ህይወትዎን የሚቀይሩ ወርቃማ ኢስላማዊ ምክሮች

Author picture
ከዱንያ ጭንቀት ወደ ልብ ብርሃን የሚመሩ ፣ ከደጋግ ቀደምቶች የተገኙ ጥበብ አዘል ኢስላማዊ ምክሮች። የነፍስዎን ጥማት ለማርካት ይህን ያንብቡ።

መግቢያ

በዚህ ዓለም የህይወት ውጣ ውረድ እና ግርግር ውስጥ ልባችን እረፍትና መረጋጋትን ስትሻ ፣ አይናችንም የእውነትን ብርሃን ስትፈልግ ፣ ከምንጩ ያልደፈረሰውን ጥበብ መጎንጨት ብርታትንና ጥልቅ መመሪያን ይሰጣል። ይህ ጽሑፍ ተራ የቃላት ስብስብ ሳይሆን በእስልምና ወርቃማ ዘመን የነበሩ ፣ አላህን በመፍራት እና እሱን በመታዘዝ ህይወታቸውን የኖሩ ታላላቅ ሶሃቦች ፣ ታቢዒዮች እና ሊቃውንት የተናገሯቸው ወርቃማ ኢስላማዊ ምክሮች በማስተዋል ይመርምሩ።

እነዚህ ንግግሮች ከሺህ ዓመታት በፊት ቢነገሩም ፣ ዛሬም ድረስ ላለነው ትውልድ ህያውና ወቅታዊ መልእክት ያስተላልፋሉ። እያንዳንዱ ሐረግ የህይወትን ትርጉም ፣ የዓላማን ምንነት ፣ የዱንያን አላፊነት እና የአኼራን ዘላለማዊነት ያስታውሰናል።

ከ አቡበክር አሲዲቅ (ረ.ዐ) ትህትና እስከ ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ (ረ.ዐ) ፍትህ ፣ ከኡስማን ኢብን አፋን (ረ.ዐ) ልግስና እስከ አሊ ኢብኑ አቢ ጧሊብ (ረ.ዐ) ጥበብ እንዲሁም እንደ ኢብኑ ተይሚያ እና ኢብኑል ቀይም ያሉ የተከበሩ ሊቃውንት ጥልቅ ዕውቀት የተጨመቁትን እነዚህን የጥበብ ጠበሎች ስናነብ ፣ ህይወታችንን የምንመዝንበት መስታወት እና ስብዕናችንን የምንቀርጽበት መሳሪያ እናገኛለን።

እንግዲህ ልብዎን ክፍት በማድረግ እና ለማስተዋል በጠራ አዕምሮ ወደዚህ የጥበብ ማዕድ እንዲገቡ እጋብዝዎታለሁ።

ወርቃማ ኢስላማዊ ምክሮች

  1. ትንሽ ስራ በኒያ (በሐሳብ) ትልቅ ይሆናል፤ ትልቅ ስራ ደግሞ በኒያ ትንሽ ይሆናል።

                                     አብደላህ ኢብኑ ሙባረክ (ረሂመሁላህ)

  1. ከመመርመራችሁ በፊት እራሳችሁን መርምሩ፤ ከመመዘናችሁ በፊት (ስራችሁን) መዝኑ።

                                     ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ (ረ.ዐ)

  1. በእርግጥ በእናንተ ላይ በጣም የምፈራላችሁ ስሜትን መከተልና ረጅም ምኞት ነው። ስሜትን መከተል ከእውነት ያግዳል። ረጅም ምኞት ደግሞ አኼራን (የወዲያኛውን አለም) ያስረሳል።

                                     አሊ ኢብን አቢ ጧሊብ (ረ.ዐ)

  1. የአደም ልጅ ምስኪን ነው! ድህነትን እንደሚፈራው እሳትን ቢፈራ ኖሮ ጀነት በገባ ነበር።

                                     የህያ ኢብኑ ሙዓዝ (ረሂመሁላህ)

  1. ቀልብ የአሏህን ኢባዳ (አምልኮ) እና አምልኮን ለእርሱ ብቻ የማድረግን (ኢኽላስ) ጣዕም ካጣጣመች፤ ከእርሱ የበለጠ ጣፋጭ ፣ ጥሩ እና ተወዳጅ ነገር አታገኝም።

                                     ኢብኑ ተይሚያ (ረሂመሁላህ)

  1. ለአማኝ ሰው ከአሏህ (ሱ.ወ) ጋር ከመገናኘት ውጭ እረፍት የለውም።

                                     አብደላህ ኢብኑ መስኡድ (ረ.ዐ)

