እስልምና ተከታዮቹ ጥሩ ስነምግባር ወይም ውብ አህላቅ እንዲላበሱ ጥሪ ያደርጋል። አሏህ መልዕክተኛውን (ሰ.ዐ.ወ) ሲገልፅ እንዲህ ይላል፡-
አል-ቁርአን
(ሱረቱል ቀለም 68፡4)
“በእርግጥ በታላቅ ምግባር ላይ ነህ።”
ብዙ የቁርአን አንቀፆች ሙስሊሞች ጥሩ አህላቅ እንዲኖራቸው ያበረታታል። አሏህ እንዲህ ይላል፡-
አል-ቁርአን
(ሱረቱል በቀራ 2፡83)
“ለሰዎችም መልካምን ነገር ተናገሩ”

ሰዎችን ወደ መልካም ምግባር ወይም ባህሪ ሚጣሩ ብዙ ነብያዊ ሐዲሶች አሉ። የሚከተሉት ጥቂት ምሳሌዎች ናቸው።
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ትርሚዚ)
“የትም ቦታ ብትሆኑ አሏህን ፍሩ፤ መጥፎ ስራን በመልካም አስከትሉ፤ ያጠፋዋልና። ለሰዎችም መልካምን አድርጉ።”
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ሙስሊም)
“በአሏህና በመጨረሻው ቀን ያመነ መልካም ነገር ይናገር ወይም ዝም ይበል። በአሏህ እና በመጨረሻው ቀን ያመነ ጎረቤቱን ያክብር። በአሏህና በመጨረሻው ቀን ያመነ እንግዳውን ያክብር።”
ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)
(ቡኻሪና ሙስሊም)
“አንዳችሁም አላመናችሁም ለእራሱ የወደደውን ነገር ለወንድሙም እስካልወደደ ድረስ።”

“በፍረርዱ ቀን የሙዕሚኖች ሚዛን ላይ የሚቀመጠው ከባዱ ነገር ጥሩ ባህሪ ይሆናል። አሏህም ፀያፍ ስድብና የብልግና ቃል (ንግግር) ይጠላል።” (ትርሚዚ)
“ በፍርዱ ቀን ከእናንተ መካከል ለእኔ በጣም ተወዳጁና ቅርብ የሆኑት ምስጉን ባህሪ (ምግባር) ያላቸው ናቸው።” (ትርሚዚ)

አኢሻ (ረ.ዐ) ስለ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ባህሪ ተጠይቃ ስትመልስ “ባህሪው የቁርአን ባህሪ ነው። ባህሪው ቁርአን ነው።” ብላ ነበር። ይህ ማለት የቁርአን አስተምህሮቶች ሰርተውበቸዋል፤ ኑረውበታል ማለት ነው።

