መግቢያ
“ጌታችሁም አለ «ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡፡»” ይህ የአላህ (ሱ.ወ) ቀጥተኛ ጥሪና የማይለወጥ ቃል ኪዳን ነው። ነገር ግን ዱዓ በኢስላም ያለው ቦታ ከዚህም የላቀ ነው።
ዱዓ የአምልኮ አንዱ አስኳል፣ የተጨነቀ ሰው መተንፈሻ፣ እና በባሪያና በጌታ መካከል ያለ ሚስጥራዊ ግንኙነት ነው። ብዙዎቻችን የምንለምነው ነገር ቢኖርም፣ የልመናችንን ሀይልና ጥበብ ሙሉ በሙሉ እንረዳ ይሆን?
በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የዱዓን ምንነት፣ የነብያትን (ዐ.ሰ) አርአያነት ያለው ልመና፤ እንዲሁም ዱዓችን ምላሽ የሚያገኝባቸውን አስደናቂ መንገዶች እንቃኛለን። ከፈጣሪዎ ጋር ያለዎትን ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ይዘጋጁ።
ለምኑኝ፤ እቀበላችኋለሁና፡ የአላህ ቀጥተኛ ጥሪ
ጥሪው ምንኛ ታላቅ ነው! ስጦታውስ ምንኛ የከበረ ነው! አሏህ ባሮቹን እንዲለምኑት ፣ እንዲማጸኑትና እንዲጠይቁት ይጠራቸዋል፡፡
ይህም ሊሰጣቸውና ሊቀበላቸው ነው። ልቦች ከፈጣሪያቸው ጋር የሚገናኙበትን የዱአ በር ከፍቶላቸዋል።
በሙሉ መተማመንና ጽናት የሚለምኑት ከእዝነቱ ይቀስማሉ። ዱዓ ማለት ፍላጎትን ለአላህ ብቻ ማቅረብ ነው።
«ለምኑኝ» የሚለውን ቃል አስተውሉ፤ ይህም ማለት ከእኔ ሌላ ማንንም አትለምኑ፤ ከእኔ ውጭ ያሉትን ጣዖታትና ፍጥረታትን አትለምኑ ማለት ነው።
ዱአ የአላህን የበላይነት ፣ ሥልጣኑንና በፈጠራቸው ላይ ያለውን ሃይሉን ማወጅና መቀበል ነው።
የነብያት ዱዓ፡ በታሪክ ገጾች ውስጥ የተቀረጸ አርአያ
የአሏህ ነብያት (ሰላም በእነሱ ላይ ይሁን) በሁሉም ፍላጎቶቻቸውና ጉዳዮቻቸው ላይ ጌታቸውን ከመለመን ተቆጥበው አያውቁም፡፡
ይልቁንም ለትንሹም ለትልቁም ፍላጎታቸው እጃቸውን ወደ እሱ በመዘርጋት አጥብቀው ይለምኑት ነበር።
- የነብዩላህ አደም (ዐ.ሰ) – የንስሐ ልመና:
እሱና ሚስቱ ስህተታቸውን በተረዱ ጊዜ እንዲህ ሲሉ ተማጸኑ፦ ‹‹ጌታችን ሆይ! ነፍሶቻችንን በደልን፤ በእርግጥ ባትምርልንና ባታዝንልን ከከሳሪዎች እንሆናለን።››
- ነብዩላህ ኑህ (ዐ.ሰ) – ከድንቁርና የመጠበቅ ልመና:
ነብዩላህ ኑህ (ዐ.ሰ) ደግሞ እንዲህ አለ፡ ‹‹ጌታዬ ሆይ! እኔ በእሱ እውቀት የሌለኝን ነገር አንተን ከመጠየቅ በአንተ እጠበቃለሁ፡ በእርግጥ ባትምረኝ እና ባታዝንልኝ ከከሳሪዎች እሆናለሁ።››
- ነብዩላህ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) – ለትውልድ የሚተርፍ ልመና:
ነብዩላህ ኢብራሂም (ዐ.ሰ) የቤቱን መሠረት ከልጁ ጋር ከፍ ሲያደርግ እንዲህ ሲል ዱዓ አደረገ፡ ‹‹ጌታችን ሆይ! ከእኛ ተቀበለን፤ አንተ ሰሚውና አዋቂው ነህና።››