  1. ኢብኑ አባስ ምላሱን ይዞ “ወዮልህ! መልካምን ተናገር ትጠቀማለህ፤ ወይም መጥፎ ነገር ከመናገር ዝም በል ትድናለህ” ሲል አየሁት።

                                     ኢብኑ ቡረይዳ (ረሂመሁላህ)

  1. ጊዜ ማባከን ከሞት የከፋ ነው! ምክንያቱም ጊዜ ማባከን ከአሏህና ከወዲያኛው አለም ያቆራርጣል፡፡ ሞት ግን ከዱንያና ከሰዎቿ ብቻ ያቆራርጣል።

                                     ኢብኑል ቀይም አልጀውዚያ (ረሂመሁላህ)

  1. ጤነኛ ሆኖ ከማመሰግንን ተፈትኖ ከምታገስ እመርጣለሁ።

                                     አቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ)

  1. የዱአ ምላሽ ምንይሆን ብየ አልጨነቅም፡፡ የምሸከመው የዱአውን ጭንቀት ነው፡፡ ዱአ ከተሰጠሁኝ ምላሹ ከእርሱ ጋር ነው።

                                     ኡመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.ዐ)

  1. የዱንያ ጭንቀት ልብ ውስጥ እንዳለ ጨለማ ነው፡፡ የአኼራ ጭንቀት ደግሞ የልብ ብርሃን ነው።

                                     ኡስማን ኢብኑ አፋን (ረ.ዐ)

  1. ከሰዎች ጋር ስትኖሩ ብትሞቱ የሚያለቅሱላችሁ ፣ በህይወት ስትኖሩ የሚናፍቋችሁ አይነት ሰዎች ጋር ጥሩ አኗኗር ኑሩ።

                                     አሊ ኢብኑ አቢ ጧሊብ (ረ.ዐ)

  1. ሁሉንም ነገር አሏህን ለምኑ፤ የጫማ ማሰሪያ እንኳ ቢሆን ማለት ነው፡፡ አሏህ ካላገራው አይገራምና።

                                     አኢሻ (ረ.ዐ)

  1. ከእያንዳንዱ ደስታ ጀርባ ሀዘን አለ፤ ቤት በደስታ አይሞላም በሀዘን ቢሞላ እንጂ።

                                     አብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ)

  1. ሙታንን ስታስታውስ እራስህን ከእሱ አንዱ አድርገህ ቁጠር።

                                     አቡ ደርዳ (ረ.ዐ)

  1. ምላስን ከመቆጠብ የበለጠ ከባድ ሐጅም ፣ ጅሃድ ፣ ሪባጥም የለም።

                                     ፉደይል ኢብኑ ኢያድ (ረሂመሁላህ)

  1. አሏህን መታዘዝ እስከምትወድር ድረስ አሏህን እንደማትወድ እወቅ።

                                     ሐሰንል በስሪ (ረሂመሁላህ)

  1. በልብህ ውስጥ ድርቀት ፣ በሰውነትህ ውስጥ ድካም እና በሲሳይህ ውስጥ እጦት ካየህ፤ በማያገባህ እና በማይመለከትህ ነገር ውስጥ እንደዘባረቅክ እወቅ።

                                    ማሊክ ኢብኑ ዲናር (ረሂመሁላህ)

  1. ሞትን ፈልገው፤ ህይወት ይሰጥሃል።

                                    አቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ)

  1. አላህን ማውሳት (ዚክር) መድሃኒት ነው አጥብቃችሁ ያዙት፤ ሰዎችን ማውሳት ደግሞ በሽታ ነውና ተጠንቀቁት።

                                      ኡመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.ዐ)

  1. ልባችን ንፁህ ቢሆን ኖሮ የጌታችነን ንግግር (ሰምተን እና አንብበን) አንጠግብም ነበር።

                                      ኡስማን ኢብኑ አፋን (ረ.ዐ)

  1. ንግግር እንደ መድሃኒት ነው! ጥቂቱ ይጠቅማል ፣ ብዙው ደግሞ ይገድላል።

                                      አሊ ኢብኑ አቢ ጧሊብ (ረ.ዐ)

  1. ከእሱ በቀር ሌላ አምላክ በሌለው በአላህ እምላለሁ! በምድር ላይ ከምላስ የበለጠ ረጅም እስራት የሚያስፈልገው ነገር የለም።

                                       አብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ)

