ መምሰል የለበትም
  5. የወንዶችን ትኩረት የሚሥብ ምንም አይነት የአሰራር ጌጥ ወይም የሰውነት ቅርፅ የማያወጣ መሆን አለበት
  6. ሙስሊም ካልሆኑ ሴቶች  ልብስ ጋር የሚመሳሰል መሆን የለበትም

ሒጃብ መልበስ ባህላዊ ልማድ አይደለም። ይልቁንም ለባሮቹ የተሻለውን ነገር የሚያውቀው ሃያሉ አሏህን የመታዘዝ መገለጫ ነው። በሙስሊሙ አለም ውስጥ የሚኖሩ አንዳንድ ሴቶች ሒጃብ መለኮታዊ ትዕዛዝ መሆኑን የማያውቁ አይለብሱትም።

አንዳንዶቹ ደግሞ ባህላዊ ልምድ እና ማህበራዊ ሸህም እንደሆነ ያምናሉ፤ አይለብሱምም።

 አንዳንዶቹ ሐገራቸው ውስጥ ሲሆኑ ይለብሳሉ። ነገርግን ከሐገር ውጭ ወጥተው ሲሄዱ ደግሞ ያወልቁታል።

ሴቶች በእስልምና ልዩ እንክብካቤ እና ጥበቃ እንደሚፈልግ እንቁ አልማዝ ናቸው።

ሴቶች በእስልምና ልዩ እንክብካቤ እና ጥበቃ እንደሚፈልግ እንቁ አልማዝ ናቸው። ያለምንም ጥርጥር ሂጃብ ሴቶች እራሳቸውን የሚጠብቁበት እጅግ በላጩ መንገድ ነው። በእርግጥ ክብሯን እና መልካም ምግባሯን እንድትጠብቅ ይረዳታል።

ሂጃብ የምትለብስ ሙስሊም ሴት የተከበረች ፣ ጨዋ ፣ ጥሩ አህላቅ መልካም ምግባር የተላበሰች በመጭው አለም ህይወት የትለቅ ምንዳ ባለቤት ናት።

0%
7
Question report close icon

Report a question

You cannot submit an empty report. Please add some details.
Question report loader icon
Created by Ahmed Yesuf

ሙስሊም ቤተሰብ

ጥያቄና መልስ፡ የሙስሊም ሴት አልባሳት

‹‹የሙስሊም ሴት አልባሳት›› የሚለው ትምህርት ፈተና 6 ጥያቄዎችን ይዟል። ፈተናውን ለማለፍ 5 ጥያቄዎችን በትክክል መመለስ አለባችሁ።

1 / 6

Bookmark question icon

1 ተበሩጅ ማለት መህረም ካልሆኑ ወንዶች ፊት መደበቅ (መሸሸግ) የምትገደደውን ውበቷን እና ጌጧን ገልጣ ማሳየት ነው።

2 / 6

Bookmark question icon

2 ሴቶች ፊታቸውን እና እጃቸውን መህረም ካልሆኑ ወንዶች ፊት ስትሆን መሸፈን የሚገባቸው ስለመሆኑ በተመለከተ ሊቃውንት በዚህ ሃሳብ ተለያይተዋል። በዚህ ዙሪያ ሁለት ሃሳቦች አሉ። እነሱም፡-

3 / 6

Bookmark question icon

3 የሙስሊም ሴት አልባሳት በተመለከተ ሊከተሏቸው ከሚገቡ ሸሪአዊ ቅድመ ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ

4 / 6

Bookmark question icon

4 ትክክለኛውን መልስ ወይም መልሶች ምረጥ፡ የእስልምና ህግ ከሙስሊም ሴቶች አለባበስ ጋር በተያያዘ በህጋዊ ድንጋጌዎች እና ደንቦች አማካኝነት ______ ይፈልጋል።

5 / 6

Bookmark question icon

5 ትክክለኛውን መልስ ወይም መልሶች ምረጥ፡ ሙስሊም ሴቶች መልበስ ከማይፈቀድላቸው አልባሳት መካከል የትኞቹ ናቸው?

6 / 6

Bookmark question icon

6 አንዲት ሙስሊም ሴት ከአህሉል ኪታብ (ከመጽሐፉ ሰዎች) ሴቶች ጋር በምትሆን ጊዜ ማሳየት የሚፈቀድላት የአካል ክፍል

የተሳታፊ መረጃ

Your score is

The average score is 14%

0%

ለሰጡን ሀሳብ አስተያየት እናመሰግናለን!

Related posts

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share