ጌታችን ሆይ! ላንተ ታዛዦች አድርገን፤ ከዘሮቻችንም ላንተ ታዛዥ የሆነችን ሕዝብ አድርግ፤ የአምልኮ ሥርዓቶቻችነንም አሳየን፤ ፀፀታችነንም ተቀበለን።)
ፍላጎቶቻቸው የተለያዩ ነበሩ፤ ጥያቄዎቻቸውም ብዙ ነበሩ።
- ነብዩላህ ዘከርያ (ዐ.ሰ) – የመልካም ልጅ ልመና:
ነብዩላህ ዘከርያ (ዐ.ሰ) ከጌታው ልጅን በጠየቀ ጊዜ እንዲህ አለ፡-
አል-ቁርአን
(ሱረቱል አንቢያ 89)
‹‹ጌታዬ ሆይ! ብቻዬን አትተወኝ፤ አንተ ከወራሾች ሁሉ በላጭ ነህና።››
- የነብዩላህ ዳውድ (ዐ.ሰ) – በጠላት ላይ ድልን መለመን:
ነብዩ ዳውድ (ዐ.ሰ) በጠላቶች ላይ ድልን በጠየቀ ጊዜ እንዲህ አለ፡-
አል-ቁርአን
(ሱረቱል በቀራ 250)
‹‹ጌታችን ሆይ! በእኛ ላይ ትዕግስትን አፍስስ፤ እግሮቻችነንም አፅና፤ በከሃዲ ሕዝቦች ላይም እርዳን።››
የነብዩላህ አዩብ (ዐ.ሰ) – የበሽታ ፈውስ ልመና:
ነብዩላህ አዩብ (ዐ.ሰ) መከራው ጫፍ ሲደርስበት አላህን እየተማጸነ ፣ እየለመነ ጌታውን ካስቀመጠው ፣ ሰውነቱን ካደከመው በሽታ እንዲፈውሰው ጠየቀ፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል አንቢያ 83)
‹‹እኔ መከራ ነካኝ፤ አንተም ከአዛኞች ሁሉ ይበልጥ አዛኝ ነህ።››
- ነብዩላህ ሙሳ (ዐ.ሰ) – ለተልዕኮ መሳካት ሲለምን:
ነብዩላህ ሙሳ (ዐ.ሰ) ጌታውን ወደ አላህና ወደ አንድነቱ የመጥራትን ግዴታ ለመወጣት እንዲረዳው ልቡን እንዲያሰፋለት ጠየቀ፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱ ጦሃ 25-28)
‹‹ጌታዬ ሆይ! ልቤን አስፋልኝ፤ ነገሬንም ቀላል አድርግልኝ፤ ንግግሬን እንዲረዱ የምላሴም ቁጥር ፍታልኝ።››
እንደ ሁሉም ነብያት ለጌታቸው ታዘዋል፤ ጉዳያቸውንም ለፈጣሪያቸው አስረክበዋል፡-
አል-ቁርአን
(ሱረቱል አዕራፍ 155)
‹‹አንተ ጠባቂያችን ነህ፤ ማረን፤ እዘንልንም፤ አንተም ከመሃሪዎች ሁሉ በላጭ መሃሪ ነህና።››
ከዚያም ምሕረትንና እዝነትን እየጠየቀ ዱአ አደረገ፡-
አል-ቁርአን
(ሱረቱል አዕራፍ 155)
‹‹ለእኛም በዚህች ዓለም መልካምን ነገር ፃፍልን፤ በመጨረሻይቱም አለም መልካም ነገር ፃፍልን፡፡ በእርግጥ ወደ አንተ ተመልሰናልና።››
- የነብዩላህ ዩኑስ (ዐ.ሰ) – ከጭንቅ የመውጣት ልመና:
በተደራረበ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ የነበረው ነብዩላህ ዩኑስ (ሰላም በእርሱ ላይ ይሁን) በሌሊት ፣ በባሕርና በአሣ ነባሪ ሆድ ጨለማ ውስጥ ሆኖ እንዲህ አለ፡
አል-ቁርአን
(ሱረቱል አንቢያ 87)
‹‹ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ ጥራት ይገባህ፤ በእርግጥም ከበዳዮቹ ነኝ።››
የማይመለስ ልመና፡ የዱዓ ምላሽ እንዴት ይረጋገጣል?