  1. ሰዎች ቢጠሏቸውም ሶስት ነገሮችን እወዳቸዋለሁ፡፡ ድህነት ፣ በሽታ እና ሞት ናቸው። ድህነትን ለጌታዬ ለመተናነስ እወደዋለሁ፤ ሞትን ጌታዬን ለመገናኘት በመጓጓት እወደዋለሁ፤ በሽታን ደግሞ ለሃጢያቴ ማበሻ እንዲሆን እወደዋለሁ።

                                       አቡ ደርዳ (ረ.ዐ)

  1. ሁለት ነገሮች ልብን ያደርቃሉ፡ ብዙ ንግግር እና ብዙ መብላት ናቸው።

                                       ፉደይል ኢብኑ ኢያድ (ረሂመሁላህ)

  1. ዱንያ ሶስት ቀናት ብቻ ናት! ትላንትና በውስጡ የነበረው ይዞ አልፏል፤ ነገን ደግሞ ላታገኘው ትችላለህ፤ ስለዚህ የዛሬዋን ቀን ምን እንደምትሰራባት ተመልከት።

                                      ሐሰንል በስሪ (ረሂመሁላህ)

  1. ከአመፀኞች ጋር ጣፋጭ ነገር ከመብላት፤ ከደጋጎች ጋር ድንጋይ መሸከም ይሻላል።

                                      ማሊክ ኢብኑ ዲናር (ረሂመሁላህ)

  1. አንድ የሐራም በር ላይ እንወድቃለን ብለን በመስጋት ሰባ የሐላል በሮችን እንተው ነበር።

                                      ኡመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.ዐ)

  1. አንድ ሰው ከቤቱ ሲወጣ የቲሃማ ተራራን የሚያክል ወንጀል ትቶ ሊወጣ ይችላል፡፡ እውቀት (ኢልም) ሲሰማ ይፈራል ፣ ከወንጀሎቹ ይመለሳል ፡ ወደ ቤቱ ሲመለስ ደግሞ ምንም ወንጀል አይኖርበትም፡፡ ስለዚህ የኡለማዎችን (የሊቃውንትን) መጅሊስ አትለዩ።

                                      ኡመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.ዐ)

  1. በእርግጥ ፀጋ ከምስጋና ጋር የተቆራኘ ነው፤ ምስጋና ደግሞ ከመሙላት (ከመትረፍረፍ) ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ሁለቱም በአንድ ገመድ የተሳሰሩ ናቸው። ከባሪያው በኩል ምስጋና እስካልተቋረጠ ድረስ ከአላህ በኩል መሙላት እና መትረፍረፍ አይቋረጥም።

                                      አሊ ኢብኑ አቢ ጧሊብ (ረ.ዐ)

  1. የአንሷር ሴቶችን አሏህ ይዘንላቸው፤ ሀፍረታቸው የዲን እውቀት ከመቅሰም አላገዳቸውምና።

                                      አኢሻ (ረ.ዐ)

  1. አሏህን እና መልእክተኛውን መውደዱን ማወቅ የፈለገ ሰው፤ ቁርአንን በመወድዱ አሏህን እና መልእክተኛውን መውደዱን ይመልከት።

                                      አብደላህ ኢብኑ መስዑድ (ረ.ዐ)

  1. የማትኖሩበትን ትገነባላችሁ ፣ የማትበሉትን ትሰበስባላችሁ ፣ የማታገኙትን ትመኛላችሁ፡፡ አታፍሩምን? ከእናንተ በፊት የነበሩት አጥብቀው ገነቡ ፣ ብዙ ሰበሰቡ ፣ ሩቅ ተመኙ፤ ቤቶቻቸው ቀብራቸው ፣ የሰበሰቡትም አመድ ፣ ተስፋቸውም ከንቱ ሆነ።

                                      አቡ ደርዳ (ረ.ዐ)

  1. ትህትና ማለት ለእውነት መገዛትና መታዘዝ ነው፡፡ ከህፃን ልጅ ብትሰማውም ትቀበለዋለህ፤ ከመሃይም ሰው ብትሰማውም ትቀበለዋለህ።

                                      ፉደይል ኢብኑ ኢያድ (ረሂመሁላህ)

  1. እውቀት አሏህ በፈለገው ቦታ ላይ የሚያስቀምጠው ብርሃን ነው፡፡ ብዙ በመዘገበ እነ ባስተላለፈ አይደለም።

                                      ኢማሙ ማሊክ (ረሂመሁላህ)

