በንባብ ጊዜ ልናዳብራቸው የሚገቡ ነገሮች

Author picture
ንባብ በህይወታችን ልናዳብረው እና ልናሳድገው የሚገባ እጅግ ጠቃሚ ክህሎት ሲሆን ጠቀሜታውም በትምህርታችን ወይም በተሰማራንበት የስራ ዘርፍ ስኬታማ ለመሆን ወሳኝ ክህሎት ነው።

ንባብ በህይወታችን ልናዳብረው እና ልናሳድገው የሚገባ እጅግ ጠቃሚ ክህሎት ሲሆን ጠቀሜታውም በትምህርታችን ወይም በተሰማራንበት የስራ ዘርፍ ስኬታማ ለመሆን ብቻ ሳይሆን በዕለት ተዕለት ኑሯችን ስኬታማ ለመሆን ወሳኝ ክህሎት ነው።

የሚከተሉት ጠቃሚ ነጥቦች የንባብ ጊዜያችነን እና የንባብ ክህሎታችነን ለማሳደግ የሚረዱን ናቸው።

  • ማንበብ የሚያስደስተንን ነገር እና ሊጠቅመን የሚችል ነገር ለይተን እንወቅ
  • ቋሚ የንባብ ወይም የጥናት ጊዜ ይኑረን
  • አዘውትረን ወደ ላይብረሪዎች ጐራ እንበል
  • የኔ የምንላቸው መጽሐፍት ይኑሩን
  • አዲስ የሆነን ነገር ለማወቅ ጉጉት ይኑረን
  • የአንድ ፅሁፍ ሃሳብ ሊገባን ወይም ትርጉም ሊሰጠን ካልቻለ እውቀት ያለው ሰው እንዲገልፅልንና እንዲያብራራልን እንጠይቅ
  • ሃሳቡን ከተረዱት ሰዎች ከአስተማሪዎቻችን ጋርም ሆነ ከጎደኞቻችን ጋር እንወያይበት
  • ቁልፍ የሆኑ ሃሳቦችን በማስታወሻ እንያዝ
  • ጥያቄ እጥር ምጥን ባለመልኩ የመጠየቅ ልምድ ይኑረን
  • በማስታወሻ የያዝናቸውን ነጥቦች ከልሰን በማየት ያልገባንን ነገር በጥያቄ መልክ በማቅረብ ለበለጠ ንባብ እራሳችነን እናዘጋጅ
  • የምናነበውን ነገር መፃፋችን እንድናስታውሰው ይረዳናነልና እየያነበብን እንፃፍ
  • ያነበብነውን ነገር ምን ያህል እንደተረዳ ነው ለማወቅ እራሳችነን የተወሰኑ ጥያቄዎችን እንጠይቅ

Related posts

ሸሃዳ የእምነት ምስክርነት ቃል

ሸሃዳ የእምነት ምስክርነት ቃል

ሸሃዳ ማለት የእምነት ምስክርነት ቃል ነው። ላኢላሃ ኢለሏህ (ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም) ማለት ከአሏህ ውጭ በሃቅ ሊያመልኩት የሚገባ ሌላ አምላክ የለም ማለት ነው።

Read More »
መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች

መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች፡ ሕይወትን በእስልምና ፣ በቁርአን እና በሱና መሰረት መኖር

ውድ ሙስሊም ወጣቶች! በዚህ ወሳኝ የሕይወት ምዕራፍ ላይ የምትገኙ ሙስሊም ወጣቶች ልባዊ ሰላምታችን እና ውዴታችን ይደረሳችሁ። ይህ ጊዜ የብርታት፣ የጉጉት፣ የእውቀት ፍለጋ እና ለወደፊት ህይወታችሁ

Read More »
ጀነት

ጀነት

ጀነት ሃያሉ አሏህ ለደጋግ ባሮቹ ያዘጋጀው ዘላለማዊ የደስታ ቤት ነው፡፡ ይህ ዘላለማዊ ደስታ አይን አይቶት ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅ ነው፡፡ ጀነት የሚገቡ ሰዎች የፈለጉትን ፣

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share