የምንለምነው እንዴት ያለ አዛኝ ጌታን ነው! የምናመልከው እንዴት ያለ ጥበበኛ እና ሁኔታችነን የሚያውቅ አምላክን ነው!
ይህን ከእኛ ይወዳል፤ የማይለምነውም ላይ ይቆጣል። አሏህ ዘንድ የተስፋ በር ክፍት ነው፡፡ እዝነቱና በእኛ ላይ ስጦታው ጠዋት ማታ ይመጣል ይሄዳል።
ጌታውን የወደደ ሰው ወደ አምልኮቱ ፣ ወደ መታዘዙና ወደ ዱአ ይቻኮላል። በትክክለኛ ሐዲስ ላይ እንደተዘገበው፡
‹‹ማንኛውም ሙስሊም በውስጡ ሃጢአት ወይም ዝምድና መቁረጥ የሌለበትን ዱአ ወደ ጌታው አያደርግም፤ አላህ ከሦስቱ አንዱን ቢሰጠው እንጅ፡- ወይ ዱአው ቶሎ ይመልስለታል ወይም በመጨረሻው አለም ያከማችለታል ወይም ደግሞ ከእሱ ላይ መጥፎ ነገርን በዚያው ልክ ያስወግድለታል። እነሱም፡- እንግዲያውስ ዱአ እናብዛለን ያ ረሱለላህ? አሉ፤ እርሳቸውም (ሰ.ዐ.ወ)፡- ‘አላህ የበለጠ ብዙ ነው’ አሉ።››
ማጠቃለያ
ሲጠቃለል ዱዓ በኢስላም ውስጥ ያለው ቦታ ልመና ብቻ ሳይሆን የሙሉ ኢማን መገለጫ ነው። ከነብያት ታሪክ እንደተረዳነው፣ እያንዳንዱ የህይወት ምዕራፍ ከዱዓ ጋር የተቆራኘ ነው።
አላህ (ሱ.ወ) ሁሌም ሰሚና ተቀባይ ነው፤ ልመናችን ወይ በዱንያ በፍጥነት ይመለሳል፣ ወይ ለአኼራ ስንቅ ይሆናል፣ ወይም ደግሞ ከሚመጣብን መከራ ይጠብቀናል።
እጆቻችንን ወደ አላህ ከማንሳት የበለጠ ታላቅ መፍትሄ የለም።
እርስዎስ ከዚህ ጽሑፍ ምን ትምህርት ወሰዱ? የዱዓን ኃይል በህይወትዎ ተመልክተው ያውቃሉ? ሀሳብዎን ከታች ባለው የአስተያየት መስጫ ላይ ያካፍሉን።
3 thoughts on “ዱዓ በኢስላም፡ የነብያት መንገድ እና የምላሽ ሚስጥር”
After looking at a numkber of the articles on your web site, I
honestly appreciate your way of blogging. I added it to my bookmark
website list and wilpl bbe checking back inn thhe near future.
Take a look at my web siye too and tel me hhow you feel.
Wow that was unusual. I just wrote an very long comment but
after I clicked submit my comment didn’t appear. Grrrr…
well I’m not writing all that over again. Anyways, just wanted to say wonderful blog!
Thanks very nice blog!
Share