  1. በአንድ አማኝ ጎን በኩል ያለ ፀጉር ብሆን እመኝ ነበር።

                                      አቡበክር አስ-ሲዲቅ (ረ.ዐ)

  1. በእርግርግጥ በእናንተ ላይ በጣም የምፈራላችሁ ስሜትን መከተል እና ረጅም ምኞት ነው። ስሜትን መከተል ከእውነት ያርቃችኋል። ረዥም ምኞት ደግሞ አኼራን ያስረሳችኋል። አዋጅ! ዱንያ ጀርባዋን ሰጥታ ተጉዛለች፤ አኼራም ፊቷን አዙራ መጥታለች። እያንዳንዳቸውም ልጆች አሏቸው። እናንተም የአኼራ ልጆች እንጅ የዱንያ ልጆች አትሁኑ። ዛሬ ስራ እንጅ ምርመራ የለም፤ ነገ ደግሞ ምርመራ እንጅ ስራ የለም።

                                      አሊ ኢብኑ አቢ ጧሊብ (ረ.ዐ)

  1. ሞትን አብዝቶ የሚያስታውስ ሰው ደስታው እና ምቀኝነቱ ያንሳል።

                                      አቡ ደርዳ (ረ.ዐ)

  1. ቁርአንን የያዘ የእስልምናን ባንድራ የያዘ ሰው ነው፡፡ ከወሬኞች ጋር መዘባረቅ ፣ ከዘንጊዎች ጋር መዘናጋት ፣ ከቸልተኞች ጋር ቸል ማለት የለበትም፤ አይመጥነውምና። ቁርአንን ያያዘ ሰው ከፍጡራን ምንም ፍላጎት ሊኖረው አይገባም፤ ከኸሊፋዎችም ሆነ ከእነሱ በታች ካሉት ቢሆን እንኳ ማለት ነው። ይልቁንም የፍጡራኑ ጉፍላጎት ወደ እሱ ሊመለስ ይገባል።

                                      ፉደይል ኢብኑ ኢያድ (ረሂመሁላህ)

  1. መጠቃቀሚያየ የተወሰነባትን ይችን ዱንያ ፣ በመታዘዝ ህይወት የማገኝባትን እና በዚህ ደግሞ አኼራን የማገኝበትን እንዴት አልወድም?

                                      የህያ ኢብኑ ሙአዝ (ረሂመሁላህ)

  1. የተዋረድን ህዝቦች ነበርን፡፡ አሏህ በእስልምና ከፍ አደረገን (ክብርን ሰጠን)። ከፍታን ከእስልምና ውጭ ብንፈልግ አሏህ ያዋርደናል።

                                      ኡመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.ዐ)

  1. በላጩ ኢባዳ ግዴታዎችን መፈጸም እና ክልከላዎችን መራቅ ነው።

                                      ኡመር ኢብኑ አብዱልአዚዝ (ረሂመሁላህ)

  1. አማኝ ሰው በዚህ አለም ውስጥ እንደ እንግዳ ነው፡፡ በውርደቷ አይከፋ ፣ ለክብሯ አይፎካከር፡፡ እሱም የራሱ ጉዳይ አለው፤ ሰዎችም የራሳቸው ጉዳይ አላቸው።

                                      ሐሰንል በስሪ (ረሂመሁላህ)

  1. ሰዎች የአሏህን ትዕዛዝ ሲተው በአሏህ ዘንድ ምንኛ የተናቁ ናቸው! የበላይና አሸናፊ ህዝብ በነበሩ ጊዜ የአሏህን ትዕዛዝ ተው፤ እንደምታያቸውም ሆኑ።

                                      አቡ ደርዳ (ረ.ዐ)

  1. ስንት ምህረት ጠያቂ የተጠላ አለ፤ ስንት ዝምተኛ የታዘነለት አለ። ይህኛው ምህረትን ይጠይቃል ልቡ ግን አመጸኛ ነው፡፡ ይህኛው ደግሞ ዝም ይላል ልቡ ግን አሏህን ያወሳል።

                                      የህያ ኢብኑ ሙአዝ (ረሂመሁላህ)

  1. ሌሊት ሰጋጅ እና ቀን ፆመኛ የሆኑ የአንድ ሺህ ሰዎች ሞት፤ የአላህ ትዕዛዝ ከተረዳና አላህ የፈቀደለትንና የከለከለውን ካወቀ፤ በእውቀቱም እራሱንና ሰዎችን ከጠቀመ የአስተዋይ ሰው ሞት የቀለለ ነው። ምንም እንኳ አሏህ በእሱ ላይ በደነገገበት በግዴታዎች ላይ ብዙ ባይጨምርም ማለት ነው።

                                      ኡመር ኢብኑል ኸጣብ (ረ.ዐ)

  1. (ቁርአንን) እንደ ተምር ፍሬ መበተን አትበትኑት፤ እንደ ግጥም አታንበልብሉ። በድንቅ ነገሮቹ ላይ ቁሙ፤ ልቦችን በእሱ አንቀሳቅሱ፤ የአንዳችሁም ግብ የምዕራፉ መጨረሻ ላይ መድረስ አይሁን።

                                      አብደሏህ ኢብኑ መስኡድ (ረ.ዐ)

  1. ኢባዳን በማይጎዳ መልኩ እውቀትን ፈልጉ፤ እውቀትንም በማይጎዳ መልኩ ኢባዳን ፈፅሙ። ያለ እውቀት የሚሰራ ሰው ከሚያስተካክለው የሚያበላሸው ይበልጣልና።

                                      ሐሰንል በስሪ (ረሂመሁላህ)

  1. የአሏህን ውዴታ እሻለሁ እያለ ድንበሮቹን የማይጠብቅ ሰው ውሸታም ነው።

                                      የህያ ኢብኑ ሙአዝ (ረ.ዐ)

  1. ገንዘብ የዚህ ህዝብ በሽታ ነው፤ አሊም (ሊቅ) ደግሞ የዚህ ህዝብ ሃኪም ነው። አሊም ሰው በሽታን ወደራሱ ከሳበ ሰዎችን መቼ ሊያድን ነው?

                                      ሱፍያኑ ሰውሪ (ረሂመሁላህ)

  1. ሰዎች እነዚህን መጽሐፍት ቢማሩና ወደ እኔም ባይጠቅሷቸው እመኝ ነበር።

                                       ኢማሙ ሻፊኢ (ረሂመሁላህ)

ማጠቃለያ

እነዚህ ከደጋግ ቀደምቶች የተገኙ ኢስላማዊ ምክሮች ለዘመናት ሳይለወጡ የቆዩ የህይወት መመሪያዎች ናቸው። እነሱም የሚያስተምሩን እውነተኛ ስኬት እና የልብ መረጋጋት ያለው ዱንያን በመናቅ ሳይሆን በአግባቡ በመጠቀም ፣ ልብን በማጥራት ፣ ምላስን በመቆጣጠር እና በሁሉም ሁኔታ አላህን በማስታወስ ውስጥ መሆኑን ነው። እነዚህን የጥበብ ቃላት ማንበብ ብቻ ሳይሆን በህይወታችን ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ እንጣር።

ከእነዚህ ውድ ኢስላማዊ ምክሮች ውስጥ የትኛው ልብዎን የበለጠ ነካው? ሀሳብዎን ከታች ባለው የአስተያየት መስጫ ላይ ያካፍሉን።

Related posts

ሸሃዳ የእምነት ምስክርነት ቃል

ሸሃዳ የእምነት ምስክርነት ቃል

ሸሃዳ ማለት የእምነት ምስክርነት ቃል ነው። ላኢላሃ ኢለሏህ (ከአሏህ ውጭ ሌላ አምላክ የለም) ማለት ከአሏህ ውጭ በሃቅ ሊያመልኩት የሚገባ ሌላ አምላክ የለም ማለት ነው።

Read More »
መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች

መልእክት ለሙስሊም ወጣቶች፡ ሕይወትን በእስልምና ፣ በቁርአን እና በሱና መሰረት መኖር

ውድ ሙስሊም ወጣቶች! በዚህ ወሳኝ የሕይወት ምዕራፍ ላይ የምትገኙ ሙስሊም ወጣቶች ልባዊ ሰላምታችን እና ውዴታችን ይደረሳችሁ። ይህ ጊዜ የብርታት፣ የጉጉት፣ የእውቀት ፍለጋ እና ለወደፊት ህይወታችሁ

Read More »
ጀነት

ጀነት

ጀነት ሃያሉ አሏህ ለደጋግ ባሮቹ ያዘጋጀው ዘላለማዊ የደስታ ቤት ነው፡፡ ይህ ዘላለማዊ ደስታ አይን አይቶት ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅ ነው፡፡ ጀነት የሚገቡ ሰዎች የፈለጉትን ፣

Read More »

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Share